ሐሙስ፣ ኦገስት 15 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ለሐሙስ ሴፕቴምበር 15 አምስት ነገሮች እዚህ አሉ፡ ስለ ኮቪድ-19 መረጃ፣ የተሻሻለው የሞባይል መሳሪያ ደንብ እና ስለሁለት የMCPS ሰራተኞች መልካም ዜና።

 1. የተሻሻለ የተንቀሳቃሽ/ሞባይል መሳሪያ ፖሊስi ትግበራ ለ MCPS ተማሪዎች
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቦርድ የተሻሻለ ደንብ (COG-RA) አፅድቋል፣ የሚመለከተውም ስለተማሪዎች የግል ሞባይል መሳሪያዎች መያዝ እና አጠቃቀም ነው። ይሄ የደንቡ ማሻሻያ መመሪያዎች አሁን ላይ ከአሉ መልካም ተሞክሮዎች ጋር እንዲጣጣሙ ያደርጋል እና የተዘጋጀውም ከሰራተኞች፣ ከተማሪዎች እና ከማህበረሰብ አባላት በተውጣጡ የስራ ቡድን ትብብር ነው።
  Learn more
 1. በትምህርት ልህቀትን ስኮላርሺፕ እውቅና መስጠት (Scholarship Recognizing Academic Excellence) በኦክቶበር ይጀመራል
  ሩት እና ኖርማን ራልስ - ፓትሪሺያ ቤየር ኦኔል በትምህርት ልህቀትን ስኮላርሺፕ እውቅና መስጠት (Ruth and Norman Rales–Patricia Baier O’Neill Scholarship Recognizing Academic Excellence) ላይ ማመልከቻዎች በቅርቡ ይጀመራሉ። ይሄ ለሁለተኛ ደረጃ ተመራቂ ተማሪዎች $10,000 ስኮላርሺፕ የተገለፀው በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በሩት እና ኖርማን ራልስ - ፓትሪሺያ ቤየር ኦኔል ፋውንዴሽን (Ruth and Norman Rales–Patricia Baier O’Neill Foundation) ሲሆን፣ የተደረገውም ሩት እና ኖርማን ራልስ እና ፓትሪሺያ ኦኔል (Ruth and Norman Rales and Patricia O’Neill) ህይወትን እና አስተዋፆዎችን ለማክበር ነው፣ የሞቱትም ሴፕቴምበር 14፣ 2021 ላይ፣ በሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ታሪክ ከሁሉም የበለጠ ለረጅም ጊዜ ከአገለገሉ በኋላ ነው።
  ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.

 

 1. አዲሱን ኮቪድ-19 ያለባቸው የመነጠል/ብቻ የመሆን መመሪያዎች ተገንዘቡ
  ሰራተኞች እና ቤተሰቦች አሁንም የኮቪድ-19 ያለባቸውን ሪፓርት ማድረግ መቀጠላቸው አስፈላጊ ነው፣ ይሄንን የሚያደርጉትም በዚህ ኦንላይን ቅፅ ነው። የተሻሻለ የመነጠል መለኪያ የተቆራኘ/ሊንክ የተደረገው ወደ ስራ ወይም ት/ቤት መቼ ብትመለሱ ተገቢ እንደሚሆን መረዳት እንዲችሉ ነው። ማስታወሻ፦ ማንኛውም በምርመራ ውጤቱ ኮቪድ የያዘው/የያዛት ግለሰብ ክትባት የወሰደ(ች) ወይም ምልክት የሚታይበት(ባት) ቢሆንም ባይሆን ለአምስት ቀናት ራሱ(ሷ)ን ማግለል አለበ(ባ)ት። በልዩ ትምህርት አሰጣጥ ውስጥ— ማስክ በቋሚነት ማድረግ በማይቻልባቸው ሁኔታዎች ውስጥ— ግለሰቦች ለ 10 ቀን ተነጥለው እንዲቆዩ ሊጠየቁ ይችላሉ።
 1. የተሻሻሉ የኮቪድ-19 ቡስተሮች (Boosters) አሁን ላይ ይገኛሉ
  በቅርቡ፣ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከላት (CDC) ለተሻሻሉ የኮቪድ-19 ቡስተር (Booster) ክትባቶች እውቅና ሰጥቷል። ክትባቶቹ ባይቫለንት/ “bivalent” ናቸው፣ ይሄም ማለት የሚሰጡት ጥበቃ ለሁለቱ ለመጀመሪያው ኮቪድ-19 ለሚያስከስተው SARS-CoV-2 ቫይረስ፣ እና አሁን ላይ እየተስፋፋ ለአለው ሌላ መገለጫው የሆነው Omicron ተለዋጭ (BA-4 እና BA-5) ነው። ማንኛውም እድሜው ከ12 አመት በላይ የሆነ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰደ ሰው ቡስተሩን (booster) መከተብ ይችላል/ትችላለች። የ Pfizer ክትባት 12 አመት እና ከዛ በላይ ለሆናቸው የተፈቀደ ነው። የ Moderna ክትባት 18 አመት እና ከዛ በላይ ለሆናቸው የተፈቀደ ነው። ሁለቱም ቡስተር (booster) ክትባቶች መሰጠት ያለባቸው ከቀዳሚ ተከታታይ ክትባቶች በኋላ ነው፣ እናም የመጨረሻው ክትባት ወይም ቡስተር (booster) ከተወሰደበት ቀን አንስቶ ከስምንት ሳምንታት በኋላ ሊሰጥ ይችላል።
  እነዚህን ክትባቶች የት ማግኘት ይችላሉ፦
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጤና እና የሰው አገልግሎቶች ክፍል አሁን ላይ የተሻሻለውን ባይቫለንት / bivalent የኮቪድ-19 COVID-19 ቡስተር (booster) ክትባት እየሰጠ ነው ። ይሄም አሁን ላይ 12+ እድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት በካውንቲ-ስፖንሰር የተደረጉ ክሊኒኮች፣ ት/ቤት-መሰረት ያደረጉ ክሊኒኮችን ጨምሮ፣ ውስጥ የሚገኘው ብቸኛ ቡስተር (booster) ነው። ቀጠሮዎች ማስያዝ አሁን ላይ ይመከራል። የሜሪላንድ ክትባት ፈላጊዎች / Maryland's Vaccine Locator የቡስተር (booster) ቀጠሮዎችን እየሰጡ የሚገኙ ፋርማሲዎችን እና ሌላ ቦታዎችን በተመለከተ እና ይሄንን ቡስተር (booster) በሚመለከት አጋዥ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች / FAQ ላይ መረጃ ይሰጣሉ።
 1. መልካም ዜና፦ የሁለት MCPS ሰራተኞችን አስደሳች ታሪኮች ተመልከቱ
  ሮቤርቶ ካስቴሎ (Roberto Castillo)፣ MCPS የባስ መስመር ተቆጣጣሪ፣ የእሱን የስራ እና እድገት እና ለተማሪዎች ቁርጠኝነት ታሪክ ያካፍላል እና ትሬሲ ፓርከር (Tracey Parker)፣ በ ጁዲት ኤ. ረስኒክ (Judith A. Resnik) የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የልዩ ትምህርት መምህርት፣ ለተማሪዎቿ ያላት ፍቅር እንዴት በስራዋ እንድታድግ/እንድትወደው እንዳደረጋት ትናገራለች።
  ቪድዮ፦ ሮቤርቶ ካስቴሎ (Roberto Castillo)፣ የባስ መስመር ተቆጣጣሪ
  ቪድዮ፦ ትሬሲ ፓርከር (Tracey Parker)፣ የልዩ ትምህርት መምህርት

  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ  Montgomery County Public Schools 


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools