መታወቅ ያለባቸው 5 ጉዳዮች

MCPS
ሐሙስ፣ዲሴምበር 8

ስለ ፍሉ/ RSV መመሪያ፣ መጪውን የስራ ማስኬጃ በጀት እንዴት በቀጥታ ስርጭት እንደሚመለከቱ፣ ስለ አዲ የትምህርት ቦርድ አመራር እና ሌሎችንም መረጃዎች ያግኙ።


 1. BOE leadership

  calendar

  ቦርዱ የበለጠ ፕሮፌሽናል ቀናት እንዲኖሩ እና ትምህርት የሚቋረጥባቸው ጥቂት ቀናት ብቻ የሚሆኑበትን የትምህርት አመት ካለንደር አጽድቋል።
  የትምህርት ቦርድ የ2023-2024 የትምህርት አመት ካለንደር ዲሴምበር 6 የስራ ስብሰባ ላይ አጽድቋል። አዲሱ የቀን መቁጠሪያ የማስተማር ቀናትን መቋረጥ ከመገደብ አንፃር ለአስተማሪዎች ሙያዊ እድገት ላይ የበለጠ ትኩረት ይሰጣል።


 2. budget

  ሱፐርኢንተንደንቷ የሚያቀርቡትን የስራ ማስኬጃ በጀት ዲሴምበር 19 ይከታተሉ።
  ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒት ዲሴምበር 19 ቀን 2024 በባለድርሻ አካላት የተመከረበትን የስራ ማስኬጃ በጀት ላይ ገለጻ ይሰጣሉ። ዲስትሪክቱ በተማሪዎች አካዴሚያዊ ትኩረት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ እንዳቀደ ያዳምጡ እና ለቀጣዩ የትምህርት አመት አመራሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እና ግቦችን አስቀድመው ግንዛቤ ያግኙ። በሚከተሉት የመገናኛ ብዙሃን የቀጥታ ስርጭቱን መከታተል ይችላሉ፦ MCPS Homepage ወይም MCPS TV Channels (En Español Comcast 33, Verizon 35, RCN 88)


 3. BOE leadership

  ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዲስ የትምህርት ቦርድ አባላትን የተቀበለ ሲሆን አዲስ አመራሮችንም ሾሟል።
  አዲስ የተመረጡት አባላት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን (ዲስትሪክት 1)/ Grace Rivera-Oven (District 1)፣ ጁሊ ያንግ (ዲስትሪክት 3)/ Julie Yang (District 3)  እና በድጋሚ የተመረጡት አባላት ብሬንዳ ዎልፍ (ዲስትሪክት 5)/ Brenda Wolff (District 5) እና ካርላ ሲልቬስትሬ (አት-ላርጅ) ሐሙስ ታኅሣሥ 1 በካርቨር ሥነ ሥርዓት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል (ceremonially sworn in)። በሮክቪል ውስጥ የትምህርት አገልግሎቶች ማእከል። ወ/ሮ ሲልቬስትሬ (አት-ላርጅ)/Karla Silvestre (At-Large) ሲሆኑ፥ ሐሙስ፣ ዲሴምበር 1 በ “Carver Educational Services Center in Rockville” በተካሄደ ስነ-ስርአት ቃለመሃላ ፈጽመዋል። ሚስ ስልቨስትሬ (አት ላርጅ)/Ms. Silvestre (At-Large) እና ሼብራ ኢቫንስ (ዲስትሪክት 4)/Shebra Evans (District 4) እንደቅደም ተከተላቸው ቦርዱን በፕሬዚዳንትነት እና በምክትል ፕሬዝዳንትነት ይመራሉ።


 4. ፍሉ/ጉንፋን/RSV መመሪያ
  MCPS የአካባቢን በሽታ አዝማሚያዎችን በቅርበት ለመከታተል እና ለትምህርት ቤቶች እና የስራ ቦታዎች ድጋፍ ለመስጠት ከአካባቢው የጤና ዲፓርትመንት ጋር መስራቱን ቀጥሏል። የኮቪድ-19 ስርጭት እና ኢንፍሉዌንዛ በዲስትሪክታችን ጨምሯል። የመተንፈሻ አካላት ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ የሚረዱ የኢንፌክሽን እና የጤና አጠባበቅ ባህሪያትን ቁጥጥር አጠናክረን እንቀጥላለን። ከሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት (MDH) ስለ ኢንፍሉዌንዛ እና የመተንፈሻ አካል ቫይረስ (RSV) የመረጃ ገጾችን ይመልከቱ፦ influenza and Respiratory Syncytial Virus (RSV)


 5. first ladies

  መልካም ዜና ፈረንሳይ መሪ ባደረጉት ኦፊሴላዊ ጉብኝት ወቅት ተማሪዎች ከቀዳማዊት እመቤቶች ጂል ባይደን (Jill Biden) እና ብሪጊት ማክሮን (Brigitte Macron) ጋር ጊዜ አሳክፈዋክ
  ከ100 የሚበልጡ የሲልቨር ስፕሪንግ ኢንተርናሽናል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ቀዳማዊት እመቤት ብሪጊት ማክሮን በመንግስት ኦፊሴላዊ ጉብኝት ወቅት የመሳተፍ እድል ነበራቸው። ቀዳማዊት እመቤት ዶ/ር ጂል ባይደን የፈረንሳይ ኢመርሽን ፕሮግራም አካል የሆኑትን ተማሪዎች ለቀዳማዊት እመቤቶቹ ሰላምታ እንዲሰጡ፣ በግጥም ንባብ ላይ እንዲሳተፉ እና ከእነሱ ጋር በፕላኔት ዎርድ ሙዚየም ውስጥ በሚገኘው ቤተ መፃህፍት የመፅሃፍት ቤተመዘክር ላይ እንዲሳተፉ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.ጋብዘዋቸዋል።

ወቅታዊ ዘገባዎችን እና መረጃዎችን ለማግኘት MCPS News Center ይጎብኙ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public SchoolsEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools