መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሀሙስ ኖቨምበር 9 2023

1. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) 2ኛ ምዕራፍ/Phase Two የትምህርት አመት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ለማዳበር አስተያየትዎን ያካፍሉን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) የ2024–2025 የትምህርት ዘመን ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር በማዘጋጀት ላይ ስለሆነ፥ ዲስትሪክቱ በሁለት ረቂቅ የቀን መቁጠሪያዎች ላይ ተጨማሪ ግብረመልስ ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች፣ ከቤተሰቦች እና ከማህበረሰብ አባላት አስተያየቶችን መስማት ይፈልጋል። ይህ ግብረመልስ፣ የዳሰሳ ጥናት #2፣ የዲስትሪክቱን ትምህርታዊ ፍላጎቶች እና የአፈጻፀም ሁኔታዎችን በማራመድ ረገድ ለማበልፀግ ስለሚጠቅም ሁለተኛውን ምዕራፍ ይወክላል (MCPS ፖሊሲ IDA፣ የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያ)። 

ቀን መቁጠሪያ ቅኝት:
English  /  Español  /  中文  /  Français /  Português /  한국어 /  Tiếng Việt  /  አማርኛ


2. በትምህርት ላይ መገኘትና መከታተል ወሳኝ ነው፡ የአንደኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት ካርዶች እና ከትምህርት ገበታ መቅረት

ወላጆች/ተንከባካቢዎች በቅርቡ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሪፖርት ካርዶችን ያገኛሉ። የአካዳሚክ እድገትን ከመመልከት በተጨማሪ፣ እባክዎን ተማሪዎ በመጀመሪያው ሩብ አመት ከትምህርት ቤት የቀረ(ች)ባቸውን ቀናት ብዛት ያስታውሱ። 

አንድ ተማሪ ለትምህርት ከተመዘገበባቸው ቀናት 10 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ (በመጀመሪያው ሩብ አመት 5 ቀናት) በትምህርት ላይ ካልተገኘ(ች) ለረጅም ጊዜ ከት/ቤት እንደቀረ(ች) ይቆጠራል። እባክዎን በየቀኑ ልጅዎን(ልጆችዎን/ልጆቻችሁን) ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ጥረት ያድርጉ። ልጅዎን (ልጆችን) ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ምንም አይነት መሰናክሎች ካሉ፣ በትምህርት ቤትዎ ውስጥ የፈለጉትን ሰራተኛ ያነጋግሩ። እዚያ ያሉት ለመርዳት ነው።


3.ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን! ኖቬምበር 14 በሚካሄደው የስራ ማስኬጃ በጀት የውይይት መድረክ የቦርድ አባል ጁሊ ያንግን ይቀላቀሉ።

የእርስዎ ድምጽ አስፈላጊ ነው፤ እናም የእርስዎን ግንዛቤ ለመስማት እንፈልጋለን! በቀጣዩ ቨርቹዋል የሥራ ማስኬጃ ባጀት የውይይት መድረክ ይቀላቀሉን። የቦርድ አባል ጁሊ ያንግ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አመራር ባቀረበልዎት የትብብር ተነሳሽነት ጥሪ ይሳተፉ።

RSVP/ይመዝገቡ እንደሚገኙ ያሳውቁን። 


4. ዝግጅቶች እና ልዩ ልዩ እድሎች 

ኖቬምበር 13 እና 15 ለተለማማጅነት ፕሮግራም ያሉትን እድሎች ይወቁ

ሰኞ፥ ኖቬምበር 13 ከቀኑ 1-4pm ተማሪዎችን እንዴት መቅጠር እንደሚችሉ ማወቅ ለሚፈልጉ አሰሪዎች የመረጃ ክፍለ ጊዜ ይኖራል። እሮብ፥ ኖቬምበር 15 ከ10 a.m. እስከ እኩለ ቀን ድረስ ከማንኛውም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጁንየሮች እና ሲንየሮች የተለማማጅነት ስራ አውደርእይ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይበልጥ ያንብቡ 

ፎል የቲያትር ፕሮዳክሽን በመካሄድ ላይ ነው

በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የፎል ወቅት የቲያትር ዝግጅቶች መጋረጃ እየተከፈተ ነው። እስከ 2024 መጀመሪያ ድረስ የሚካሄዱትን ምርጥ ትርኢቶች ለማየት አሁኑኑ ያቅዱ። ይበልጥ ያንብቡ

የሽልማት መስጫ ወቅት በመካሄድ ላይ ስለሆነ ዛሬውኑ እጩዎችን ይጠቁሙ! 

በትምህርት ቤትዎ እውቅና ሊሰጠው/ሊሰጣት የሚገባ   ልዩ የሆነ(ች) ሰራተኛ፣ አስተዳዳሪ ወይም አስተማሪ አለ(ች)? ሰራተኞችን፣ መምህራንን እና አስተዳዳሪዎችን ለማክበርና ለበርካታ ሽልማቶች እጩዎችን ለመጠቆም ክፍት ነው። 


ብሩህ ቦታዎች 

የላቀ ምደባ (AP) የትምህርት ቤት ኦነር ሮል ለ18 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የላቀ የትምህርት ስኬት እውቅና ተሰጥቷል

አሥራ ስምንት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በታዋቂው 2023 AP ት/ቤት የክብር እውቅና አግኝተዋል። ይህ ስኬት ዲስትሪክቱ ልዩ የትምህርት እድሎችን ለመስጠት እና ተማሪዎችን ለኮሌጅ፣ ለስራ እና ለማህበረሰብ አገልግሎት ለማዘጋጀት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ይበልጥ ያንብቡ. 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መምህራን ከሜሪላንድ የጤና እና የአካል ብቃት አስተማሪዎች ማህበር/Society of Health and Physical Educators Maryland (SHAPE MD) የሚሰጠውን ከፍተኛ ሽልማት አሸንፈዋል። ለጤና ትምህርት፣ ለአካላዊ ትምህርት (P.E.) እና/ወይም ለተማሪዎች ደህንነት ላበረከቱት ስራ እና አስተዋጾ እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ

በእያንዳንዱ ሩብ አመት፣ ዊትስተን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Whetstone Elementary School ቀይ ምንጣፍ በመዘርጋት የት/ቤቱን Wildcat ዋና እሴቶች ያሳዩ ተማሪዎችን ክብር/እውቅና ይሰጣቸዋል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)