እንግሊዝኛ/English / ስፓንሽኛ/español / 中文 / ፈረንሳይኛ/français / ፖርቹጋልኛ/Português / 한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt / አማርኛ
ውድ ወላጆች
አዲስ የትምህርት አመት ስንጀምር፣ የልጆቻችሁን የወደፊት ትምህርት እና የህይወት ስኬት በመቅረጽ ረገድ የተማሪዎች በትምህርት ላይ መገኘት ያለውን ትልቅ ጠቀሜታ አጉልተን ማሳየት እንፈልጋለን። አብረን ትምህርት ቤት ስንሆን፣ አብረን ስንማር እና አብረን ስናሳካ፣ አስገራሚ ነገሮች ይከሰታሉ።
በትምህርት ላይ የመገኘት የድርጊት መርሃ ግብር ዓላማው፥ አሁን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ እና ሁሉም በአንድ ላይ፣ በትምህርት ቤት አብረው፣ ሲማሩ አብረው፣ ሲያሳኩ አብረው፡ሲሆኑ ስር የሰደደ ከትምህርት መቅረትን ለማስወገድ እና ለተማሪዎች ስኬት ምክንያት ይሆናል። እቅዱ በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ሥር የሰደደ ከትምህርት መቅረትን ለመቅረፍ ዘርፈ ብዙ አካሄድ አለው።
በመጀመሪያ፣ በመደበኛነት ከትምህርት ቤት መቅረት የሚያስከትለውን ውጤት አስቡበት። በዚህ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በትምህርት ቤት አለመገኘትን በተመለከተ አንዳንድ አሳሳቢ ስታቲስቲክስ እዚህ ያገኛሉ። እነዚህ ቁጥሮች በመደበኛነት ትምህርት ቤት መከታተልን ለማረጋገጥ እና ከትምህርት ቤት መቅረት በልጆቻችን ትምህርት ላይ ያለውን ተጽእኖ ለማስወገድ የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች ያንፀባርቃሉ፡
በዩ.ኤስ. የትምህርት ዲፓርትመንት፣ 2019-2020 የትምህርት አመት ወደ 6.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች ሥር የሰደደ/በተደጋጋሚ ሁኔታ ከት/ቤት እንደቀሩ ይገመታል።
ት/ቤት መገኘትን የሚከታተለው ድርጅት እንደዘገበው በመዋለ ህፃናት እና አንደኛ ክፍል ስር የሰደደ መቅረት የሚያበዙ ተማሪዎች በሶስተኛ ክፍል በብቃት የማንበብ ችሎታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው።
በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ሥር የሰደደ መቅረት ያለባቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፣ ይህም የወደፊት እድላቸውን ውስን ከማድረጉም በላይ የገቢ አቅማቸውን ይቀንሳል።
ከትምህርት ቤት መቅረት የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከአካደሚክ ስኬትም በላይ ነው። የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከላት (CDC) ከትምህርት ቤት የሚቀሩ ተማሪዎች ተገቢ ላልሆኑ አሉታዊ ማህበራዊ እና ስሜታዊ ውጤቶች የበለጠ ተጋላጭ መሆናቸውን በጉልህ ያሳያል፣ ይህም በአደገኛ ባህሪያትን መለማመድ እና በትምህርት ቤት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፎ መቀነስን ይጨምራል።
በሜሪላንድ፣ በአንድ የትምህርት ዓመት 18 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ከትምህርት መቅረት ሥር የሰደደ ከትምህርት ቤት መቅረት ተብሎ ይገለጻል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከወረርሽኙ ጥቂት ቀደም ብሎ እና ወዲያውኑ ከወረርሽኙ በኋላ መረጃው ምን እንደሚመስል እነሆ።
2018-2019 የትምህርት ዓመት – 30,349 ተማሪዎች በተደጋጋሚ/ለረጅም ጊዜ በትምህርት ቤት አልተገኙም (19.55%)
2022-2023 የትምህርት ዓመት – 42,863 ተማሪዎች በተደጋጋሚ/ለረጅም ጊዜ ትምህርት ቤት አልተገኙም (27%)
እነዚህ አኃዛዊ መረጃዎች ትምህርት ቤት በመደበኛነት ለመከታተል ቅድሚያ የመስጠት አስፈላጊነትን ያስታውሰናል።
የተማሪዎች በትምህርት ቤት መገኘት ወሳኝ ሚና የሚኖረው ለምን እንደሆነ እነሆ፦
አብረው በትምህርት ቤት ውስጥ፡
ትምህርት ቤት በመደበኛነት መገኘት ልጆቻችን በትምህርቶቻቸው በንቃት መሳተፋቸውን እና ከእኩዮቻቸው እና ከአስተማሪዎች ጋር መገናኘታቸውን ያረጋግጣል። ተማሪዎች ትምህርት ቤት በአካል በመገኘት፣ ልጆቻችን ጠቃሚ ግብአቶችን፣ መገልገያዎችን እና የአእምሮ መጎልመስ እና እድገትን የሚያበረታታ የተመቻቸ የመማሪያ አካባቢ ማግኘት ይችላሉ።
አብሮ መማር፡
ትምህርት ቤት አዘውትሮ መገኘት ልጆች ወጥ የሆነ ትምህርት እንዲያገኙ፣ ሥርዓተ ትምህርቱን በብቃት እንዲከታተሉ እና በአካዳሚክ ግስጋሴ እንዲቀጥሉ ያስችላቸዋል። የክፍል ውስጥ መስተጋብር እና ውይይቶች ልጆች ሃሳቦችን እንዲለዋወጡ፣ አስተሳሰባቸውን እንዲፈታተኑ እና ስለሚማሯቸው ጉዳዮች ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
አብረው ማሳካት፦
ጥሩ የትምህርት ቤት መከታተል እና በአካዳሚክ አፈፃፀም መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን ጥናቶች ያሳያሉ። ተማሪዎች በመደበኛነት ትምህርት ቤት ሲማሩ/ሲከታተሉ፣ በአካዳሚክ ስኬታማ ለመሆን እና ሙሉ አቅማቸውን ለማሳካት ብዙ እድሎች አሏቸው። በክፍል እንቅስቃሴዎች እና ፕሮጀክቶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረኝ፣ ትብብርን፣ ሂሳዊ አስተሳሰብን፣ እና ችግርን የመፍታት ክህሎቶችን ያበረታታል። እነዚህ ሁሉም ለወደፊቱ ስኬታቸው አስፈላጊ ናቸው።
አሁን ሁላችንም አንድ ላይ፣ ለልጆቻችን የትምህርት ጉዞ አጋዥ እና ምቹ አካባቢ ለመፍጠር አብረን እንስራ። በህመም ወይም በሌሎች እውነተኛ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት መቅረትን ማስወገድ የማይቻልባቸው ሁኔታዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ እንረዳለን። እንደዚህ ያሉ አጋጣሚዎች ሲከሰቱ በልጅዎ ትምህርት ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ተጽእኖ ለመቀነስ፣ ከትምህርት ቤቱ ጋር እንዲገናኙ፣ አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና ከመምህራን ጋር እንዲተባበሩ እናበረታታዎታለን።
በትምህርት ቤት የመገኘት እና የትብብር ባህል ለማዳበር ስለሚያደርጉት ወሳኝ ድጋፍ እናመሰግናለን። አንድ ላይ ሆነን በጋራ፣ ልጆቻችን በትምህርት እንዲበለጽጉ፣ ማህበራዊ እድገት እንዲያገኙ እና ህልማቸውን እንዲያሳኩ እናበረታታለን። ደስታ እና እድል የተሞላበት ጥሩ የትምህርት አመት የሚሆነው ተማሪዎቻችን በየቀኑ ትምህርት ቤት ሲሆኑ ነው።
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)
MCPS ትምህርት ቤት የመገኘት የድርጊት መርሃ ግብር አንብቡ።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org