ሁሉም አሁን አንድ ላይ፣ ሁሉም ለተማሪዎቻችን፣ ሰራተኞች እና ማህበረሰብ

August 29, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

እንኳን ለኣዲሱ ዓመት አደረሳችሁ!

የመጀመሪያው የትምህርት ቀን አዲስ ጅማሮ ሲሆን ካልተገደበ አቅማችን እና አብረን ለምንሰራቸው ነገሮች በሙሉ ከደስታ ጋር ነው። እንደ አስተማሪዎች፣ በሚማሩ ተማሪዎቻችን ትምህርታዊ እድገት ላይ ጥልቅ ሙያዊ ኩራት ይሰማናል። ማህበረሰባችን የት/ቤት ስርዓታችንን ስኬታማነት ያረጋግጣል፣ በህንፃዎቻችን ከሚገኙ ከቤተሰቦቻችን እስከ ባለሙያዎቻችን እንዲሁም እስከ ለአላማው የቆሙ የማህበረሰብ አጋሮችን ድረስ በጋራ እንሰራለን። ሞንትጎመሪ ካውንቲ የት/ቤት ስርዓት ልህቀት ላይ ኢንቨስት የሚያደርግ/የሚሰራ ማህበረሰብ ነው። የመጀመሪያው የትምህርት ቀን የማህበረሰብ የሚከበርበት በዓል ነው፣ ይሄም ማህበረሰብ የዛሬውን መንፈስ አመቱን ሙሉ ይዘን እንድንቀጥል ይረዳናል። ለዚህም ነው የመክፈቻ የት/ቤቶቻችን ጭብጥ/ዋና ሀሳብ፣ "ሁሉም በጋራ አሁን ላይ፣ ሁሉም ለተማሪዎቻችን" የሆነው።

አዲሱን አመት ስንጀምር፣ MCPS፣ በስትራቴጂያዊ ዕቅዳችን እንደሚጠበቅበት፣ ትምህርት ላይ የጨረር መሰል ትኩረት (laserlike focus) የሚኖረው። አስተማሪዎቻችን እያንዳንዱ ልጅ እንዴት እየሰራ እንደሆነ ያውቃሉ፤ የተማሪን ፍላጎቶች ለማሟላትም መረጃን ይጠቀማሉ። ተማሪዎቻችን ያላቸው እውቀት ላይ የላቀ እንደሚገነቡ፣ በክህሎቶቻቸው እንደሚጎለብቱ እና በትምህርት ላይ መሻት/ፍላጎት እንደሚኖራቸው እንጠብቃለን። ይሄ እንዲፈጠር በትጋት የሚሰሩ ምርጥ አስተማሪዎች፣ የድጋፍ ባለሙያዎች እና አስተዳደሮች አሉን።

ተግዳሮቶች ይኖሩብናል እና እኛም ተዘጋጅተን እየጠበቅናቸው ነው። ተማሪዎች ምርጥ በሆነ ብቃታቸው እንዲሰሩ እና የትምህርታዊ እድገታቸውን እንዲያሳኩ፣ ለአለንበት አለም በስሜት ጠንካራ፣ በአካል ደህንነታቸው የተጠበቀ እና በስነ-ልቦና ዝግጁ መሆን አለባቸው።

ይሄንን ስራ ቅድሚያ በምሰጣቸው ሦስት ነገሮች አንፃር/አይታ እንሰራለን፦

  • ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች እና ከማህበረሰብ ጋር መተማመንን መገንባት እና ዳግም መገንባት፣
  • የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን የአእምሮ ጤንነት እና ጤናማነት መደገፍ።
  • የዲስትሪክቱን ትኩረት ወደ ፍትሀዊ ማስተማር እና መማር መመለስ

ለተማሪዎቻችን፣ የሚከተለውን ፈተና አቀርባለሁ፦ በት/ቤት የሚቀርብላችሁን አስገራሚ እድሎች በደስታ ተቀበሏቸው። ለሁሉም የማህበረሰባችን አባላት፣ የማቀርበው ፈተና ይሄ ነው፦ በዚህ ስራ ላይ አጋራችን ሁኑ። በጋራ፣ የነገ ቃል-ኪዳን ብሩህ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን። በዚህ አስደሳች አዲስ የትምህርት አመት የመጀመሪያው ቀን ላይ፣ ይሄንን እድል አሁን እናገኛለን። ጊዜው አሁን ነው።

ለት/ቤት ዝግጁነት፣ ለምርቃት፣ ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁነት፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በጋራ ሆነው የተማሪዎቻችን ወደፊት የተሻለ እንዲሆን ያደርጋሉ። ይሄ በጣም አስፈላጊ ስራ ነው፣ እናም ማህበረሰባችን ከጎናችን እንደሚሆን እንተማመናለን። ሁሉም በጋራ አሁን ላይ፣ ሁሉም ለተማሪዎቻችን!

ከአክብሮት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D. 
Superintendent of Schools



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools