ለሐሙስ፣ ኦክቶበር 13 ማወቅ ያለብዎት ስምንት ጉዳዮችን እነሆ! ስለ አውቶቡስ ደህንነት መረጃ፣ የአውቶቡስ መስመር ሲዘገይ ወይም ሲሰረዝ ምን እንደሚፈጠር፣ የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ ማሻሻያ፣ የተማሪ እድገት ሪፖርቶች፣ አጋዥ ስልጠናዎች፣ የተማሪ አገልግሎት ሠዓት (SSL) እድሎች እና ሌሎችንም ያካትታሉ።
ስለ ትምህርት ቤት አውቶቡስ ደህንነት ጠቃሚ ምክሮች
የአውቶቡስ ሹፌሮችን በመመልመል፣ በመቅጠር እና ሥራ ላይ በማቆየት ረገድ ለትምህርት ስርዓቱ እና ለትራንስፖርት ኢንዱስትሪዎች በአካባቢ ደረጃም ሆነ በሀገር ውስጥ ከባድ ፈተና አለ። የአውቶቡስ ሹፌር ወይም ረዳት በህመም ወይም ባልተጠበቀ ምክንያት በፈቃድ ወደ ሥራ መምጣት ካልቻለ(ች)፣ አውቶቡሱን ወደ ሥራ ለማሠማራት በሲስተሙ ላይ ጫና ይፈጥራል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትራንስፖርት ዲፓርትመንት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በየቀኑ ለማድረስ በተቻለ መጠን በቂ አውቶቡሶች መሠማራታቸውን ለማረጋገጥ ተተኪ ሾፌሮችን ይጠቀማል እና በርካታ ጉዞዎችን ያደርጋል። የአውቶቡስ መስመር መሰረዝ የመጨረሻ አማራጭ ነው።
የልጅዎ የአውቶቡስ መስመር ከዘገየ ወይም ከተሰረዘ፣እንዴት እንደምናሳውቅዎት እነሆ፡-
መሸፈን ያልተቻለ የአውቶቡስ መስመሮች ከአንድ ቀን በፊት ወይም በማለዳው 6፡15 a.m. ይፋ ይደረጋል። |
መልእክቱ የሚተላለፈው MCPS ድረገጽ እና ConnectEd መልዕክት ላይ ይላካል። |
ሽፋን ላላገኙ የአውቶቡስ መስመሮች የትራንስፖርት ዲፓርትመንት አሽከርካሪዎችን ለማግኘት ጥረት ያደርጋል። |
የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርድ እስከ 9፡30 a.m. ድረስ በየግማሽ ሰዓቱ ይለጣል። |
የከሰዓት በኋላ የአውቶቡስ መስመሮችን በሚመለከት |
የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርድ 1፡30 p.m. ላይ ይወጣል። |
ስለማንኛውም የት/ቤት አውቶቡስ መስመር መስተጓጎል ለርእሰ መምህራን እና የ MCPS አመራር ይገለፅላቸዋል።
የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርዱን ይመልከቱ።
የትምህርት ቦርድ ስለ MCPS ፀረ-ዘረኝነት ኦዲት "Mid-Atlantic Equity Consortium, Inc." ከተሰኘ ገለልተኛ ኦዲት ኦክቶበር 11 ህዝባዊ ገለጻ አግኝቷል። ሪፖርቱ MCPS ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች እና ለሰራተኞች የዘር ልዩነቶችን ለማስወገድ የሚያስፈልጉ ብዙ ነገሮች እንዳሉት አረጋግጧል። ነገር ግን ጥናቱ ፀረ ዘረኝነትን የትም/ቤት ስርዓትን ለማሳካት MCPS ግልፅ፣ ስርአት አቀፍ አጠቃላይ አቀራረብን እንዲያዳብር ይጠይቃል። ኦዲቱ ተከታታይ ምክረሃሳቦችን ለይቶ አቅርቧል፣ እነዚህን ምክረሃሳቦች ለማንበብ ከዚህ በታች የተያያዘውን ሙሉውን የፀረ-ዘረኝነት ኦዲት ይመልከቱ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ የፕሮግራም ስራዎችን ማከናወን ይቀጥላል። የቫርሲቲ ፉትቦል ጨዋታዎች በዚህ ጊዜ በደረጃ 1 ውስጥ ይቀጥላሉ፣ የደረጃ 2 ጨዋታዎች በተናጠል ሊተገበሩ ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ደረጃ የውሳኔ አሰጣጥ መመሪያዎች በደህንነት እቅድ ውስጥ ተዘርዝረዋል። ለሌሎች ስፖርቶች፣ የአካባቢ ትምህርት ቤቶች ለደረጃ 1 ገደቦችን በማሻሻል ተገቢውን መስተንግዶ ሊያደርጉ ይችላሉ፣ ለምሳሌ የመግቢያ ሂደቶችን ማሻሻል (የምዝገባ እና/ወይም የግማሽ ሰዓት ጨዋታ መግቢያ)። MCPS በመላው ፕሮግራሙ ላይ የሚከናወኑትን ድርጊቶች ተጽእኖ መገምገም ይቀጥላል፥ ማሻሻያዎች ከተደረጉ ለማህበረሰቡ ያሳውቃል።
የመጀመሪያው የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜ ሪፖርቶች ከመዋእለ ህጻት እስከ 12ኛ ክፍል (K-12) ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ዛሬ ይሰራጫሉ። ParentVUE አካውንት ያላቸው ተማሪዎች እና ወላጆች፣ ሪፖርቱን PreentVUE እና StudentVUE ውስጥ ባለው የሰነዶች ፋይል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ። ParentVUE አካውንት ለሌላቸው ተማሪዎች ወላጆች፣ እነዚህ ሰነዶች ወደ ቤት የሚላክላቸው ስለሆነ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ይደርሳቸዋል። እነዚህን ሰነዶች በተመለከተ ጥያቄዎች ካሏችሁ ወደ ልጅዎ ትምህርት ቤት መቅረብ አለባቸው። ለመክፈት ወይም ስለ ParentVUE እዚህ የበለጠ ይወቁ።
ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በርካታ በነጻ የማስጠናትና የማስተማሪያ አማራጮች አሉ። "FEV Tutor እና Tutor Me Education" በነፃ፣ ቨርቹወል ያስጠናሉ። ተማሪዎች ወደ "Clever accounts" በመግባት፣ የማጠናከሪያ ክፍለ ጊዜን መቀላቀል ይችላሉ። ሁለቱም ኩባንያዎች አንድ አይነት ሁለት አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፡- በፍላጎት የቤት ስራ እርዳታ ለሚፈልጉ ምንም አይነት ቀጠሮ ሳይያዝ እና በቀጠሮ የሚሰጥ፣እንዲሁም ለረጅም ጊዜ የማስጠናት ድጋፍ ለሚፈልጉት ቀጣይነት ያለው ትምህርት ይሰጣሉ።
FEV Tutor ተጨማሪ መረጃ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ይገኛል ከ3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ያለ ካሜራ ምርጥ ትምህርትን ይሰጣል። የማስጠናት ክፍለጊዜ ለመሣተፍ: mcps@fevtutor.com |
Tutor Me Education |
ኖቨምበር 1 ቀን 1864 ሜሪላንድ በህዝብ ድምጽ በተሰጠው የህገ መንግስት ማሻሻያ ባርነትን ያስወገደበትን ቀን ለመዘከር በየዓመቱ ኖቨምበር 1 በሜሪላንድ የነጻነት ቀን ይከበራል። በሕዝብ ድምፅ ባርነትን ለማስወገድ ሜሪላንድ የመጀመሪው ስቴት ነው። MCPS ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን የአካባቢውን የነጻነት ቀን አከባበር Button Farm Living History Center ኦክቶበር 29፣ 2022፣ ከ 12 p.m. - 3 p.m. እና ሳንዲ ስፕሪንግ ስሌቭ ሙዚየም/Sandy Spring Slave Museum ኖቨምበር 5፣ ከ 10 am - 4 a.m.. እንዲጎበኙ ያበረታታል። ተማሪዎች ከተገኙ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ቦታው ላይ ስትደርሱ SSL ቅጾችን ለማግኘት የ MCPS ጠረጴዛዎች ላይ ይመልከቱ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአትሌቲክስ ውድድሮች ባለስልጣኖች እና ዳኞች ቁርጠኝነት ሳይታከልበት አይካሄዱም። ከሜሪላንድ የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አትሌቲክስ ማህበር (MPSSAA) ጋር በመተባበር MCPS ፎል የአትሌቲክስ ኃላፊዎች የምስጋና ሳምንት ኦክቶበር 10-15 ያከብራል። እባኮትን ጨዋታዎቹ እንዲቀጥሉ በማድረጋቸው ዳኞችን ለማመስገን ጊዜ ይውሰዱ!
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org