እንግሊዝኛ/English / ስፓንሽኛ/Español / 中文 / ፈረንሳይኛ/Français / ፖርቹጋልኛ/Português / 한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt / አማርኛ
ጁን 12, 2024
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጁን 11 የበጀት አመት 2025 የስራ ማስኬጃ በጀት ማፅደቁን ተከትሎ ለቀጣዩ የትምህርት አመት በበርካታ ክፍሎች የክፍል መጠን በአንድ ተማሪ ይጨምራል። ይህ ውሳኔ፣ ተስማሚ ባይሆንም፣ ከተጠየቀው የባጀት ድጋፍ እስከ $30 ሚሊዮን ዶላር በመቀነሱ ምክንያት ይህን ርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኗል። በጡረታ እና በስራ መልቀቂያ ምክንያት የመምህራን ክፍት የስራ መደቦች ስላሉ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ክሱልስ (MCPS) በሥራ ላይ የሚገኝ/የምትገኝ ማንኛውም መምህር(ት) በመጪው የትምህርት አመት የሥራ መደባቸው ላይቀነስ ይችላል።
የሚከተሉት ሠንጠረዦች ስለ 2023–2024 እና 2024–2025 መደበኛ የትምህርት ክፍል መጠን መመሪያ ያመለክታሉ። እያንዳንዳቸው ትምህርት ቤቶች ዋናዎቹን ፕሮግራሞቻቸውን በሚወስኑበት ጊዜ፣ የትኞቹ መማሪያ ክፍሎች በአንድ ተማሪ እንደሚጨምሩ እና የትኞቹ ክፍሎች መጨመር እንደሌለባቸው የት/ቤት መሪዎች አስፈላጊ ውሳኔዎችን ያደርጋሉ።
አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች |
መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች |
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች |
||||||||||||||||
|
ለሌሎች ኮርሶች የመማሪያ ክፍል መጠን በመመሪያው መሠረት 32 ነው። |
ለሌሎች ኮርሶች የክፍል መጠን መመሪያው 32 ነው። |
አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች |
መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች |
ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች |
||||||||||||||||
|
ለሌሎች ኮርሶች የክፍል መጠን መመሪያው 33 ነው። |
ለሌሎች ኮርሶች የክፍል መጠን መመሪያው 33 ነው። |
ተማሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የተወሳሰቡ የአካዳሚክ እና የአዕምሮ ጤና ፍላጎቶች ስለሚኖራቸው፣ የትኛውም የክፍል መጠን መጨመር ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል። የት/ቤቶች እና የሴንትራል አገልግሎቶች መሪዎች በተማሪዎች እና በሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ተፅእኖ ለመቀነስ ዋና መርሃ ግብሮች ሲከለሱ አብረው ይሰራሉ። ወላጆች እና ተንከባካቢዎች የልጆቻቸውን ግለሰባዊ አካዴሚያዊ ግስጋሴ እንዲከታተሉ በቤተሰቦች እና በትምህርት ቤቶች መካከል፣ ከግለሰብ አስተማሪዎች ጭምር መስተጋብር ይኖራል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አማካኝ የመማሪያ ክፍል መጠን በብሔራዊ ደረጃ ካሉት ውስጥ ናቸው፤ እንዲሁም በሜሪላንድ ውስጥ ብዙ ተመሳሳይ መጠን ያላቸው የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ከ MCPS የበለጠ አማካይ የመማሪያ ክፍል መጠን አላቸው። በሜሪላንድ ተመሳሳይ መጠን ካላቸው የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች የተገኘ መረጃ በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የክፍል መጠን ሪፖርት 2023 የተዘጋጀ ይመልከቱ።
M. Brian Hull, Chief Operating Officer Montgomery County Public Schools
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org