ሐሙስ፣ ኦክቶበር 20 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ለሀሙስ ኦክቶበር 20 መታወቅ ያለባቸው ስድስት ጉዳዮችን እነሆ! ስለ ስፖርት ሻምፒዮናዎች፣ የተሻሻለ የአውቶቡስ መረጃ ዳሽቦርድ፣ ለትራንስፖርት ሰራተኞቻችን አክብሮት፣ አንድ ትምህርት ቤት የእግር ኳስ ቡድን ምልመላ እንዴት ማከናወን እንደቻለ እና አንዳንድ ማሳሰቢያዎችን በተመለከተ መረጃ ያገኛሉ።

 1. transportation updatesየአውቶቡስ ትራንስፖርት ዳሽቦርድ ተሻሽሏል
  የልጅዎ የት/ቤት አውቶቡስ ትራንስፖርት መዘግየቱን ወይም መሰረዙን ማወቅ ይፈልጋሉ? MCPS የትራንስፖርት ማሻሻያ ዳሽቦርዱን ይክፈቱ እና የልጅዎን ባለአራት አሃዝ የትራንስፖርት መስመር ቁጥር ያስገቡ። ዳሽቦርዱ በአዲስ መልክ የተዘጋጀ ስለሆነ ከአሁን በኋላ መረጃ በ 15 ደቂቃ ይለዋወጣል። የአውቶቡስ መስመር መሰረዝ የመጨረሻ አማራጭ ነው፣ ነገር ግን ሲከሰት ለሚመለከታቸው ቤተሰቦች ConnectEd ኢሜይል በቀጥታ ይገለጽላቸዋል።
  የልጅዎ የአውቶቡስ መስመር ከዘገየ ወይም ከተሰረዘ፣እንዴት እንደምናሳውቅዎት እነሆ፡-

መሸፈን ያልተቻለ የአውቶቡስ መስመሮች ከአንድ ቀን በፊት ወይም በማለዳው 6፡15 a.m. ይፋ ይደረጋል።

መልእክቱ የሚተላለፈው MCPS ድረገጽ እና ConnectEd መልዕክት ላይ ይላካል።

ሽፋን ላላገኙ የአውቶቡስ መስመሮች የትራንስፖርት ዲፓርትመንት አሽከርካሪዎችን ለማግኘት ጥረት ያደርጋል።

የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርድ በየ15 ደቂቃው እስከ ጠዋቱ 9፡30 a.m. ድረስ ይቀያየራል።

የከሰዓት በኋላ የአውቶቡስ መስመሮችን በሚመለከት

የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርድ 1፡30 p.m. ላይ ይወጣል።

ስለማንኛውም የት/ቤት አውቶቡስ መስመር መስተጓጎል ለርእሰ መምህራን እና የ MCPS አመራር ይገለፅላቸዋል።
የአውቶቡስ መስመር መረጃ ዳሽቦርዱን ይመልከቱ።

 1. school busብሔራዊ የትምህርት ቤት አውቶቡስ ደህንነት ሳምንት ነው - ከትራንስፖርት ዲፓርትመንታችን የተወሰኑ ድንቅ ሰራተኞችን ያግኙ
  MCPS የትራንስፖርት ሰራተኞች በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ የሚደነቁ ሰዎች ከመሆናቸውም በላይ፣ ቁርጠኞች፣በሙያ የተካኑ እና ተማሪዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቀልጣፋ ጉዞ ወደ ትምህርት ቤት ለማድረስ ጥረት የሚያደርጉ ናቸው።
  ብሔራዊ የትምህርት ቤት አውቶብስ ደህንነት ሳምንትን ስናከብር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ካቀረብናቸው ታታሪ ሰራተኞች መካከል ጥቂቶቹን ማግኘት ይችላሉ።

ያግኟቸው: Bertha Reyes (ሾፌር)Barbara Busby (አቴንዳንት)Jose Lopez (መካኒክ)
ይህን ምርጥ ቡድን ማግኘት ይፈልጋሉ? ክፍት ቦታዎች አሉን! ለማመልከት ይህን ድረገጽ ይጎብኙ

 1. athleticsለብዙ ስፖርቶች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ወቅት ተጀምሯል
  የፎል ወቅት ስፖርት እያለቀ ስለሆነ ሻምፒዮናዎች እየተጀመሩ ነው። ለተማሪ-አትሌቶች እና ለተመልካቾች አስደሳች ጊዜ ነው። ከእግር ኳስ እስከ ፊልድ ሆኪ፣ ቮሊቦል፣ ቺርሊዲንግ፣ ጎልፍ እና ሌሎችም ለሁሉም የስፖርት አፍቃሪዎች የተሟላ የዝግጅት መርሃ ግብር ወጥቷል። ይህንን በአህጽሮት የተጻፈ ዝርዝር እዚህ ይመልከቱ።
 2. የላቲኖ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ስራ ቡድን ዛሬ ማታ፣ ኦክቶበር 20 የጎልማሳ የአእምሮ ጤና ፓናል ያስተናግዳል።
  የላቲኖ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት የስራ ቡድን በወጣቶች ላይ ከአእምሮ ጤና ጋር የተያያዙ የተሳሳቱ አመለካከቶችን እና መገለሎችን ለመፍታት እና ስለ ማህበረሰብ ሪሶርሶች መረጃ ለመስጠት በስፓኒሽኛ ቋንቋ ቨርቹወል ውይይት ያካሄዳል። ውይይቱ ዛሬ ማታ፣ ኦክቶበር 20 ከ 6-7 ፒኤም ይሆናል። ወላጆች ለመሳተፍ መመዝገብ ይችላሉ። Zoom webinar ወይም በፌስቡክ Facebook የቀጥታ ስርጭት MCPS en Español, Montgomery County en Español, Latino Health Initiative ወይም Identity
  ተሳታፊዎች በዝግጅቱ ወቅት ወይም በዙም ዌቢናር ላይ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ።
 1. helmetከዜና ላይ፦
  በዋሽንግተን ፖስት ተለይቶ የቀረበ፡
  የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ ሚካኤል ኤሪጎ (Michael Errigo) በክላርክስበርግ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አሰልጣኞች ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች መልቀቅን ለመቅረፍ ያደረጉትን ልዩ ሁኔታ ይተርካል። ብዙ ተማሪዎች በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በእግር ኳስ ፕሮግራም ተመርቀዋል።
  እንዴት እንዳደረጉ ከዚህ ርእሰ አንቀጽ በንባብ ይመልከቱ።
 2. የመዝጊያ ማስታወሻ፡ ማሳሰቢያዎች
 • ስም-የማይገለጽ የትምህርት ቤቶች ደህንነት የጥቆማ መስመር

ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት አካባቢን ስለመደገፍ ደጋግመን እንናገራለን፣ “አንድ ነገር ካዩ ወዲያው ይናገሩ/If you see something, say something። የሜሪላንድ ሠላማዊ ት/ቤቶች የጥቆማ መስመር ለተማሪዎች፣ለመምህራን፣ለትምህርት ቤት ሰራተኞች፣ለወላጆች እና ለመላው ህብረተሰብ ማንኛውንም የት/ቤት ወይም የተማሪ ደህንነት ስጋቶች፣ የአእምሮ ጤና ስጋቶችን ጨምሮ ሪፖርት ለማድረግ ስም ይፋ የማይደረግበት ነፃ የሪፖርት አቀራረብ ስርዓት ነው። አገልግሎቱ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት ሰባት ቀን፣ በዓመት 365 ቀናት ይሰጣል።
(1-833-MD-B-SAFE / 1-833-632-7233)
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

 • የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት ስኬት

ወጣቶች እና ቤተሰቦች ለእነሱ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እንዲሰሙ እድል ለመስጠት MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች ማህበር ኦክቶበር 10-15 ነጻ ቨርቹወል ዝግጅቶችን አስተናግደዋል። የቀረቡትን ሁሉንም ጠቃሚ ሪሶርሶች ይመልከቱ።

 • ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ነጻ የማስጠናት ጊዜ ይሰጣል።
 • FEV Tutor

ተጨማሪ መረጃ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ
ከ 3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ያለ ካሜራ ምርጥ ትምህርት ይሰጣል።
በማስጠናት ክፍለጊዜ ለመሣተፍ: mcps@fevtutor.com

 • Tutor Me Education

ተጨማሪ መረጃ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ
የማስጠናት ክፍለ ጊዜ ለመሳተፍ: MCPS@tutormeeducation.com or 240-618-2549

 • በሜሪላንድ የነጻነት ቀንን በመደገፍ የተማሪ አገልግሎት ሠዓት (SSL) ያግኙ

የነጻነት ቀን ክብረበዓል በ Button Farm Living History Center ኦክቶበር 29፣ ከእኩለቀን - 3 p.m. እና በ Sandy Spring Slave Museum ኖቨምበር 5፣ ከ 10 a.m.–4 p.m. ይከበራል። በክብረ በዓሉ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools