መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሀሙስ ሜይ 16/2024

ተማሪዎች $2.3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ስኮላርሺፕ ተሸላሚ ሆነዋል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ፋውንዴሽን "2024 Ruth እና Norman Rales-Patricia Baier O'Neill" ስኮላርሺፕ ጨምሮ በ 18 ስኮላርሽፖች ከ 225 በላይ ስኮላርሺፕ ያገኙትን ተሸላሚዎች ሜይ 15 እውቅና ሰጥቷል። ይበልጥ ያንብቡ


ሁለት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የዩ.ኤስ. ፕሬዝዳንታዊ ምሁር ስያሜ ተሰጥቷቸዋል 

ሁለት የሪቻርድ ሞንትጎመሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የ 2024 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምሁራን የተሰኘ ስያሜ አግኝተዋል። አንጀሊና ሹ እና ማክሲሚሊያን ፒ. ቤሊያንሴቭ (Angelina Xu and Maximilian P. Belyantsev) የተባሉት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች አስደናቂ የትምህርት ስኬትን፣ ስነ ጥበባዊ ብቃትን፣ ቴክኒካዊ እውቀትን፣ አመራርን፣ ስነ ዜግነትን፣ አገልግሎትን ጨምሮ ለት/ቤቶቻቸው እና ለማህበረሰባቸው አስተዋጾ ካደረጉ 161 ምርጥ አሜሪካውያን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መካከል ናቸው። ይበልጥ ያንብቡ


በትምህርት ላይ መገኘት እና መከታተል ጠቃሚ እና አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡ የቤል ፕሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ፕሮግራም ምልከታ

በዚህ ቪዲዮ የቤል ፕሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰራተኞች ከትምህርት ቤት መቅረትን ለመቀነስ እና አዘውትሮ በትምህርት ላይ መገኘትን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ከቤተሰቦች እና ከተማሪዎች ጋር እንዴት እንደሰሩ ያጋራሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎችን አዘውትረው በትምህርት ላይ መገኘት እንዳለባቸው ለመደገፍ ከቤተሰቦች ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኛ ነው። 

አንድ ተማሪ ከተመዘገበ(ች)በት ጊዜ አንስቶ 10 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ከቀረ(ች) ትምህርት ላይ እንደሌለ(ች) ይቆጠራል። እባክዎን በየቀኑ ልጅዎን(ልጆችዎን/ልጆቻችሁን) ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ጥረት ያድርጉ። ልጅዎን (ልጆችን) ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ምንም አይነት መሰናክሎች ካሉ፣ በትምህርት ቤትዎ ውስጥ የፈለጉትን ሰራተኛ ያነጋግሩ። እዚያ ያሉት ለመርዳት ነው።


መጪዎቹ የተማሪዎች እና የቤተሰብ ዝግጅቶች እንዳያመልጥዎት 

የበለጠ ለማወቅ ርእሶቹ ላይ ጠቅ ያድርጉ


የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰአታት ቅጾች የሚቀርቡበት ቀን ሜይ 31 

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ቅፆች የሚመለሱበት የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ሜይ 31 ነው። SSL ቅጾች በሙሉ ከጁን 1, 2023 በኋላ ለተጠናቀቀ ማንኛውም የተማሪ SSL አገልግሎት የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ የት/ቤቶች ስርአት አቀፍ የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ሜይ 31 መቅረብ አለባቸው። 2023–2024 የትምህርት አመት ወይም ከሠመር ወቅት በፊት ለተጠናቀቁ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት SSL ቅጾች ከሜይ 31 በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት SSL ሰዓቶች ማግኘት አለባቸው። 

ስለሚያስፈልጉት SSL ሰነዶች የበለጠ ይወቁ እና ከሠመር ወራት በፊት SSL የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ዕድሎችን ለማግኘት ይሞክሩ። 


ሃያ ስምንት የሂስፓኒክ ሲንየሮች የአካዳሚክ፣ እና የአመራር ብቃት እውቅና አግኝተዋል።

"Hispanic Alliance for Education" የሂስፓኒክ ትብብር ለትምህርት አመታዊ የተለየ ብቃት ያሳዩ የሂስፓኒክ ተማሪዎችን ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ሜይ 9 አካሄዷል። ሃያ ስምንት የላቲንክስ ተማሪዎች ታላቅ የአካዴሚያዊ ስኬት፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ እና የአመራር ችሎታ ሽልማት አግኝተዋል። በዝግጅቱ ላይ የነበሩትን ፎተግራፎች ይመልከቱ


ሜይ የተማሪ ፐርሶኔል ሰራተኞች እውቅና የሚሰጣቸው(PPW) ወር ነው! የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪ ፐርሶኔል ሰራተኞች (PPWs) ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ለሚያደርጉት ወሳኝ ስራ እውቅና በመስጠት ያለንን ጥልቅ አድናቆት በመግለጽ ከእኛ ጋር ይቀላቀሉን። የተማሪ ፐርሶኔል ሰራተኞች (PPWs) የፕሮግራም ለውጦችን በማድረግ እና ያለውን እድገት በመከታተል ተለይተው ለሚታወቁ ተማሪዎች እንደ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ያገለግላሉ። ከአስተዳዳሪዎች፣ ከወላጆች፣ ከካውንስለሮች እና ከአስተማሪዎች ጋር ይተባበራሉ፣ ስለ MCPS ፕሮግራሞች እና የማህበረሰብ ሪሶርሶች ያላቸውን እውቀት በመጠቀም ስለ ተማሪዎች ምደባ እና ጣልቃገብነት ይወስናሉ። 

በት/ቤቶች 2023-2024 የተማሪ ፐርሶናል ሰራተኞች ምደባ


መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦

  • ሜይ 18 ጌትስበርግ የመጽሐፍ ፌስቲቫል
  • ሜይ 23 የትምህርት ቦርድ ስብሰባ
  • ሜይ 24 ለተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን (ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ ለሚከተሉ ትምህርት ቤቶች ብቻ)
  • ሜይ 27 ሜሞሪያል ዴይ — ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው
  • ጁን 1 የኩሩ ማህበረሰብ ቀን/Pride Community Day
  • ጁን 13 ለተማሪዎች የመጨረሻ የትምህርት ቀን፣ ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን (ሁሉም ትምህርት ቤቶች)
  • ጁን 14* ውጤት መስጠት እና የተርሙ ማብቂያ እቅድ ማዘጋጀት
  • ጁን 19 ስርዓት አቀፍ ት/ቤቶች ዝግ የሚሆኑበት ቀን—ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ይሆናሉ


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)