ርእሰ ጉዳይ

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ፦ ኦክቶበር 25, 2024
ኖቬምበር 8, 2024

የትምህርት ቦርድ/Board of Education ዓመታዊ የበጀት ሂደቱን የጀመረው በበላይ ተቆጣጣሪው ለተመከረው የስራ ማስኬጃ በጀት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች በመዘርዘር ነው። በተጨማሪም ቦርዱ ለ2025-26 የትምህርት ዘመን የሂሳብ ትምህርት ስርዓተ ትምህርትን   እና pilot/የሙከራ ኮርሶችን አጽድቋል።

እንዲሁም የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም እና የካፒታል በጀት/Capital Improvement Program and Capital Budget በሚል ርዕስ ሁለት ህዝባዊ ውይይቶችን ካስተናገደ በኋል በዚህ ርዕስ ላይ ውይይት ለማድረግ ቦርዱ አርብ፣ ኖቬምበር 8, የስራ ክፍለ ጊዜ አካሂዷል። ቦርዱ በዚህ ርዕስ ላይ ሐሙስ፣ ኖቬምበር 21 የመጨረሻ እርምጃ ይወስዳል። የበለጠ ለማወቅ የስራ ክፍለ ጊዜውን ቅጂ መመልከት/ማየት ይችላሉ።

ልህቀትን ማረጋገጥ፡ ለተማሪ ስኬት እና ደህንነት ሲባል ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች በጀት መመደብ/Budget Priorities for Student Achievement and Safety

የ2026 በጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀትን የማዘጋጀት እና የማጽደቅ ሂደት ገና በሂደት ላይ ነው። በቦርዱ በተቀመጡት ግቦች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች በመመራት፣ የMCPS የበላይ ተቆጣጣሪ ዶ/ር ቶማስ ቴይለር በበጀት እቅዱ ላይ እየሰራ ሲሆን ዕቅዱንም ዲሴምበር ላይ ለትምህርት ቦርዱ ያቀርባል። 

ቦርዱ የካውንቲ ሀብቶች/ሪሶርሶች ጥሩ አስተዳዳሪ ለመሆን ያለመ ሲሆን አሁን ያለውን የፊስካል ሁኔታም ይገነዘባል። የቦርዱ ፕሬዘዳንት ካርላ ሲልቬስትሬ የውይይቱን ዓላማ አስቀምጠዋል፣ “ግባችን ይህ የት/ቤት ስርዓት ለሚታወቅበት ከፍተኛ የስኬት ደረጃዎች ቅድሚያ የሚሰጥ በጀት በማዘጋጀት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ ፍትሃዊነትን እና አካዴሚያዊ ልህቀትን ማረጋገጥ፣ እና የተማሪዎቻችንን ደህንነት መጠበቅ ነው።''

ቦርዱ የሚከተሉትን በጀት ሲመደብ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለዶ/ር ቴይለር እና ለህዝቡ አጋርቷል፡

  • የተሻሻለ የሂሳብ እና የማንበብና መጻፍ አፈፃፀም ለሁሉም ተማሪዎች

  • የተማሪዎቻችን ደህንነት

  • ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች የጤንነት/የደስተኛነት ድጋፍ

  • የኮሌጅ እና የሙያ ዝግጁነትን የሚደግፉ ሪሶርሶች

  • በካውንቲው ውስጥ ያሉ ፕሮግራሞችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ተደራሽ ማድረግ

የበጀት ሂደቱ ሲቀጥል፣ ህዝቡ የሚሳተፍባቸው እድሎች ይኖራሉ። ቦርዱ ጃንዋሪ ላይ የስራ ክፍለ ጊዜዎችን እና ህዝባዊ ውይይቶችን ያካሂዳል። ቦርዱ ፌብርዋሪ ላይ የስራ ማስኬጃ በጀት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፣ ይህም ለግንዛቤ/አጽንዖት እንዲሰጠው ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት ይቀርባል።

በጀት ሲመደብ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ላይ የቀረበውን ፕረዘንቴሽን ይመልከቱ

ቦርዱ አዲስ የመማር እድሎችን/New Learning Opportunities አጽድቋል

ቦርዱ ለ2025-2026 የትምህርት ዘመን አንድ አዲስ የሁለተኛ ደረጃ ፓይለት/የሙከራ ኮርስን አጽድቋል እና የሙከራ/የፓይለት ኮርሶችን ዝርዝር በመካከለኛ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አክቲቭ እንዲሆኑ አድርጓል። ይህ ስራ የMCPS የስርዓተ ትምህርት የተሟላ እና አጠቃላይ ግምገማን እና የምረቃ መስፈርቶችን መደገፍ ከሚለው ከቦርዱ ዓመታዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የሚጣጣም ነው።

በስርአተ ትምህርት እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ጽህፈት ቤት/Office of Curriculum and Instructional Programs የቀረቡት የሚከተሉት ምክረ ሀሳቦች/ሪኮመንዴሽኖች ለ2025-2026 የትምህርት ዘመን ጸድቀዋል፡

  • አንድ አዲስ ዋና ያልሆነ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፓይለት/የሙከራ ኮርስ - Hip Hop Poetics and Rhetoric: Exploring the Golden Age of Hip Hop at Montgomery Blair High School.

  • በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሰባት ኮርሶች አክቲቭ ይሆናሉ፡

    • Color Guard በ James Hubert Blake ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በ Northwood ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

    • የዘር ማጥፋት ጅምላ ግድያ ጥናቶች/Holocaust Studies በBethesda Chevy-Chase ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

    • ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ/Global Climate Change በNorthwood ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በWalter Johnson ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

    • የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ምናባዊ እውነታ ንድፍ መርሆዎች/Principles of Artificial Intelligence and Virtual Reality Design (AIVR) በNorthwood ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 

    • የጎሳ/የዘር ጥናቶች/Ethnic Studies በPoolesville ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

    • ማስተዋል ለታዳጊዎች/Mindfulness for Teens በThomas S. Wootton ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

    • የሙስሊም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች/Muslim Global Experiences በCol. (Col. Zadok Magruder High School)

  • በተመረጡ መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ሶስት ኮርሶች አክቲቭ ይሆናሉ፡

    • በHumanities ውስጥ ስነ-ጽሁፍ 7/8 በ Eastern መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

    • የስፖርቶች እና የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች/ተግባሮች ሳይንስ/Science of Sports and Recreational Activities (SSRA) በKingsview መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

    • Technical Theater ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ Mario Loiederman መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ተማሪዎች በሙከራበፓይለት ኮርስ ሂደት ውስጥ በንቃት ይሳተፋሉ። የተማሪ ፍላጎት እና ቅስቀሳ /ሙግት ለአዲስ የሙከራ/ፓይለት ኮርሶች ርዕሶችን ለመለየት ይረዳል። ዓመታዊ የጥናት ፕሮግራም ሲዘጋጅ ፓይለት/የሙከራ ኮርሶች በተሳትፎ ላይ ተመስርተው ይገመገማሉ። ስለእነዚህ ፓይለት/የሙከራ ኮርሶች እና ስለሂደቱ ፕረዘንቴሽኑን በመመልከት ይወቁ/ይማሩ

ቦርዱ የሂሳብ ስርዓተ ትምህርትን መጠቀም መቀጠልን አጽድቋል። 

ቦርዱ፣ የተማሪን የሂሳብ ውጤት ለማሻሻል ዲስትሪክቱ በሚያደርገው ጥረቶች ላይ በማተኮር Eureka Mathematics and Illustrative Mathematics የMCPS ዋና የሒሳብ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርቶች ሆነው እንዲቀጥሉ አጽድቋል። 

እነዚህ ሥርዓተ ትምህርቶች የትምህርት ደረጃዎችን/መመዘኛዎችን የሚያሟሉ እና ተማሪዎች ጠንካራ የሂሳብ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ የሚያግዙ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሳቁሶች/ማቴሪያሎች ያቀርባሉ። ተማሪዎች ስለ ሂሳብ በጥልቀት እንዲያስቡ እና በዕለት ተዕለት ሁኔታዎች ውስጥ እንዲጠቀሙበት በማድረግ ላይ ያተኩራሉ። በተጨማሪም ፕሮግራሞቹ ተማሪዎች የቱ ጋር እንደሚቸገሩ ለመለየት የሚረዱ መሳሪያዎችን እና እንዲሻሻሉ የሚረዷቸው ሪሶርሶችን ያካትታሉ። እነዚህን ሥርዓተ ትምህርቶች በወጥነት/በተከታታይ በመጠቀም፣ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በተማሩት ነገር ላይ መገንባት ይችላሉ፣ እና መምህራን ለተሻለ ውጤት የማስተማሪያ ዘዴያቸውን ማሻሻል ይችላሉ።

ፕረዘንቴሽኑን በመመልከት የበለጠ ይወቁ።

አዲስ የሰብዓዊ ካፒታል ማኔጅመንት ሲስተም/New Human Capital Management System በዲሴምበር ይመጣል።

MCPS ዲሴምበር ላይ የሰው ሃብት መረጃ ስርዓቱን በዘመናዊ፣ ኢንተርኔትን መሰረት ባደረገ የሰብዓዊ ካፒታል ማኔጅመንት/Human Capital Management(HCM) መድረክ ያዘምናል። አዲሱ ሲስተም የበለጠ ቀልጣፋ እና ለተጠቃሚ ምቹ ይሆናል። ሰራተኞቹ የሽግግር እቅዱን እና ይህ አዲስ ሲስተም ሰራተኞችን እና ጡረተኞችን እንዴት እንደሚጠቅም የሚመለከት ወቅታዊ መረጃ አጋርተዋል። የበለጠ ለማወቅ ፕረዘንቴሽኑንይመልከቱ።

ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ኖቬምበር 14, ሀሙስ - የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴ/Policy Management Committee

  • ኖቬምበር 18, ሰኞ - ፊስካል ማኔጅመንት ኮሚቴ/Fiscal Management Committee

  • ኖቬምበር 21, ሀሙስ - የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም ውሳኔዎች ስብሰባ/Capital Improvement Program Decisions Meeting

  • ዲሴምበር 2, ሰኞ - የቦርድ አባል ቃለ-መሀላ መፈጸሚያ ፕሮግራም

  • ዲሴምበር 5, ሀሙስ - የቢዝነስ ስብሰባ

አጀንዳዎችን፣የስብሰባ ግብአቶችን ለመከታተል በቀጥታ ስርጭት ወይም የተቀዳ የስብሰባ ውይይት ለመመልከት የእኛን ድረ ገጽ ይጎብኙ።

የመሳተፍ እድሎች

ማህበረሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍ እና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።

ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በፌስቡክ እና X  ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org