ወደ 2022-2023 የትምህርት ዘመን/አመት እንኳን በሰላም ተመለሳችሁ

ለ 2022-2023 የትምህርት ዓመት እንኳን ደህና መጣችሁ! ሰኞ ነሐሴ 29 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወደ 160,000 ለሚጠጉ ተማሪዎች በሮቹን ይከፍታል። ለአስተማሪዎቻችን፣ ለሠራተኞቻችን እና ለአስተዳዳሪዎች ይህ ለወራት ስንጠብቅ የነበረና እና በሠመር ወቅት በሙሉ ስንዘጋጅበት የነበረ ቀን ነው። ተማሪዎቻችንን ወደ ልዩ የሆነው አዲስ የትምህርት አመት እና ወደሚወክለው አቅም ስንጋብዝ በታላቅ ደስታ ነው። በዚህ ቪድዮ ላይ፣ ለ 2022-2023 የትምህርት አመት ያለንን መነሳሳት እና የዚህ አመት ጭብጥ/ዋና ሀሳብ "ሁሉም አሁን አንድ ላይ ነው፣ ሁሉም ደግሞ ለተማሪዎቻችን ነው" እንጋራለን። እንዲሁም የMCPS ሰራተኞቻችን ለዚህ አዲስ የትምህርት አመት እኛን ለማዘጋጀት የሰሩት ታላቅ ስራ ላይ ምልከታ እናደርጋለን። እነሱ ናቸው ለተማሪዎቻችን ይሄንን እውን ያደረጉት! ዝግጁ ነን። እንኳን በደህና ተመልሳችሁ መጣችሁ!

Dr. Monifa B. McKnight
Superintendent, Montgomery County Public Schools

Brenda Wolff
President, Montgomery County Board of Education