መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ፌብርዋሪ 8/2024

1. የትምህርት ቦርድ ዶ/ር ሞኒክ ፌልደርን የትምህርት ቤቶች ጊዜያዊ ሱፐርኢንተንደንት አድርጎ ሾመ 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 6 ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ዶ/ር ሞኒክ ፌልደርን ጊዜያዊ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት አድርጎ ሾሟል።

ዶ/ር ፌልደር በሰሜን ካሮላይና የኦሬንጅ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት በመሆን የዓመቱ የስቴቱ ምርጥ ሱፐርኢንተንደንት በመሆን የተሾሙበትን ጨምሮ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች 32 ዓመታት ልምድ አካብተዋል። ይበልጥ ያንብቡ 


2. የሁለተኛ ሩብ አመት የሪፖርት ካርዶች PreentVUE ላይ ይገኛሉ

የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ II የሪፖርት ካርዶች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለተማሪዎች ተሰራጭተዋል፣ አሁን ParentVue ላይ ያገኛሉ። የሪፖርት ካርዶች ከትምህርት ቤቶች ተሰራጭተው ከልጅዎ ጋር ወደ ቤት ተልከዋል። የሪፖርት ካርዱን ቅጂ ካልደረሰዎት፣ ParentVUE ላይ መመልከት/ማውረድ ይችላሉ። ስለ ParentVue መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ እዚህ ጠቅ ያድርጉ። 

ParentVue guide: EnglishEspañol  / 中文  / Français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ  


3. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና ሪሶርሶች 

ስለ ኮሌጅ የገንዘብ ድጋፍ የበለጠ ይወቁ

ለዩኒቨርሲቲ ትምህርትህ(ሽ) የገንዘብ ድጋፍ ስለማግኘት ሂደት ጥያቄ አለህ(ሽ)? ለኮሌጅ ትምህርት የገንዘብ ዕርዳታ ስለማግኘት እድሎች የበለጠ ማወቅ የምትፈልግ(ጊ) ሰነድ አልባ ተማሪ ነህ(ሽ)? የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ስለ ፋይናንሻል ዕርዳታ ሂደቱ የበለጠ ለማሳወቅ ከ MCPS ጋር በመተባበር ቨርቹዋል ወርክሾፕ ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 15 6 p.m. ያካሂዳል። ቨርቹዋል ክፍለ ጊዜው የሚካሄደው በስፓኒሽኛ ይሆናል። ይመዝገቡ/RSVP 

የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምን በሚመለከት የቤተሰብ ውይይት መድረክ/ፎረም ፌብሩዋሪ 24 ይካሄዳል 

ጠንካራ የአእምሮ ጤናን ስለመጠበቅ እና የአደንዛዥ እፅ አጠቃቀምን ለመከላከል የቤተሰብ ውይይት መድረክ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 24 በስፕሪንግብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስለሚካሄድ PTSA ይቀላቀሉ። ተሳታፊዎች ስለ fentanyl፣ አልኮል፣ እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች አደገኛነት ይማራሉ። የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ መረጃ፣ ትምህርት ቤት እና ማህበረሰብን መሰረት ባደረገ የዕፅ ሱሰኝነት መከላከል፣ የጉዳት ቅነሳ ህክምና ውጥኖችን ለመከወን ምን የመድን ሽፋን እንደሚያስፈልግ ውይይት ያደርጋሉ። ይመዝገቡ/RSVP

MCPS ማርች 9 የልጃገረዶች ጉባኤ ያስተናግዳል

ቅዳሜ፣ማርች 9 በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ልጆች ስብሰባ ስለሚካሄድ ይቀላቀሉን። ይህ ዝግጅት 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃ ሰጭ አውደ ጥናቶችን ያካሄዳል። ይበልጥ ያንብቡ

ይመዝገቡ/RSVP

ሠመር ራይዝ 2024 የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል

ምዝገባ፡ ተማሪዎች "Summer RISE 2024" አካል በመሆን እንዲሳተፉ ምዝገባው ተጀምሯል። Summer RISE ለመጀመሪያ አመት እና ለመጨረሻ አመት ተማሪዎች ተግባራዊ፣ በሙያ ላይ የሚያተኩሩ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል፤ ይኼውም አሰሪዎች ዝንባሌ ያላቸውን በመለየት በስልጠና እንዲያዳብሩ ይረዳል። ምዝገባው ፌብሩዋሪ 27 ይዘጋል። የበለጠ ለመረዳት እዚህ ያንብቡ

ጠቃሚ የዲስትሪክትአቀፍ ዳሰሳ ጥናት በቅርቡ ይመጣል፡ 

MCPS ትምህርትን ለማሻሻል እና ትምህርት ቤቶቻችን እና ዲስትሪክታችን ለሁሉም ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች የበለጠ ምቹ ቦታ ለማድረግ እየሰራ በመሆኑ የእርስዎን እገዛ/አስተዋጽኦ/እርዳታ እንፈልጋለን። የዳሰሳ ጥናቱ ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 12  ስለ ት/ቤቶች ዲስትሪክት የእርስዎን አስተያየት የሚጠይቅ ይሆናል። ሁሉም ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች እንዲሳተፉ እናበረታታለን። ዳሰሳው ከፌብሩዋሪ 12 እስከ ማርች 15 ድረስ ክፍት ይሆናል።


4. ለ 9ኛ ክፍል ተማሪዎች የኮርስ ማጠናቀቂያ ፈተና ማሳሰቢያ 

የሜሪላንድ አጠቃላይ ምዘና ፕሮግራም (MCAP) የኮርስ ማጠናቀቂያ (EOC) የሳይንስ እና የስነመንግስት ፈተናዎች፥ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች (2027 ተመራቂዎች) በሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው የባዮሎጂ እና የስነመንግስት ኮርሶች (NSL) የመጨረሻ ክፍለጊዜ ውጤት 20 በመቶ ይቆጠራል።) ይህ የሆነበት ምክንያት በሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት በተሰጡ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመመረቂያ መስፈርቶች ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት ነው። ይበልጥ ያንብቡ


5. በዚህ ሳምንት የ MCPS ዘገባ  

የቶማስ S. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚያስደንቅ ሁኔታ ተሰጥኦ ያላቸው የሁሉም ጾታ የካፔላ ቡድን፣ The Acatonics፣ በኒውዮርክ የሲንግስትሮንግ/SingStrong ውድድር ስላሸነፈ እንኳን ደስ አላችሁ! 

WUSA 9 Feature 

የፌብሩዋሪ ዋና ዋና ዘገባዎች፡ 

ፌብሩዋሪ የቴክኒክ ሙያ ትምህርት ወር ነው

MCPS   የእኛ የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት ፕሮግራሞች ለተማሪዎች የሚሰጡትን አስደሳች እድሎችን በጉልህ ያሳያል። የበለጠ ለማወቅ CTE ድረገጽ ይጎብኙ። 

ብሄራዊ ትምህርት ቤት ካውንስሊንግ እውቅና የሚሰጥበት ሣምንት 

በብሔራዊ ትምህርት ቤት ካውንስሊንግ ሳምንት ውስጥ ተማሪዎችን እና ወላጆችን የሚያገለግሉትን ድንቅ ካውንስለሮች ሁሉ ለማመስገን MCPS ን ይቀላቀሉ። የዚህ አመቱ መሪ ሃሳብ/ጭብጥ "የትምህርት ቤት ካውንስሊንግ፡ ደረጃዎችን መሰረት ያደረገ፣ ተማሪዎች ላይ ያተኮረ" ሲሆን የማህበረሰብን ትኩረት ልዩ ልዩ የትምህርት ቤት ባለሙያ ካውንስለሮች ተማሪዎችን በመርዳት ላይ ያነጣጠረ ነው።

ስለ ጥቁሮች ታሪክ   የሚከበርበት ወር

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል በቅርቡ የሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ኬኔት ስሚዝን በቤቴስዳ-ቼቪ ቼዝ እና በሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስለ ሂፕ ሆፕ ታሪክ እና ባህል ማህበራዊ ጥናቶች ኮርስ በማዳበር እና በማስተማር እውቅና ሰጥቷል። 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ቺፍ ማርከስ ጆንስ በፌርላንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጥቁሮች ታሪክ ወር እውቅና በሚሰጥበት ወቅት ተጋባዥ እንግዳ ተናጋሪ ነበሩ። 

ከ 25 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተውጣጡ ቡድኖች በሞንትጎመሪ ብሌየር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 27ኛው አመታዊ የፖምፖነስ ውድድር በደስታ ተሳታፊዎች በመሆን አሳልፈዋል። የፎተግራፍ ክምችቱን/ጋለሪውን ይመልከቱ። 

የጨረቃ አዲስ አመት/Lunar New Year እራት ግብዣ ላይ በሺዎች የሚቆጠር የተማሪዎች ስኮላርሺፕ ተገኝቷል

በዚህ አመት የጨረቃ አዲስ አመት/Lunar New Year የስኮላርሺፕ እራት ግብዣ ወቅት በሆንግ ኮንግ ፒርል "Seafood" ምግብ ቤት $16,000 ዶላር በላይ ተሰብስቧል። በኤዥያውያን አሜሪካውያን ፕሮግረስ (LEAAP) የመምህራን ሊግ የተካሄደው የእራት ግብዣ የዲግሪ ትምህርት መከታተል ለሚፈልጉ የኤዥያ ፓስፊክ አሜሪካውያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች የስኮላርሺፕ ገንዘብ ማሰባሰብያ የተዘጋጀ ነው። ተጨማሪ ፎቶዎች



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)