ስለ ሠመር ትምህርት ቤት መጓጓዣ

ጁላይ 5

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሠመር ትምህርት ቤት ቤተሰቦች፣

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለሁሉም የሰመር ፕሮግራሞቻችን ለተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ጉጉት አለን። ከ 600 በላይ የአውቶቡስ መስመሮች በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ከ175 በላይ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች የፕሮግራም ጣቢያዎች ያመላልሳሉ።
በአሁኑ ወቅት፣ ወደ ሠመር ፕሮግራማቸው መጓጓዣ ለሚፈልጉ ተማሪዎች ሁሉንም መስመሮች ሙሉ በሙሉ ሠራተኞችን መመደብ እንችላለን።ተማሪዎችን በአስተማማኝ ሁኔታ የማጓጓዝ ቁርጠኝነትን ማስቀጠል ቅድሚያ የምንሰጠው ቢሆንም፣ የሰው ሃይል አቅርቦት ፈታኝ መሆኑ ስለቀጠለ በየቀኑ ቁጥጥር ይደረግበታል። የሰራተኞቻችን ስራ በሠመር ወቅት በጣም የተጨናነቀ ስለሆነ ያልተጠበቁ መስተጓጎሎች ለምሳሌ በሰራተኞች ህመም ምክንያት ያልተሸፈነ የማጓጓዣ መስመር ሊያጋጥም ይችላል።

ማንኛውም የአውቶቡስ መስመር ከተስተጓጉለ፣ መረጃው በዋናው MCPS website/ድረገጽ ላይ 4:30–5 p.m. ከቀጣዩ የትምህርት ቀን በፊት በየቀኑ ይለጠፋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትራንስፖርት ዲፓርትመንት የመገናኛ አድራሻ እዚህ ይገኛል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools