ባነር

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ ጁላይ 19፣ 2024

ቦርዱ በዚህ የሠመር ወቅት ለሚመጣው አመት የሥራ እቅድ በማዘጋጀት ጠንክሮ እየሰራ ነው። ስለ ቦርድ አባላት ተግባራት፣ ስለ 2024-25 የሥራ እቅድ ዝግጅት፣ እና ስለ አመቱ ክንውን ግምገማ ለማወቅ በተከታታይ ያንብቡ። ለህዝብ አገልግሎት ፍላጎት ያላቸው፣ በስነምግባር ፓነል ( Ethics Pane) ላይ ለማገልገል እንዲያመለክቱ እንጋብዛለን። 

በተገባደደው አመት የተማሪዎችን ስኬቶች እና ግስጋሴዎች እናከብራለን

በ 2023-24 የትምህርት አመት የተከናወኑትን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎችን አስደናቂ ስኬቶች ቦርዱ ያከብራል! ከተገባደደው ዓመት ስኬታማ ክንውኖች ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • 2024 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂዎች ውስጥ 268 ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ ዲግሪ አግኝተዋል 

  • 3,904 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓታት ማጠናቀቃቸው ተመዝግቧል

  • 17,926 ተማሪዎች CTE ኮርሶች ላይ ተመዝግበዋል።

ምን ያህል ተማሪዎች በስራ ላይ የተመሰረተ ትምህርት ላይ እንደተሳተፉ፣ MCPS የተማሪ-አትሌቶች ምን ያህል ታይትሎችን እንዳገኙ፣እና ሌሎችንም ሙሉውን የተገባደደውን አመት ክንውን በማየት በርካታ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የቦርድ አባላት ሚና ውስጥ፡ ከትርፍ ጊዜ የሥራ ኃላፊነት የበለጠ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አባላት ሃላፊነታቸውን ከመወጣት አንጻር በሀገሪቱ 15ኛ ትልቁ የት/ቤቶች ዲስትሪክት የሥራ ክንውኖችን ለመከታተል እና ፖሊሲ ማውጣትና ረገድ የሙሉ ጊዜ ኃላፊነት ወስደው በቁርጠኝነት እያሠሩ ናቸው። 

ቦርዱ ስራዎቹን ለማከናወን ስብሰባዎችን ማካሄድ ወሳኝ ናቸው። በ 2023-24 የትምህርት አመት የቦርድ አባላት 79 ኦፊሴላዊ ስብሰባዎችን አካሄደዋል። መረጃዎችን ለማደራጀት፣ ለመሰብሰብ፣ እና ለመገምገም፣ እንዲሁም ከሰራተኞች ጋር በመተባበር ለእያንዳንዱ ስብሰባ ለመዘጋጀት ከበርካታ ጊዜ በመሰዋት ሠርተዋል።

ሌላው ቁልፍ የቦርድ አባላት ሚና ከተማሪዎች፣ ከቤተሰቦች፣ እና ከሰራተኞች ጋር መገናኘት ነው። እነዚህን ጠቃሚ ግንኙነቶች ከማህበረሰቡ ጋር በተለያዩ መንገዶች ማለትም በኢሜል፣ የስልክ ጥሪዎችን በማድረግ፣ እና ትምህርት ቤቶችን በመጎብኘት ያከናውናሉ።

የቦርድ አባላት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተወካዮች እና አቀንቃኞች በመሆን፣በማህበረሰቡ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ። በትምህርት ቤቶች እና በማህበረሰብ ዝግጅቶች ላይ በቋሚነት የሚሳተፉ ናቸው፣በካውንቲው ውስጥ ካሉ ድርጅቶች ጋር ያገለግላሉ፣ እና በካውንቲው ውስጥ ከተመረጡ ባለስልጣናት ጋር ይተባበራሉ።

ጁላይ 18 በተከናወነ ዝግጅት ላይ የቀረበውን መግለጫ በመመልከት የቦርድ አባል መሆን ማለት ምን ያህል ሥራ እንደሚሠራ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ያግኙ።

ስለ የቦርዱ የሠመር ስራ ያውቃሉ?

ስለ ሠመር ወቅት የእረፍት ጊዜ እና ሥራዎች የሚቀዛቀዙበት ጊዜ እንደሆነ እናስባለን። ለትምህርት ቦርድ አባላት ግን እንዲህ አይደለም። የሠመር ወቅት የተለያዩ እቅዶች የሚዘጋጁበት፣ስራ የሚበዛበት፣የዝግጅት ጊዜ ነው። 

ባለፉት በርካታ ሳምንታት ውስጥ የቦርድ አባላት ለ 2024-25 የትምህርት አመት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ለማቀድ የ MCPS ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን፣ እና ሰራተኞችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በማጥናት፣በማንበብ እና ፍላጎቶችን የመገምገም ሥራዎችን እያከናወኑ ሰንብተዋል።

ቦርዱ በአንድነት የተባበረ ቡድን እንደመሆኑ፣በ 2024-25 የትምህርት አመት ትኩረት የሚደረግባቸው ስራዎችን እንደሚከተለው በቅደምተከተል አስቀምጧል።

  • በሂሳብ ትምህርት እና በንባብ የተማሪዎችን ስኬት ማሻሻል፣

  • ለሉም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ እና አካታች የትምህርት አካባቢ መኖሩን ማረጋገጥ፣

  • የትምህርት ባለሙያዎች ፍሰት ማሻሻል፣ 

  • የተማሪዎችን ተሳትፎ የሚያበረታቱ እና የሚደግፉ የምረቃ መስፈርቶች እና ሥርዓተ-ትምህርት በተጓዳኝ እንዲከናወኑ ማስቻል። 

በተጨማሪ የቦርድ ኮሚቴዎች የአመቱን የስራ እቅድ በማዘጋጀት ላይ ይሳተፋሉ። የቦርዱ አምስት ኮሚቴዎች በሴፕቴምበር ወር እንዲፀድቅ እቅዳቸውን ያቀርባሉ። የኮሚቴ አባላት ትኩረት የሚሰጧቸው ጉዳዮች ቦርዱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች እንዴት እንደሚደግፍ/እንደሚያሣልጥ እና ዲስትሪክቱን ወደፊት እንደሚያራምድ ለመወሰን ብዙ ጊዜ እና ጉልበት ያጠፋሉ። 

ቦርዱ ቅድሚያ ትኩረት ስለሚሰጣቸው ጉዳዮች እና የኮሚቴ የስራ እቅዶችን በተመለከተ ዝርዝር ለማወቅ ኦገስት እና ሴፕቴምበር ላይ ይጠብቁን።

ቦርዱ ለሥነምግባር ፓነል ክፍት የሥራ ቦታ (Ethics Panel Vacancy) አመልካቾችን ይጋብዛል

የሥነ ምግባር ፓነል ከፍተኛ የስነምግባር ደረጃን ያበረታታል፣ እንዲሁም ማህበረሰቡ በቦርዱ ላይ ያለው እምነት እንዲጎለብት ጥረት ያደርጋል። የህብረተሰቡ አባላት በሥነ ምግባር ፓነል ያለውን ክፍት የሥራ ቦታ ለመሙላት ፍላጎታቸውን እንዲገልጹ ተጋብዘዋል። ፍላጎታቸውን የሚገልጹበት ደብዳቤ እና የስራ ልምድ መግለጫ (resume) እስከ ኦገስት 2 መቅረብ አለበት። ድረ ገጽ ላይ ስለሚኖራቸው ሚና እና ማመልከቻ ስለሚቀርብበት ሂደት የበለጠ ይወቁ።

የተሳትፎ እድሎች

ህብረተሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።

ቅዳሜ፣ ኦገስት 24፣ቀን 10:00 a.m. - 1:00 p.m., በዌስትፊልድ ዊተን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ በሚካሄድበት ቦታ ተገኝታችሁ የቦርድ አባላትን ተቀላቀሉ! 

ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ማክሰኞ፣ ኦገስት 20 - መደበኛ የሥራ ስብሰባ

አጀንዳዎችን፣የስብሰባ ግብአቶችን ለማየት/ለመከታተል በቀጥታ ስርጭት ወይም የተቀዳ የስብሰባ ውይይት ለመመልከት የእኛን ድረ ገጽ ይጎብኙ።

ግንኙነትዎ ይቀጥል

ፌስቡክ እና X  ላይ ይከታተሉ

ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org