እንግሊዝኛ/English / ስፓንሽኛ/Español / 中文 / ፈረንሳይኛ/Français / ፖርቹጋልኛ/Português / 한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
አዲሱ የትምህርት አመት በጥንካሬ ተጀምሯል፣እና ወደፊት እየገሰገስን ነው። የትምህርት ቤቶች መከፈት ዝግጅት አቀራረቡ ስኬትን ያሳያል፤ እና መሻሻል ያለባቸውንም ነገሮች ያመላክታል። እንዲሁም በቦርድ ስብሰባ ላይ፣ የዲስትሪክቱ ሰራተኞች - በዚህ አመት ቦርዱ ቅድሚያ መስጠት ያለበትን የተማሪዎችን የሊተርሲ ትምህርት የአፈፃጸም ቁመና አጉልተው አሳይተዋል። በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የቦርድ ኮሚቴዎች ስራቸውን ስለሚጀምሩ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።
ዶ/ር ቴለር የትምህርት ቤቶችን መከፈት ለቦርዱ ሲያሳውቁ “ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በጉጉት መቀበላቸውን እና የትምህርት አመቱ በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን ገልፀዋል”።
ትምህርት ከተጀመረበት ጥቂት ሳምንታት ብዙ የሚደነቁ ነገሮች አሉ። ሰራተኞቻችን ጅማሬአችንን በጠንካራ ሁኔታ ለማቀላጠፍ ቁርጠኝነት አሳይተዋል። ይህ የሚያካትተው፦
ለተማሪዎች አወንታዊ የትምህርት ስኬቶችን የሚያጎናጽፉ ስልቶች
ከማዕከላዊ የሚሰጡ አገልግሎቶችን እና በትምህርት ቤቶች መካከል ግንኙነቶችን መገንባት እና ማጠናከር
የትምህርት ቤቶችን ደህንነትን እና ሠላም ማሻሻልና ማጠናከር
ንቁ የሆነ ግንኙነትን ማዳበር እና ክትትል ማድረግ
የትምህርት ቤቶችን መክፈቻ ዝግጅት ዝርዝሮቹን ይመልከቱ።
በዚህ የትምህርት አመት ከቦርዱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባሮች ውስጥ አንዱ የተማሪዎችን የማንበብ ስኬት ለማሻሻል የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በትኩረት እንዲሠራና ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ ነው። ሴፕቴምበር 12 በተካሄደው የቦርድ ስብሰባ፣የቅድመ ሊተርሲ ክህሎትን በሚመለከት ትርጉም ያለው እድገት መታየቱን ሰራተኞች ሪፖርት አድርገዋል።
ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ሁለተኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የማስተማር ዘዴዎቻችን እና የማሻሻል ጣልቃ ገብነት ጥረቶቻችን የትምህርት ችሎታቸውን ለማዳበር ምን ያህል እንደጠቀማቸው ለማወቅ የሚያግዙ የንባብ ግምገማዎች ይደረጋሉ። የተማሪዎች የሊተርሲ ችሎታቸው የሚገመገመው የሚከተሉትን ፈተናዎች/ቴስቶች በመጠቀም ነው።
መሠረታዊ ቀደምት የሊተርሲ ችሎታ እድገት አመልካቾች (DIBELS)
Lectura
2023-24 የትምህርት አመት ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 2ኛ ክፍል የተማሪዎች የፈተና ውጤት መረጃ ከፍተኛ የንባብ ክህሎት እድገት መኖሩን ያሳያል። በሁሉም የክፍል ደረጃዎች እና በተለያየ ዘር/ብሄረሰብ እና የአገልግሎት ቡድኖች ውስጥ 2023 ፎል እና 2024 ዊንተር ፈተናዎች ጋር ሲነጻጸር በስፕሪንግ ወቅት ምዘናዎች ላይ ከፍ ባለ ፐርሰንቴጅ ተማሪዎች አልፈዋል።
ይህ ዘገባ/ሪፖርት አበረታች ዜና ነው። በዝቅተኛ ክፍሎች የማንበብ ሳይንስ አቀራረባችን ለሊተርሲ ትምህርት የቁርጠኝነት ትልማችን እየሰራ ነው።
ሁሉም ተማሪዎች አስፈላጊ የንባብ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ለመደገፍ ዲስትሪክቱ በተሻለ ሁኔታ እየሠራ ስላለ ቦርዱ በቀጣይነት የተሻሻሉ ውጤቶችን በጉጉት ይጠብቃል።
ከውሂቡ የተወሰኑ ግኝቶችን ጭምር ተጨማሪ ለማወቅ እዚህ የቀረበውን ይመልከቱ።
የቦርዱ የስራ አድማስ ሰፊ ስለሆነ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በዝርዝር ይዳስሳል። ቦርዱ ውሳኔዎችን ማጤን፣ የተከናወኑ መሻሻሎችን መገምገም፣ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ለመወሰን የሚራመድበት አንዱ መንገድ የኮሚቴዎች ሥራ ነው። እያንዳንዱ ኮሚቴ በሚከተሉት የተለየ ዘርፍ ላይ ያተኩራል፦
የኮሚቴ ስብሰባዎች ዓመቱን ሙሉ የሚካሄዱ ሲሆን በቦርዱ የስብሰባ ካላንደር ላይ ተዘርዝረዋል። ልክ እንደ መደበኛ የሥራ ስብሰባዎች፣ በአካል ለመገኘት እና በቀጥታ ስርጭት የኮሚቴ ስብሰባዎች ለህዝብ ክፍት ናቸው።
ከእርስዎ ፍላጎት ጋር የሚስማማ የኮሚቴ ስብሰባዎችን እንዲከታተሉ እናበረታታዎታለን። የትምህርት አመቱ የመጀመሪያ ስብሰባዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳሉ፣ ቀኖቹን ለማወቅ ወደ ታች ይሸብልሉ።
ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 16- የኮሙዩኒኬሽን/የግንኙነት እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ኮሚቴ ስብሰባ
ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 17- የፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ስብሰባ
ሀሙስ፣ ሴፕቴምበር 19- የልዩ ማህብረሰብ/Special Populations ኮሚቴ ስብሰባ
ሰኞ፣ ሴፕቴምበር 23 - የስትራቴጂክ እቅድ ኮሚቴ ስብሰባ
ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 24 - የፊስካል ማኔጅመንት ኮሚቴ ስብሰባ
ሀሙስ፣ ሴፕቴምበር 26- የስራ ስብሰባ
አጀንዳዎችን፣የስብሰባ ግብአቶችን ለማየት/ለመከታተል በቀጥታ ስርጭት ወይም የተቀዳ የስብሰባ ውይይት ለመመልከት የእኛን ድረ ገጽ ይጎብኙ።
ማህበረሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍ እና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።
ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org