2024 የምረቃ ፕሮግራሞች በመካሄድ ላይ ናቸው!
ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዲፕሎማ ያገኛሉ ተብሎ ለሚጠበቁ 12,000 በላይ ተማሪዎች በዚህ ሳምንት የምረቃ ስነ ስርዓት ተጀምሯል። ከሞንትጎመሪ ብሌር፣ ከደማስከስ፣ ከዊተን፣ እና ከፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ከጆን ኤል ጊልድነር ሪጅናል የህጻናት እና ጎልማሶች ተቋም (RICA) ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማቸውን ለመውሰድ ቀዳሚ ሆነዋል። በዊንስተን ቸርችል፣ ፑልስቪል፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ እና ቶማስ ኤስ. ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምረቃ ሥነ ሥርዓቶች ይቀጥላሉ። ይበልጥ ያንብቡ
የምረቃ ቀናት፣ጊዜ/ሠአት፣ንግግር የሚያደርጉ እንግዶች፣ እና የምረቃ ሥነ ስርአት የሚካሄዱባቸው ቦታዎች ዝርዝር
ለሪጅናል እና የሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት እና የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰአት ቅጽ ተሞልቶ መቅረብ ያለበት ጊዜ አርብ፣ ሜይ 31 የመጨረሻ ቀን ነው።
ሪጅናል የሠመር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም (በአካል) እና የሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ፕሮግራም (ቨርቹዋል) የመጀመሪያው ዙር ምዝገባ አርብ፣ ሜይ 31 ይጠናቀቃል/ይዘጋል። ክፍያ እስከ ጁን 16 ድረስ ማጠናቀቅ ያስፈልጋል፤ ካልሆነ ተማሪው(ዋ) ከትምህርቱ ይወጣል/ትወጣለች። የመጀመሪያው ዙር ከጁን 26 እስከ ጁላይ 16 ይካሄዳል (ጁላይ 4 ትምህርት የለም)፣ ሁለተኛው ዙር ከጁላይ 18 እስከ ኦገስት 6 የሚካሄድ ሲሆን የ 2ኛው ክፍለ ጊዜ ምዝገባ እሁድ፣ ጁን 30 ይዘጋል። ወላጆች ተማሪዎቻቸውን ParentVue አካውንታቸው ላይ ማስመዝገብ ይችላሉ። ለሠመር ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የክፍያ መጠየቂያው ሠነድ ካልደረሰዎት፣ እባክዎ የተማሪዎን ካውንስለር ያነጋግሩ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ቅጾችን ለማስረከብ የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ሜይ 31 ነው። SSL ቅጾች በሙሉ ከጁን 1, 2023 በኋላ ለተጠናቀቀ ማንኛውም የተማሪ SSL አገልግሎት የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ የት/ቤቶች ስርአት አቀፍ የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ሜይ 31 መቅረብ አለባቸው። 2023–2024 የትምህርት አመት ወይም ከሠመር ወቅት በፊት ለተጠናቀቁ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት SSL ቅጾች ከሜይ 31 በኋላ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 SSL ሰዓቶች ማግኘት አለባቸው።
ስለሚያስፈልጉት ሰነዶች የበለጠ ይወቁ እና ከሠመር ወራት በፊት SSL የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ዕድሎችን ለማግኘት ይሞክሩ።
ጁን 1 የኩሩ ማህበረሰብ ቀን ይካሄዳል።
ቅዳሜ፣ ጁን 1 ከሠአት በኋላ 1:30–5 p.m. የኩሩ ማህበረሰብ ቀን በቤተስዳ-ቼቪ ቼዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ይህ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ችሎታ የሚታይባቸው ትርኢቶች፣ ጨዋታዎች፣ ዲጄ እና ዳንስ፣ የእጅ ስራዎች፣ የትረካ ጊዜ፣ በመኪናዎች የሚቀርብ ምግብ፣ እና ሽልማቶችን ያካትታል። እንዲሁም ለእንክብካቤ ሰጪዎች እና ለሰራተኞች ጠቃሚ የሆኑ የሪሶርሶች ትርኢት እና አውደ ጥናቶች ይኖራሉ። ይበልጥ ያንብቡ
ለዓመታዊው ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ካላንደርዎን (ቀን መቁጠሪያ) ምልክት ያድርጉ
MCPS ዓመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ቅዳሜ፣ ኦገስት 24 ቀን 10፡00 a.m. እስከ 1 p.m. በዊተን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል/Westfield Wheaton mall ያስተናግዳል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤቶች ስርዓትአቀፍ መረጃ እና የካውንቲ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው። ሙዚቃ፣መዝናኛ፣ልዩ ልዩ ስጦታዎች እና የቤተሰብ እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩ በነጻ ይደሰታሉ። ክትባት የሚሰጥበትም ክሊኒክ ይኖራል ነፃ የመጓጓዣ አውቶቡስ ይኖራል።
አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road. በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ጋር ይከታተሉ።
"GIVE Backpacks" ዘመቻ እየተካሄደ ስለሆነ ዛሬውኑ ይለግሱ
13ኛው አመታዊ GIVE BACKpacks ዘመቻ በመካሄድ ላይ ስለሆነ፥ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በጀርባ የሚያዝ የደብተር/የመጻህፍት ቦርሳዎችን እና የት/ቤት ቁሳቁሶችን በመግዛት የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው።
እስከ $20 ዶላር ወጪ ቢለግሱ፣ ወረቀት፣ እርሳሶች፣ ከለሮች/ እስክሪብቶዎች፣ የእርሳስ መቅረጫ፣ የወረቀት መያዣ ባይንደሮችን፣ ፎልደሮችን፣ እና ሌሎችንም አስፈላጊ የትምህርት እቃዎችን ጨምሮ የታጨቀ ቦርሳ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች መስጠት ይችላሉ።
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፓራኢጁኬተር/ረዳት መምህር ይሁኑ!
ሰኞ፣ጁን 3 ቀን 5–7 p.m. የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በስፕሪንግብሩክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለፓራዱካተሮች የስራ አውደ ርእይ ያዘጋጃል። ከመዋለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍል የመሥራት እድሎች ይኖራሉ። አመልካቾች/እጩዎች MCPS Careers ላይ ክፍት የስራ መደቦችን መፈለግ ይችላሉ።መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org