1. ኤፕሪል 22 ስለሚሰጠው ትምህርት አስፈላጊ የሆነ መረጃ
ሰኞ፣ ኤፕሪል 22 አሁን በዲጂታል የሚተላለፍ የትምህርት ቀን ነውይኼውም ተማሪዎች ያመለጣቸውን ትምህርት ማካካሻ ቀን ይሆናል። ተማሪዎች ራሳቸውን ችለው እንዲያጠናቅቁ ከተመደበላቸው የቤት ሥራ ጋር ወደ ቤታቸው ይላካሉ።
ዲጅታል በይነመረብ ላይ የሚሰጥ ትምህርት አስተማሪዎች በቀጥታ የሚሰጡት ትምህርት ሳይሆን ወይም ቴክኖሎጂን ሳይጠቀሙ ተማሪዎችን በመማር ላይ የሚያሳትፉ ትምህርታዊ እንቅስቃሴዎችን እና የተመደበላቸውን የትምህርት የቤት ስራዎችን ይገልጻል። ተማሪዎች በእለቱ በትምህርት ላይ መገኘታቸውን ለማረጋገጥ የተመደበላቸውን የቤት ስራዎች ማጠናቀቅ አለባቸው። ማናቸውም አዳጋች ወይም ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ቢከሰቱ ለተማሪዎች የተሰጣቸውን የትምህርት ቤት ሥራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጣቸዋል። ተጨማሪ ኣንብቡ.
2. የቅድመ መዋእለ ሕጻናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ ማርች 1 ይከፈታል።
ለ 2024-2025 የትምህርት አመት የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት እና የሄድ ስታርት ምዝገባ አርብ፣ ማርች 1 ይጀምራል። ልጆች በሴፕቴምበር 1, 2024 ወይም ከዚያ በፊት 4 አመት እድሜ የሚሞሉ መሆን አለባቸው፣ እንዲሁም ቤተሰቦች ለማመልከት በገቢ አቅም ረገድ ብቁ መሆን አለባቸው። ቤተሰቦች ልጆቻቸውን በኦንላይን ወይም በአካል ተገኝተው ማስመዝገብ ይችላሉ።
ልጅዎ በሴፕቴምበር 1, 2023 ላይ ወይም ከዚያ በፊት 4 አመት ከሆነ(ች)፣ በዚህ የትምህርት አመት ለቀሪው የቅድመ መዋዕለ-ህፃናት/ሄድ ስታርት ማስመዝገብ ይችላሉ።
እንዴት ማስመዝገብ እንደሚቻል ለማወቅ እዚህ ጠቅ/ይጫኑ።
ስለ ብቁነት መመሪያ፣ ስለ አስፈላጊ ሰነዶች፣ ወይም በኦንላይን እንዴት ማስመዝገብ እንደሚችሉ ለበለጠ መረጃ፣ በስልክ ቁጥር 240-740-4530 ይደውሉ፤ ወይም MCPS ድረ ገጽ ይጎብኙ።
3. የዳሰሳ ጥናት ተከፍቷል—እንዴት እየሰራን እንዳለን እንዲያሳውቁን እና ትምህርት ቤትዎን እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ለማሻሻል በተከፈተው የዳሰሳ ጥናት ላይ በመሣተፍ ይረዱ
እንዴት እየሠራን እንደሆነ ከእናንተ መስማት እንፈልጋለን። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS)፦ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ወላጆች/ተንከባካቢዎች ሁሉንም በአካዳሚክ፣ በተግባቦት እና በአጠቃላይ የትምህርት ስርአቱን እርካታ በሚመለከት ከትምህርት ቤትዎ እና ከዲስትሪክቱ እና/ወይም MCPS ውስጥ በመስራት ያለዎትን ልምድ/ተሞክሮ እንዲያካፍሉን እየጋበዘ ነው። በደንብ እየተሠራ ያለውን እና መሻሻል ያለበትን እንድንረዳ እርስዎ የሚሰጡን አስተያየት ግብአት እና ግንዛቤ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። የእርስዎ ተሳትፎ እና ማንኛውም የተለየ መረጃ ሙሉ በሙሉ ሚስጥራዊ ነው። የሚሰበሰበው ግብረመልስ መተግበር ያለባቸውን ውሳኔዎች ለማሳወቅ እና በዲስትሪክታችን ለሚገኙ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ቤተሰቦች የበለጠ አጋዥ እና ትምህርትን የሚያበለጽግ አካባቢ ለመፍጠር ይጠቅማል።
ስለ ዳሰሳ ጥናቱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ጠቅ ያድርጉ። የዳሰሳ ጥናቱ አርብ፣ ማርች 15 ይዘጋል።
4. በቅርቡ የሚከናወኑ ዝግጅቶች፣ ማሳሰቢያዎች እና መገልገያዎች/ሪሶርሶች
ማርች 9 በሚካሄደው የሚቀጥለው የልጃገረዶች ጉባኤ ላይ ለመገኘት ዛሬውኑ ይመዝገቡ/RSVP
ቅዳሜ፣ማርች 9 በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሴት ልጆች ስብሰባ ስለሚካሄድ ይቀላቀሉን። ይህ ዝግጅት 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃ ሰጭ አውደ ጥናቶችን ያካሄዳል። ይበልጥ ያንብቡ ይመዝገቡ/RSVP
MCPS ከተፅዕኖ ፈጣሪ ልጃገረዶች ጋር በአጋርነት ይሠራል
MCPS ከ 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ከሚገኙ ተፅእኖ ፈጣሪ ልጃገረዶች እና ስለ ጾታ ከሚያቀነቅኑ ወጣቶች እና ነፃ የንግድ/የቢዝነስ እና የአመራር ፕሮግራምን ለማዳበር "Girls With Impact"ጋር በትብብር እየሠራ ነው። ከሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ መሪዎች ጋር የተገነባው ይህ 10-ሳምንት የኦንላይን ፕሮግራም ማርች 11 የሚጀምር ሲሆን ልጃገረዶች ስራ ፈጣሪዎች፣ የፈጠራ ችሎታ እንዲኖራቸው እና መሪዎች እንዲሆኑ ክህሎትን፣ እውቀትን እና በራስ መተማመንን ያስታጥቃቸዋል። ይበልጥ ያንብቡ
የሠመር ራይዝ ተቀባይ/አስተናጋጅ ለመሆን ዛሬውኑ ይመዝገቡ
ከ 2024-2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስኬታማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁኒየር እና ሲንየር ተማሪዎች ጋር የስራ ልምድዎን ለማካፈል ይፈልጋሉ? 2024 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም እንዴት ተቀባይ መሆን እንደሚችሉ ይወቁ! ይበልጥ ያንብቡ
Pregúntale a MCPS en Español Live
አምልጦዎት ከሆነ፤ "Preguntale a MCPS" ቡድን ከወላጆች ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል፣ እና ወላጆች በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ለሚፈልጉት ለውጥ እንዴት መደገፍና ማስተጋባት እንደሚቻሉ መግለጫ ሰጥቷል። MCPS en Español Facebook ገፅ ለመቀላቀል ለሁሉም ወላጆች የዝግጅቱ ክፍለጊዜ ክፍት ነበር። ቡድኑ ስለ ቅድመ-መዋእለ ህጻናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ፣ አፕሪል 22 በዲጅታል ስለሚሰጠው ትምህርት እና ስለ COSA ወቅታዊ መረጃዎችን አብራርቷል። ለመመልከት እዚህ ጠቅ ያድርጉ/ይጫኑ።
5. MCPS ዘገባዎች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ FY 2025 የበጀት አመት ኃላፊነት የተሞላበት በጀት አፅድቋልፌብሩዋሪ 22 በተካሄደ መደበኛ የስራ ስብሰባ፣ የትምህርት ቦርድ FY 2025 የበጀት አመት የስራ ማስኬጃ በጀት ወስኗል፣ ይህም የመማር ማስተማር ሂደትን የሚደግፍ እና ተጠያቂነትን የሚያጠናክር ሲሆን እንዲሁም ውስን የኢኮኖሚ ሁኔታንም ግምት ውስጥ በማስገባት በንቃት የሚተገበር ይሆናል። ሙሉውን መረጃ እዚህ ያንብቡ።
የህብረ ዝማሬ/Choral አስተማሪ የአመቱ ምርጥ ራይዚንግ አስተማሪ የሚል ስያሜ አግኝታለች
ዳንዬል ገቨር በስራዋ ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ብቃቷን ከፓርኩ በማውጣት አስደናቂ ውጤት አስመዝግባለች። በዌስትላንድ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የመዘምራን አስተማሪ የሆነችው ገቨር የዚህ አመት የአመቱ "Rising Star" መምህርት ሆናለች። ይበልጥ ያንብቡ
የጋልዌይ/Galway አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን የምህንድስና የምድር ትርኢት ቀን አካሂዷል። በትምህርት ቤት አቀፍ የተካሄደው የሙሉ ቀን ዝግጅት፤ ተማሪዎች የምህንድስና ችሎታቸውን ሁሉንም አይነት የምድርን ተዋጽኦ ሳያበላሹ በጥንቃቄ እየጠበቁ በአካባቢያዊ ተግዳሮቶች ላይ መፍትሔ የሚሆኑ ነገሮችን እንዲተገብሩ እድል ሰጥቷቸዋል።
የመጀመሪያው የወጣቶች የፀረ-ዘረኝነት ፊልም ፌስቲቫል 3 ምርጥ አሸናፊዎች
የመጀመሪያው የወጣቶች የፀረ-ዘረኝነት ፊልም ፌስቲቫል የተከናወነው በአስደናቂ ስኬት ነበር። ይህ በማይኖሪቲ ምሁራን ፕሮግራም የተስተናገደው ዝግጅት የተከናወነው ፌብሩዋሪ 24 ቀን AFI ሲልቨር ቲያትር እና የባህል ማዕከል ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በመማሪያ ክፍል ውስጥ ለዘረኝነት ምንም ቦታ እንደማይኖረው የሚገልጹ ኃይለኛ መልዕክቶችን የያዙ ዶክመንተሪዎችን አቅርበዋል። በአውደ ርእዩ ላይ 12 ፊልሞች የቀረቡ ሲሆን ከ100 በላይ ሰዎች ተገኝተዋል። የአሸናፊዎችን ዝርዝር ይመልከቱ።
"Caps Youth Hockey" የሮሊንግ ቴራስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን አስደንቋቸዋል
ዋሽንግተን ካፒታልስ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በሮሊንግ ቴራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ5ኛ ክፍል ተማሪዎች የሆኪ ክሊኒክ አስተናግዷል። ተማሪዎች የስፖርቱን መሰረታዊ ነገሮች ማለትም ዱላ አያያዝን፣ ማለፍ/ማሳለፍ እና መለጋትን ተምረዋል። የአካል ማጎልመሻ ትምህርት ባለሙያ የሆኑት ጄኒፈር ሩሺን እንዳሉት ዕድሉ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የተማሩትን ችሎታዎች እና ፅንሰ ሀሳቦችን እንዲለማመዱ ያበረታታቸዋል። ተማሪዎች ከክሊኒኩ ተቆጣጣሪዎች ጋር አንድ ለአንድ በሚሰጣቸው ገለጻ እየተመሩ ስለስፖርቱ ጥሩ የአድናቆት ስሜት እንዲኖራቸው ተደርጓል።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org