እንግሊዝኛ/English / ስፓንሽኛ/Español / 中文 / ፈረንሳይኛ/Français / ፖርቹጋልኛ/Português / 한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የ (MCPS) ተመራቂ የሆኑት ዶ/ር ቶማስ ቴይለር (Dr. Thomas Taylor)፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ሱፐርኢንተንደንት እንዲሆኑ እንደሚሾማቸው አስታውቋል። ቦርዱ ስለ ዶ/ር ቴለር ሹመት ጁን 25 በሚደረገው መደበኛ ስብሰባ ላይ ድምጽ ይሰጣል።
ዶ/ር ቴለር በዲስትሪክት ደረጃ ከ 12 ዓመታት በላይ በአመራር፣ እና 6 ዓመታት በሱፐርኢንተንደንትነት፣በጠቅላላ ከ 25 ዓመታት በላይ በትምህርት ባለሙያነት የማገልገል ልምድ አላቸው። እርሳቸው በአሁኑ ጊዜ በቨርጂኒያ የስታፎርድ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ሱፐርኢንተንደንት በመሆናቸው ጠንካራ የትምህርት ባለሙያ እና የመሪነት ስኬት ታሪክ አላቸው። ዶ/ር ቴለር በስታፍፎርድ ካውንቲ ባከናወኑት ተማሪዎች ላይ ያተኮረ ተግባር 2024 የቨርጂኒያ ሪጅን III የአመቱ ምርጥ ሱፐርኢንቴንደንት በመባል ተሰይመዋል።
“ዶ/ር ቴለር ልዩ የትምህርት ባለሙያ እና መሪ ናቸው” ሲሉ የቦርዱ ፕሬዝዳንት ካርላ ሲልቬስትሬ ገልፀዋቸዋል። "እንደ ትምህርት ባለሙያ እና መሪ ባካበቱት ልምድ እኛን ወደፊት ሊመሩን እንደሚችሉ ቦርዱ ይተማመንባቸዋል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ዶክተር ቴለር ከመሰየማቸው በፊት ከማህበረሰቡ ጋር ስናስተዋውቅ ደስታ ይሰማናል።
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org