ለሐሙስ ኖቨምበር 10 ማወቅ ያለብን ስድስት ጉዳዮች

ሐሙስ ኖቨምበር 10 ማወቅ የሚገባን ስድስት ጉዳዮችን እነሆ!
ስለመጪው የበጀት መረጃ ውውጥ ክፍለ ጊዜ፣ ስለ ቅርብ ጊዜው የደህንነት ፕሮቶኮል ስልጠና፣ በትምህርት ቤት ካላንደር ላይ አስተያየት/ግብአት እንዴት መስጠት እንደሚቻል፣
ለአውቶቡስ ኦፕሬተር የስራ መደቦች እንዴት ማመልከት እንደሚቻል፣ የመታሰቢያ እና የእርቅ ወር የመረጃ ልውውጥ ወርክሾፖች እና ስለዚህ ሳምንት አትሌቲክስ የሚመለከቱ ናቸው።

 1. budget info. sessionsስለ ዲስትሪክቱ የበጀት አሠራር ሂደት  ለማወቅ በዚህ ቅዳሜ ከእኛ ጋር ይሁኑ
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከሶስቱ የማህበረሰብ የበጀት መረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜዎች የመጀመሪያውን ያስተናግዳል በዚህ ቅዳሜ ኖቨምበር 12። ይህ ለ 2024 የበጀት ዓመት ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክኒት ያቀረቡት የስራ ማስኬጃ በጀትን እንዴት ለመገንባት እንደታቀደ ለማወቅ እድል ይሰጣል። ስብሰባው የሚካሄደው በሚድ-ካውንቲ ሪጅናል አገልግሎት ማዕከል ነው፦ Mid-County Regional Services Center, 2425 Reedie Dr., 2nd Floor, Wheaton, MD 20902, 11 a.m.–12:30 p.m.
  እባክዎ ይመዝገቡ
  የሚቀጥለው የውይይት መድረክ፡ ሰኞ፥ ኖቨምበር 28 (6፡30 - 8 p.m.) ቨርቹወል ይካሄዳል

 2. ስለ ደህንነት እና የደህንነት ፕሮቶኮሎች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችዎ መልስ አግኝተዋል።
  ለድንገተኛ ሁኔታዎች መዘጋጀት ብዙ ጊዜ ጥያቄዎችን እና ስጋቶችን ያስነሳል።ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተሻሻለው የደህንነት እና የሰኩሪቲ ፕሮቶኮል ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ናቸው። መረጃ ለመስጠት እና ቤተሰቦችን ለማረጋጋት MCPS ተደጋግሞ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ዝርዝር አዘጋጅቷል።
 1. calendar2023–2024 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ (ካለንዳር) ላይ የእርስዎን ሃሳብ/አስተያየት ይስጡ
  እባኮትን ስለቀጣዩ አመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ (ካለንዳር) ሃሳብዎን ያካፍሉን። ይህ ፈጣን የዳሰሳ ጥናት ለ 2023-2024 የትምህርት ዘመን በተዘጋጁ የቀን መቁጠሪያ (ካለንዳር) ሁኔታዎች ላይ የማህበረሰቡን አስተያየት ለማወቅ ይረዳል። ማክሰኞ፥ ዲሰምበር 6 በትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ የሚቀርበውን የመጨረሻ ምክረሃሳብ ለማዘጋጀት ሠራተኞች የእርስዎን ግብረ መልስ ይጠቀማሉ። ሐሳብዎን እስከ ረቡዕ፣ ኖቨምበር 30 ያካፍሉን። የዳሰሳ ጥናቱን ሠነድ እዚህ ያግኙ

 2. remembranceየመታሰቢያ እና የእርቅ ወር ወርክሾፖች/አውደጥናቶች ይካሄዳሉ
  MCPS በዚህ ወር የአካባቢያዊ የነጻነት ቀን አከባበርን በመደገፍ እና ትምህርት ቤቶችን ከእድሜ ጋር የሚስማማ ትምህርት ስለ አካባቢው አፍሪካዊያን አሜሪካዊያን ማህበረሰቦች ታሪካዊ የመታሰቢያ እና የእርቅ ወር እያከበረ ነው። ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ቨርቹወል የለውጥ ማቀንቀን አውደ ጥናቶች በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ኖቬምበር 15-17 ይካሄዳሉ። በአውደ ጥናት ላይ ለመሳተፍ እዚህ ይመዝገቡ

 3. driverየአውቶቡስ ኦፕሬተር ይሁኑ - እንፈልግዎታለን!
  የትራንስፖርት ዲፓርትመንት የሠራተኛ ቅጥር ጽሕፈት ቤት ለአውቶብስ ኦፕሬተር የሥራ መደቦች አመልካቾችን ምልመላ ላይ ይገኛል። ይህ ለእርስዎ ወይም ለሚያውቁት ሰው ጥሩ ክፍያ፣ በርካታ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት እና በልጆች ህይወት ለውጥ ለማምጣት መልካም እድል ይሰጣል። እንዴት ማመልከት እንዳለብዎት

 4. ለስቴት ሻምፒዮና እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዊንተር ስፖርቶች ምዝገባ አሁንም ክፍት ነው።
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አትሌቲክስ ማክሰኞ፥ ኖቨምበር 15 ለሚጀመረው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዊንተር ወቅት በዝግጅት ላይ ነው። የዊንተር ምዝገባን በተመለከተ መረጃው MCPS አትሌቲክስ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛል። የስቴት ሻምፒዮናዎች ውድድር በዚህ ሳምንት መጨረሻ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎችን ለሚጫወቱ የሜዳ ሆኪ፣ ፉትቦል፣ የወንዶች እና የሴቶች እግር ኳስ እና የቮሊቦል ቡድኖች ቀጥሏል። በተጨማሪም፣ የአገር አቋራጭ ቡድኖች ቅዳሜ በሄሬፎርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Hereford High School) ለስቴት ሻምፒዮና ይሮጣሉ። የስቴት ሻምፒዮና ሴንትራል የጥሎ ማለፍ ጨዋታን ይከታተሉ።

ተከታታይ ማሳሰቢያዎች፦

 • ከባድ የአየር ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት ከ MCPS ጋር ግንኙነት ይኑርዎት
  ከባድ/መጥፎ የአየር ሁኔታ በሚኖርበት ጊዜ MCPS ስለ ተማሪዎች ትምህርት ቤት መዘጋት፣ስለ ት/ቤት ዘግይቶ መከፈት እና ተማሪዎች ከመደበኛው ሠዓት ቀደም ብለው  ስለሚሰናበቱበት ሁኔታዎችን ለማሳወቅ ብዙ መንገዶችን ይጠቀማል። ስለ አየር ሁኔታ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እና ከ MCPS ጋር እንዴት መገናኘት እንደሚችሉና የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ፦  ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools 




Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools