ሐሙስ፣ ኦገስት 22 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 22 መታወቅ የሚገባቸው ሰባት ነገሮች፦ MCPS የአትሌቲክስ ዝግጅቶች፣ የተማሪዎች የመከባበር ጥሪ፣ ለወላጆች ነፃ ESL ትምህርቶች፣ ስለ "Rockville Goes Purple" መረጃ፣ የሂስፓኒክ ቅርስ መታሰቢያ ወርን ማክበር እና ስለ MCPS የሙዚቃ መምህር የምስራች ዘገባዎችን ያካትታሉ።
athletes
ይህን ቪድኦ ይመልከቱ: https://youtu.be/78RPq1Krso8

 1. ተማሪ-የአትሌቲክስ መሪዎች በሁሉም የ MCPS ዝግጅቶች ላይ የመከባበር ባህሪ እንዲሰፍን ጥሪ አቅርበዋል
  የ MCPS አትሌቲክስ ፕሮግራም መሰረታዊ ዕሴቶች አክብሮትን እና ስፖርታዊ ጨዋነትን፣ በትምህርት ልህቀትን፣ ታማኝነት እና በጎ ባህሪን፣ በስሜት የተሞላ እና ደህንንነቱ የተጠበቀ ውድድርን፣ እንዲሁም ፍትሀዊነት እና ተደራሽነትን ያስተምራሉ እና ያጠናክራሉ። ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ MCPS ተማሪዎች ተመልካቾች፣ አትሌቶች እና ጎልማሶች የማይታዘዝ እና አክብሮት የጎደለው ባህሪን እምቢ በማለት እነዚህን እሴቶች እንዲያጠናክሩ የሚጠይቁበት ነው። 
  እነዚህን ቀላል መመሪያዎች ይከተሉ፦
  1. የተማሪ-አትሌቶችን ለጥረታቸው አድናቆታችሁን ስጡ።
  2. የዳኞችን እና የአሰልጣኞችን ውሳኔዎች ተቀበሉ።
  3. ሁሉንም ተሳታፊዎች ለአሳዩት ቁርጠኝነት አድናቆታችሁን ስጡ።
  4. የት/ቤት ሰራተኞች በስሜት የተሞላ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ውድድር እንዲያካሂዱ ደግፏቸው።
  5. እረፍቶች ከቡድንዎ ጋር የሚቃረኑ በሚመስሉበት ጊዜም መረጋጋትዎን ያስቀጥሉ።
  6. የሌሎች ተመልካቾችን መብቶች አክብሩ።
  7. የስፖርታዊ ጨዋነት ባህሪን በማበረታታት ሸልሙ።
  8. ትኩረትዎን የውድድር መልካም መገለጫዎች ላይ አድርጉ።
  9. የተማሪ-አትሌቶችን በሞቀ ስሜት እና መልካም እውቅና በመስጠት አበረታቱ።
  10. ለተማሪ-አትሌቶች ድህንነት እና ጤናማነት አሳቢነታችሁን አሳዩ።
  11. ማንኛውም ያልተገቡ ወይም አግላይ አስተያየቶችን እና ባህሪያትን ለት/ቤት ሰራተኞች ሪፖርት አድርጉ።
   ጨዋታዎችን በሠላም እንዲካሄዱ ምን ማድረግ እንደሚችሉ (የተማሪ ዳሰሳ ጥናት) ላይ ተማሪዎች አጋሮቻቸውን ሃሳብና አስተያየት እንዲሰጡ እየጠየቁ ናቸው።
 1. athleticsለአትሌቲክስ ዝግጅቶች የተሻሻሉ የደህንነት ጥበቃ እርምጃዎች ይፋ ተደርገዋል
  MCPS ከነገ አርብ ሴፕቴምበር 23 ጀምሮ በአትሌቲክስ ዝግጅቶች ላይ በርካታ የተሻሻሉ የደህንነት እርምጃዎችን ተግባራዊ ያደርጋል። ዲስትሪክቱ በተለያዩ የአትሌቲክስ ውድድሮች መደሰት ለሚፈልጉ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት ደህንነት እና ሠላም ቁርጠኛ ነው። በዚህ ፎል ወቅት የመክፈቻ ሳምንታት የተከሰቱት የማይታለፉ እና የጥቃት ባህሪ እና ድርጊቶች በቀላል የሚታዩ አይደሉም። እነዚህ እርምጃዎች ከሴፕቴምበር 23 ጀምሮ በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጨዋታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
 1. ኦሎምፒያን ቶኒ ሆፍማን ስለአእምሮ ጤና፣ ስለ ሱሰኝነት እና ማገገም ሴፕቴምበር 27 ንግግር ያደርጋል
  Rockville Goes Purple ቶኒ ሆፍማን ከእስር ቤት ወደ ኦሎምፒክ የተጓዘበትን ባለ ድል ኮከብ አትሌት ንግግር ያቀርባል። የቀድሞ የ BMX አሽከርካሪ እና አሰልጣኝ ቶኒ ታሪኩን እና በአእምሯዊ ጤንነት፣ በአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም እና በማገገም መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያካፍል ሲሆን፣ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣ ትምህርት ቤቶች እና ማህበረሰቦች የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀም መዛባትን ለመከላከል ወይም ለማከም ምን ማድረግ እንደሚችሉ ያብራራል። ይህ ዝግጅት ነፃ እና ለህዝብ ክፍት ነው።
  መቼ? ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 27፣ 6-8፡30 ፒ.ኤም
  የት? በሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ
  እንዴት፡ ቲኬቶች በ Eventbrite በኩል እንደሚገኙ
 1. esl classesየሊተርሲ ካውንስል ለ MCPS ወላጆች ESL ትምህርት በነፃ ይሰጣል
  ከ MCPS ጋር በመተባበር የሞንትጎመሪ ካውንቲ (LCMC) የሊተርሲ ካውንስል (LCMC) እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋ ለሆነ የ MCPS ወላጆች በነፃ የእንግሊዝኛ ትምህርት ይሰጣል። ትምህርቶቹ የሚካሄዱት በቨርቹወል እና በአካል ሲሆን በሁሉም ደረጃ የእንግሊዝኛ ትምህርት አማራጮች አሉ። ትምህርቱ እንግሊዝኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ላልሆነ ማንኛውም የ MCPS ወላጅ ይሰጣል። ወላጆች የምደባ ፈተና ለመቀበል  ይህንን የፍላጎት መግለጫ ቅጽ መሙላት ይችላሉ።
  ክፍል እንደሚገኝ እና የምዝገባ ሂደትን በተመለከተ ጥያቄዎች ያሏቸው ወላጆች ለኬቨን ራልፍ (Kevin Ralph) LCMC kevin@lcmcmd.org ኢሜይል ማድረግ ወይም 240-665-0471 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
 1. hispanic heritageየሂስፓኒክ ቅርስ የሚከበርበት ወር
  የትምህርት ቦርድ ከሴፕቴምበር 15 እስከ ኦክቶበር 15 የሂስፓኒክ ቅርስ ወር እንዲሆን ደንግጓል። ወሩን በሙሉ፣ የ MCPS ትምህርት ቤቶች የስፔይን ዝርያ ያላቸውን እና ሌሎች የስፓንሽ ተናጋሪ አገሮችን በሰሜን አሜሪካ፣ ሴንትራል አሜሪካ፣ ሳውዝ አሜሪካ እና የካሪቢያን ተማሪዎችን፣ አስተማሪዎችን፣ ሠራተኞች እና የማህበረሰብ አባላትን ልዩ ባህል እና ልማዶችን ያከብራሉ።
  የበለጠ ግንዛቤ  እዚህ ያግኙ፦
 1. ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ስለ ግል የሞባይል ስልክ አጠቃቀም ተሻሽሎ የተዘጋጀ ደንብ
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቦርድ የተሻሻለ ደንብ (COG-RA) አፅድቋል፣ የሚመለከተውም ስለተማሪዎች የግል ሞባይል መሳሪያዎች መያዝ እና አጠቃቀም ነው። ይሄ የደንቡ ማሻሻያ መመሪያዎች አሁን ላይ ከአሉ መልካም ተሞክሮዎች ጋር እንዲጣጣሙ ያደርጋል እና የተዘጋጀውም ከሰራተኞች፣ ከተማሪዎች እና ከማህበረሰብ አባላት በተውጣጡ የስራ ቡድን በትብብር ነው።
  ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
 1. መልካም ዜና፡ የኬኔዲ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሙዚቃ መምህርት የፕሮፌሽናል ስኬት ሽልማት አሸነፈች!
  በጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (John F. Kennedy High School) የሙዚቃ መሳሪያ አስተማሪ የሆነችው አማንዳ ሄሮልድ (Amanda Herold) በጌቲስበርግ ኮሌጅ ተመራቂ በነበረችበት ወቅት ለሙዚቃ ትምህርት ዘርፍ የላቀ ቁርጠኝነት እና ችሎታ በማሳየቷ በብሔራዊ የሙዚቃ ትምህርት ለሙያዊ ስኬት ሽልማት በመመረጧ እንኳን ደስ አለሽ እንላለን! ስለ ሽልማቷ እዚህ እና እዚህ የበለጠ ማንበብ ትችላላችሁ።
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ

  Montgomery County Public Schools 

 

 Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools