ሐሙስ፣ ጁላይ 14 ማወቅ ያለብን ጉዳዮች

ሐሙስ ጁላይ 14 ስምንት ጉዳዮችን እነሆ። ዕድሜያቸው 5 እና ከዚያ በታች ለሆኑ ህጻናት የክትባት መረጃ፣ ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ጊዜ ትርኢት መረጃ፣ ስለ ፕራይመሪ ምርጫ ቀን ማሳሰቢያ፣ የሠመር ምግብ ቦታዎች እና ሌሎችም መረጃዎች ተካተዋል።

  1. ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና የሠመር ፕሮግራሞች በፕራይመሪ ምርጫ ቀን ጁላይ 19 ዝግ ይሆናሉ።

በርካታ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች የምርጫ ቦታዎች ናቸው። ስለዚህ ሁሉም የ MCPS ትምህርት ቤቶች እና የሠመር መርሃ ግብሮች ማክሰኞ፣ ጁላይ 19 ሁሉንም የማህበረሰብ ዝግጅቶች፣ የመዋእለ ሕጻናት፣ ካምፖች እና የጤንነት እንቅስቃሴ ማዕከላት ጭምር ይዘጋሉ። የሠመር ፕሮግራሞች ጁላይ 20 ይቀጥላሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ለየብቻ በኢሜል መረጃ ይደርሳቸዋል።

  1. የኮሌጅ ውይይቶች፡ከለር ተማሪዎችን ከከፍተኛ ኮሌጆች ጋር ያገናኛሉ።

college conversations hashtagይህ ሁነት ለሲንየር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከለር ተማሪዎች እና የኮሌጅ ምዝገባ ኃላፊዎች ነው። ይህ የቨርቹዋል ኮሌጅ ትርኢት በጁላይ 22 ከ6፡30 እስከ 8፡30 ፒ.ኤም ነው። ምሽቱ ለቀለም ተማሪዎች ከአቅማቸው ጋር በሚስማማ መልኩ ለኮሌጆች እና ዩኒቨርስቲዎች ልዩ ልዩ የቅበላ ሂደቶች እንዲጋለጡ ልዩ ልምድ ይሰጣል።
የ QR ኮድን በመጠቀም ወይም በዚህ አገናኝ ይመዝገቡ፡ rebrand.ly/2022college

  1. ቀኑን ያስታውሱ፡ MCPS ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት ቅዳሜ፣ ኦገስት 27 ይካሄዳል።

fairሁሉም የ MCPS ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው አዲሱን የትምህርት አመት ቅዳሜ ኦገስት 27 በ "Westfield Wheaton mall" የገበያ አዳራሽ10 a.m. እስከ 1 p.m. ባለው ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ስርዓቱ እና የካውንቲ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች እንዲያውቁ፣ ለቤተሰብ ተስማሚ ስለሆኑ እንቅስቃሴዎችና መዝናኛዎች፣ስለ ነጻ የኮቪድ-19 የክትባት ክሊኒኮች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ለማወቅ ጥሩ አጋጣሚ ነው።
አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road in Wheaton.
ስለ ዝግጅቱ የበለጠ ይረዱ።

  1. የፎል ወቅት አትሌቲክስ ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

ወላጆች እና አሳዳጊዎች አሁን ParentVue በመጠቀም የተማሪ-አትሌቶችን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፎል አትሌቲክስ ማስመዝገብ ይችላሉ። በኦንላይን የምዝገባ ሂደት የሚያግዙ መርጃዎች እዚህ ይገኛሉ። የፎል ወቅት ሙከራ ከመጀመሪያው ቀን በፊት ኦገስት 10, 2022 አካላዊ ግምገማ ይደረጋል። ቅጾችን እዚህ ያገኛሉ። በስፓኒሽ ቋንቋ ሪሶርሶች እዚህ ይገኛሉ። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል ወቅት አትሌቲክስ ምዝገባ ኦገስት 15, 2022 ይጀመራል። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአትሌቲክስ ምዝገባን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።

  1. በትምህርት ቤቶች የክትባት ክሊኒኮች በዚህ ሠመር ይቀጥላሉ

MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር ከ6 ወር እስከ 5 አመት እድሜ ያላቸው ህጻናት በት/ቤት-የክትባት ቦታዎች እየከተቡ ናቸው። ተጨማሪ መረጃ ያግኙ እና ቀጠሮ ይያዙ

  1. ስለ አእምሮ ጤና እና ደህንነት ጠቃሚ መርጃዎች አሉ።

mental healthይህ መረጃ ሰጪ በራሪ ወረቀት ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች አስፈላጊ መረጃን፣ የአደጋ ጊዜ ጥሪዎችን፣ ስለ MCPS መርጃዎችን እና የካውንቲ እና የአጋር ባለድርሻ አካላትን መረጃ የያዘ ነው። ስለ አእምሮ ጤና እና ደህንነት መርጃዎች በዚህ ድረገፅ www.montgomeryschoolsmd.org ይገኛሉ።

English /  español  / 中文  / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

  1. በ MCPS ጣቢያዎች የሚሰጡ ነፃ የሠመር ምግቦች

በካውንቲው ውስጥ 175 የሚጠጉ ጣቢያዎች በየሳምንቱ ባሉት ቀናት የነጻ ምግቦች አገልግሎት ይሰጣሉ። 18 እና ከዚያ በታች ያሉ ልጆች ሁሉም እና የአካል እና የአዕምሮ እክል ያለባቸው እስከ 21 አመት የሆኑ ወጣቶች ምግብ መቀበል ይችላሉ። ወደ ክፍት ቦታዎች በመሄድ እንዲሁ የምግብ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። የትምህርት ቤት መመገቢያ ቦታዎችን እና ጊዜዎችን ዝርዝር ይመልከቱ።

  1. ለዓመታዊ "GIVE Backpacks" ዘመቻ በመለገስ የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው

backpacksበ MCPS ትምህርት ቤቶች ላሉ ተማሪዎች የትምህርት እቃ መያዣ ቦርሳዎችን እና የት/ቤት አቅርቦቶችን ለማከፋፈል ለ11ኛው አመታዊ "GIVE Backpacks" ዘመቻ ለመለገስ ያስቡበት። በአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እና በዋጋ ንረት ምክንያት ለአንድ ቦርሳ የሚከፈለው ወጪ ወደ $15 በማደጉ እና ፍላጎቱ በጣም የጨመረ ስለሆነ አሁን ከምንጊዜውም በላይ የእርስዎን ድጋፍ እንፈልጋለን። በተቻለ መጠን ለብዙ ተማሪዎች በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ከት/ቤት አቅርቦቶች ጋር ቦርሳዎችን ለመስጠት MCPS በሠመር ወራት የግዢ ትእዛዝ ይሰጣል።
የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ልገሳ ያድርጉ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools

###



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools