እንግሊዝኛ/English / ስፓንሽኛ/Español / 中文 / ፈረንሳይኛ/Français / ፖርቹጋልኛ/Português / 한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt / አማርኛ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አመራር ይሰጣል እና ክትትል ያደርጋል። የዚህ ሳምንት የትምህርት ቦርድ ዘገባ የበጀት ማስተካከያዎችን እንዴት እያቀድን እንዳለን እና በሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ ላይ ባለው ወቅታዊ መረጃ ላይ ያተኩራል።
ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
ቦርዱ ለ 2024 ተመራቂዎች እና ከእነሱ ጋር ለሚያከብሩ ሁሉ ልባዊ የእንኳን ደስ አላችሁ መልክት ያስተላልፋል! ተመራቂዎቹ ላደረጉት ትጋት እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋና ይግባቸውና እያንዳንዳቸው የአዲስ ጉዞ ምዕራፍ ለመጀመር ተዘጋጅቷል። የትምህርት ቦርድ ቀጣይ የምረቃ ሥነ ስርአቶችንም በጉጉት ይጠብቃል።
ስለ በጀት ማስተካከያዎች እቅድ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከካውንቲው ካውንስል የተፈቀደውን የበጀት ድልድል ለማሟላት ከቀደምት የበጀት ጥያቄያችን ላይ ማስተካከያ ለማድረግ በትጋት እየሰራን ነው። ባለፈው ሳምንት፣ማስተካከያ ስለሚደረግባቸው ሁኔታዎች ዝርዝር አጋርተናል። በዚህ ሂደት ውስጥ በምንሰራበት ጊዜ፣እባክዎ የሚሰጡት አስተያየቶች ተሰሚነት እና ዋጋ እንዳላቸው ይገንዘቡ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ MCPS FY 2025 በጀት ጁን 11 በሚደረገው የቦርድ ስብሰባ ላይ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።
ስለ ት/ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ
ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት፣ የሜሪላንድ ስቴት የካውንቲ ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ምደባ እስከ ጁላይ 1 ድረስ መጠናቀቅ እንዳለበት ይደነግጋል። አሁን ወደ ጁን የተጠጋን ስለሆነ፣ ቀጣይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ በሂደት ላይ ነው ወይ ብላችሁ ታስቡ ይሆናል።
በሒደት ላይ መሆኑን ቦርዱ በደስታ ይገልጻል። ብቁ የሆኑ በርካታ አመልካቾች ቃለ መጠይቅ እየተደረገላቸው ነው። ከቃለ መጠይቆቹ በተጨማሪ ቦርዱ የሙያዊ ማስረጃዎችን፣ የበፊት ታሪኮቻቸውን መፈተሽ/ማጣራት እና ሌሎችም አስፈላጊ መረጃዎችን ይገመግማል።
እንዲህ አይነቱ አስፈላጊ ውሳኔ በጥንቃቄ መደረግ አለበት። ስለዚህ፣ ከጁላይ 1 ቀነ ገደብ በላይ ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ጊዜያዊ ሱፐርኢንተንደንት ይሰየማል።
የፍለጋውን ሁኔታ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ቦርዱ በቅርቡ ያሳውቃል። የሂደቱ ወሳኝ ደረጃ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት ህብረተሰቡ ታጋሽነቱን እንዲቀጥል እና የእጩዎችን የግላዊነት መብት እንዲያከብር እንጠይቃለን።
የተሳትፎ እድሎች
ህብረተሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።
ቀጣይ ስብሰባዎች
አጀንዳዎችን ለማየት እና የቀጥታ ስርጭት ለመከታተል ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ።
ግንኙነትዎ ይቀጥል
ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org