ርእሰ ጉዳይ

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ፦ ኦክቶበር 25, 2024
ኖቬምበር 22, 2024

የትምህርት ቦርድ በCIP ላይ እርምጃ የወሰደ ሲሆን ኖቬምበር 21 በተደረገው ስብሰባ ወቅት የወሰን ጥናት ሂደት ላይ ተወያይቷል። ዲሴምበር 2 ለሚደረገው የአባላት ሽግግር እየተዘጋጀን ነው፣ ግን በመጀመሪያ፣ ለሁሉም መልካም የታንክስጊቪንግ በዓል እንዲሆን እንመኛለን።

ቦርዱ አዲስ ትምህርት ቤቶችን እና የመሠረተ ልማት ማሻሻያዎችን ጨምሮ የ169.9 ሚሊዮን ዶላር የካፒታል በጀት ጥያቄ አጽድቋል።

ቦርዱ በበላይ ተቆጣጣሪው የተመከሩ የ2026 የበጀት ዓመት/Fiscal Year (FY) ካፒታል በጀትን እና የ2025-2030 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ማሻሻያዎችን በስድስት አመት የCIP ጊዜ ውስጥ በድምሩ 1.853 ቢሊዮን ዶላር አጽድቋል።

የFY26 የካፒታል በጀት የመጠቀም ፈቃድ ጥያቄ በድምሩ 169.9 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን የገቢ እጥረቶችን ለመፍታት ከካውንቲው ተጨማሪ 21.6 ሚሊዮን ዶላርን ያካትታል። 

በጀቱ እና ማሻሻያዎቹ አራት ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ አቅርቦት ማድረግ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡

  • ቻርልስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - የኦዲቶሪያም ግንባታ ማጠናቀቅን ጨምሮ

  • ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - ኦዲቶሪየም፣ ስታዲየም፣እና ሌሎች የመማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ አዲስ ግንባታ ማጠናቀቅ

  • ኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - ስታዲየምን እና የውጪ ቦታዎችን ግንባታ መሥራት

  • የሎደርማን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት - ማሞቂያ፣ አየር ማናፈሻ፣ እና የአየር ማቀዝቀዣ መሠረተ ልማትን ሥራ ማጠናቀቅ

ቦርዱ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በተደረጉት ሁለት የCIP የህዝብ ውይይቶች ላይ ለተሳተፉት ሁሉ አድናቆቱን ይገልጻል። ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለት/ቤቶቻችን ለመሟገት የወጣው ጊዜ እና ጥረት የሂደቱ ጠቃሚ አካል ነው።

በካፒታል በጀት ሂደት ውስጥ ቀጣዩ ደረጃ የካውንቲው ምክር ቤት የቦርዱን የድጋፍ ጥያቄ መገምገም ነው። የመጨረሻው የማጽደቅ ሂደት በዊንተር ወቅት መጨረሻ ላይ ይጠበቃል።

ስለ CIP የበለጠ ለማወቅ ፕረዘንቴሽኑን ይመልከቱ።

ቦርዱ ለመጪው የድንበር ጥናቶች/Upcoming Boundary Studies አቅራቢን ግምት ውስጥ እያስገባ/እየተመለከተ ነው።

MCPS ከ26ቱ የMCPS 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ19ኙን እና ከእነሱ ጋር ተዛማጅ የሆኑ መለስተኛ/መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በማሳተፍ መጠነ ሰፊ የወሰን ጥናት ያካሂዳል። 

የድንበር ጥናቱ የሚያስፈልገው የCrown ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የDamascus ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና የ Charles W. Woodward ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ድንበሮችን ለመወሰን ነው። እንዲሁም በዲስትሪክቱ ውስጥ የቦታ ፍላጎቶችን ለማቃለል እድል ነው። ቦርዱ ዲሴምበር 5፣ 2024 በሚደረገው የቦርድ ቢዝነስ ስብሰባ ላይ ግምት ውስጥ የሚያስገባቸውን ጉዳዮች ይቀጥላል።

MCPS ለCrown እና Woodward የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፕሮጀክቶች መጪውን የወሰን ጥናት እንዲያካሂድ አቅራቢ፣ FLO Analyticsን ጠቁሟል። በውይይቱ ወቅት፣ ቦርዱ በወሰን ጥናቱ የፕሮግራም ትንተና ገፅታ ላይ እና በሂደቱ ውስጥ በሙሉ አቅራቢው የቦርዱን የአካታች እና የወካይ ማህበረሰብ መመዘኛዎችን/ደረጃዎችን እንዴት እንደሚያሟላ ይበልጥ ለመረዳት ግልጽ እንዲደረግለት ጠይቋል። ቦርዱ ዲሴምበር 5 በሚካሄደው የቢዝነስ ስብሰባ ላይ የተመከረው አቅራቢን በተመለከተ እርምጃ ይወስዳል ተብሎ ይጠበቃል።

እነዚህ ሁለቱም የድንበር ጥናቶች በርካታ ትምህርት ቤቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ቦርዱ በተሰየሙ የቡድን ስብስቦች ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰቦች በየጊዜው ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኙእና በሂደቱ ውስጥ እንዲሳተፉ ያበረታታል።

የሁለቱን የድንበር ጥናቶች ወሰን ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ፕረዘንቴሽኑን ይመልከቱ ወይም ይህን ሰነድ (pdf) ይመልከቱ።

አዳዲስ አባላትን ለመቀበል እና ጡረታ የሚወጡትን ክብር ለመስጠት የትምህርት ቦርድ የቃለ-መሃላ ሥነ ሥርዓት ዲሴምበር 2 ይካሄዳል ።

ዲሴምበር 2 በሚካሄደው የቃለ-መሃላ ሥነ ሥርዓት ላይ የትምህርት ቦርድ ሶስት አዳዲስ አባላትን በይፋ ይመድባል እና የሚሰናበቱ አባላት ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና ይሰጣል። 

ሪታ ሞንቶያ፣ ላውራ ስቱዋርት እና ናታሊ ዚመርማን ኖቬምበር ላይ ለቦርዱ ተመርጠዋል። ሞንቶያ ተለይቶ የተቀመጠ የስራ መደብ የሌላቸው ሙሉ አባል በመሆን ቦርዱን ተቀላቅለዋል፣ ስቴዋርት ዲስትሪክት 4ን ይወክላሉ እና ዚመርማን ዲስትሪክት 2ን ይወክላሉ። ዲሴምበር 2 በሚካሄደው ዝግጅት ላይ በይፋ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙ ሲሆን የመጀመሪያ የቢዝነስ ስብሰባቸው ዲሴምበር 5 ይሆናል።

እያንዳንዳቸው በቦርድ ውስጥ ለ12, ለስምንት፣ እና ለአራት ዓመታት ያገለገሉት ተሰናባች የቦርድ አባላት ረቤካ ስሞንድሮቭስኪ፣ ሼብራ ኢቫንስ፣እና ሊን ሃሪስ ያበረከቱት አስተዋፅዖም በዲሴምበር 2 ሥነ ሥርዓት ላይ እውቅና ተሰጥቶ የሚከበር ይሆናል።  

የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓቱ ሰኞ ዲሴምበር 2፣ 4፡00 p.m ላይ በ15 W. Gude Drive ይከናወናል እና ሥነ ሥርዓቱም ለህዝብ ክፍት ይሆናል። እንዲሁም MCPS ድረገጽ ላይ በቀጥታ ይሠራጫል። 

ቦርዱ ዲሴምበር 5 በሚካሄደው የቢዝነስ ስብሰባ ላይ ኦፊሰሮችን ይመርጣል እና የኮሚቴ ስራዎችን/አሳይመንቶችን ያፀድቃል።

ከትምህርት ቦርድ የተላከ የምስጋና መልእክት፡ በዚህ የታንክስጊቪንግ በዓል ስለማህበረሰብ ድጋፍ ማሰላሰል

ስለምናመሰግነበት ነገር ሁሉ ቀም ብለን ስናሰላስል፣ በተለይ ደግሞ ማህበረሰባቸው ላሳየን የማያወላውል ድጋፍ አመስጋኞች ነን። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች በት/ቤቶቻቸው እና በአጠቃላይ በMCPS ስኬት ላይ በጥልቅ ይሳተፋሉ። ለተማሪዎቻችን እና ለሰራተኞቻችን ትሟገታላችሁ፣ ይህም በየጊዜው እንድናሻሽል እና የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ያነሳሳናል። ትርጉም ያላቸው ዝግጅቶች፣ በዓላት እና የተማሪ ስኬት ማሳያዎች አካል እንድንሆን ተቀብላችሁ ታስተናግዱናላችሁ።

እንደዚህ ባለ ንቁ እና ብዝሃነት ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ በትምህርት ቦርድ ውስጥ ማገልገል ክብር እና እድል ነው።

ለሁላችሁም አስደሳች እና ሰላማዊ የታንክስጊቪንግ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ዲሴምበር 2, ሰኞ - የቦርድ አባል ቃለ-መሀላ መፈጸሚያ ፕሮግራም

  • ዲሴምበር 5, ሀሙስ - የቢዝነስ ስብሰባ

አጀንዳዎችን፣የስብሰባ ግብአቶችን ለመከታተል በቀጥታ ስርጭት ወይም የተቀዳ የስብሰባ ውይይት ለመመልከት የእኛን ድረ ገጽ ይጎብኙ።

የመሳተፍ እድሎች

ማህበረሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍ እና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።

ግንኙነትዎን ይቀጥሉ

በፌስቡክ እና X  ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org