እንግሊዝኛ/English፣ / ስፓንሽኛ/español፣ / ቻይንኛ/中文 / ፈረንሳይኛ/français፣ / ፖርቹጋልኛ/Português፣ / ኮርያንኛ/한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt፣ / አማርኛ/Amharic።
የትምህርት ቦርድ የታጨቀ አጀንዳ የበዛበትን ሣምንታዊ የሥራ ስብሰባ ዲሴምበር 5 አጠናቋል። የሥራ ስብሰባው የመጀመሪያ ተግባር አዲስ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት መምረጥ ነበር። ቦርዱ በበርካታ የሥራ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል፣ ከሱፐርኢንተንደንቱ የተሻሻለ ወቅታዊ የመግቢያ እቅድ ተቀብሏል፣ እና ከሱፐርኢንተንደንቱ የቀረበለትን የበጀት ዓመት 2026 የስራ ማስኬጃ በጀት ዝርዝር ተመልክቷል።
ይሄኛው የ 2024 የቦርዱ የመጨረሻ የስራ ስብሰባ ነው። የዊንተር/የክረምቱን ዕረፍት እና የበዓል ሰሞን እየተቃረብን ስለሆነ "መልካም እና ጤናማ የበዓል ወቅት ይሁንላችሁ" በማለት ቦርዱ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
ጁሊ ያንግ/Julie Yang፣ ከዲስትሪክት 3፣ የዲሴምበር 5 የሥራ ስብሰባን በፕሬዝዳንትነት የመሩ ሲሆን፣ ይህም የኦፊሰሮችን የሥራ ኃላፊነት ኦፊሴላዊ ሽግግር መከናወኑን ያመለክታል። ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን/Grace Rivera-Oven፣ ከዲስትሪክት 1፣ የምክትል ፕሬዚዳንቱን ሚና ይዘዋል።
"የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ሆኖ ማገልገል ትልቅ ክብር ነው" ሲሉ ወይዘሮ ያንግ ገልፀዋል። “ቦርዱ የትምህርት ዳቦ-እና-ቅቤ ስጋት ቤተሰቦቻችን በእውነት የሚጨነቁበት ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል። በተማሪዎቻችን፣ በሰራተኞቻችን እና በቤተሰቦቻችን የእለት ተእለት ተግባራዊ ክንውኖች ላይ እናተኩራለን።
በተጨማሪም ቦርዱ አዲስ የኮሚቴ አባላትንም አጽድቋል። ከዲሴምበር 5 ጀምሮ የቦርድ ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ናቸው፦
የፊስካል ማኔጅመንት ኮሚቴ፣ በካርላ ሲልቬስትሬ/Karla Silvestre የሚመራ ሲሆን፦ ናታሊ ዚመርማን ( Natalie Zimmerman)፣ ላውራ ስቲዋርት (Laura Stewart) እና ፕራኔል ሱቫርና (Praneel Suvarna) በአባልነት ያገለግላሉ።
የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴ በጁሊ ያንግ (Julie Yang) የሚመራ ሲሆን ካርላ ሲልቬስትሬ (Karla Silvestre)፣ ብሬንዳ ወልፍ (Brenda Wolff) እና ፕራኔል ሱቫርና (Praneel Suvarna) በአባልነት ያገለግላሉ።
የልዩ ትኩረት ማህበረሰብ ኮሚቴ፣ በግሬስ ሪቬራ-ኦቨን (Grace Rivera-Oven) የሚመራ እና ሪታ ሞንቶያ (Rita Montoya) እና ላውራ ስቲዋርትን (Laura Stewart) አባል ሆነው ያገለግላሉ።
የስትራቴጂክ እቅድ ኮሚቴ፣ በብሬንዳ ወልፍ (Brenda Wolff) የሚመራ እና ናታሊ ዚመርማን (Natalie Zimmerman) እና ሪታ ሞንቶያ (Rita Montoya) በአባልነት ያሉበት ነው።
ቦርዱ በማህበረሰብ ግንኙነት ማዳበር እና በተሳትፎ ላይ ያተኮረ ቋሚ አማካሪ ኮሚቴ በመሰየም የማህበረሰብ ግንኙነቶችን የማጠናከር እድል መኖሩን ተመልክቷል። በየአመቱ ኮሚቴው የማህበረሰብ ግንኙነትን እና ተሳትፎን በማሻሻል ላይ የታለመ አንዳንድ ቁልፍ ርዕሶችን ያነሳል። ይህ በ 2019 የተቋቋመውን የግንኙነት እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ኮሚቴን ይተካል። አዲሱ አማካሪ ኮሚቴ በሂደቱ ውስጥ ንቁ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችላቸው የማህበረሰብ አባላትን ያካትታል። ምክትል ፕሬዚዳንቷ በኮሚቴው ውስጥ የቦርዱ ተወካይ ሆነው ያገለግላሉ። አዲሱ አማካሪ ኮሚቴ በመጀመሪያው የሚያነሳው ርዕስ ስለመጪው የወሰን ማካለል ጥናት ነው። የኮሚቴውን ስራ በተመለከተ ተጨማሪ ዝርዝሮችን በቅርቡ እናጋራለን።
ቦርዱ እና አስተዳደሩ በየደረጃው ባሉ የመንግስት እርከኖች ባሉት ችግሮች እና በገንዘብ ውስንነት ምክንያት ዘንድሮ የበጀት አጠቃቀምን በተመለከተ ከባድ ውሳኔዎች ይጠብቃቸዋል። ይህም ቢሆን፣ የተማሪዎችን ውጤት በሚያሻሽሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ለማተኮር ቁርጠኞች ነን። የዲስትሪክቱን ግቦች ለማሳካት የረጅም ጊዜ እቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ቦርዱ እና ዶ/ር ቴይለር ይስማማሉ።
2026 በጀት የሚከተሉትን እንደሚያካትት መጠበቅ እንችላለን፦
አገልግሎቶችን እና ግብዓቶችን ይበልጥ ወደ ትምህርት ቤቶች ማዞር
የተደራረቡ ቢሮክራሲዎችን መቀነስ
በፊስካል እና በፊሲካል መሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስትመንት ማድረግ
የወደፊት እድገት ላይ ያተኮረ መሠረት መጣል
ዶ/ር ቴይለር የ 2026 በጀት ዓመት የሥራ ማስኬጃ በጀት ዲሴምበር 18 ከቀኑ 6፡00 ፒ.ኤም ላይ ያቀርባሉ።
ህብረተሰቡ በሚከተለው አኳኋን በሂደቱ እንዲሳተፍ ቦርዱ ይጋብዛል፦
ጃንዋሪ 14፣ 10፡00 am - የስራ ማስኬጃ በጀት የስራ ክፍለ ጊዜ
ጃንዋሪ 16, 6:00 p.m. - የሥራ ማስኬጃ በጀት የሕዝብ አስተያየት የሚቀርብበት ክፍለጊዜ
ጃንዋሪ 23፣ 10፡00 a.m. - የስራ ማስኬጃ በጀት የስራ ክፍለ ጊዜ
ጃንዋሪ 27, 6:00 p.m. - የሥራ ማስኬጃ በጀት የሕዝብ አስተያየት የሚሰጥበት ክፍለጊዜ
ጃንዋሪ 30፣ 10፡00 a.m. - የስራ ማስኬጃ የበጀት ስራ ክፍለ ጊዜ (ካስፈለገ)
ፌብሩዋሪ 4፣ እኩለ ቀን - ከኦፕሬቲንግ ባጀት በጊዜያዊነት የሚፀድቅበት የሥራ ስብሰባ
የቀረበውን የበጀት ዝግጅት በመመልከት ዝርዝሩን ይወቁ።
ቦርዱ 2025-2026 መደበኛ እና የኢኖቬቲቭ የትምህርት አመት የቀን መቁጠሪያዎችን አጽድቋል። መደበኛው የቀን መቁጠሪያ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
181 የትምህርት ቀናት
የተማሪዎች ሽግግር ቀን - ሰኞ፣ ኦገስት 25, 2025
ለሁሉም ተማሪዎች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን - ማክሰኞ፣ ኦገስት 26, 2025
የዊንተር/የክረምት ዕረፍት (ለተማሪዎች) - ዲሴምበር 24, 2025 እስከ ጃንዋሪ 4, 2026
የስፕሪንግ ዕረፍት (ለተማሪዎች) - ማርች 28, 2026 እስከ ኤፕሪል 6, 2026
የመጨረሻው የትምህርት ቀን - ጁን 17, 2026
የተማሪዎች ሽግግር ቀን 2025-2026 የትምህርት አመት ላይ አዲስ የተጨመረ ነው። ግቡ በመዋዕለ ህጻናት (K)፣ 6ኛ፣ እና 9ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች፣ እንዲሁም 3ኛ ክፍል ተማሪዎች 3ኛ እስከ 5ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ወደ ትምህርት ቤቱ ወይም ወደ MCPS አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እና አዲሱን የትምህርት ቤት አካባቢያቸውን እንዲለማመዱ ለማድረግ ነው።
የቀን መቁጠሪያውን የማደስ ሂደት የተቀየሰው MCPS በት/ቤቶቻችን ውስጥ ላሉ ሰዎች ሁሉ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ምቹ አካባቢን በማዘጋጀት የትምህርት ቦርድ ግቦችን ለመደገፍ ነው። ሰራተኞች የማህበረሰቡን ፍላጎቶች እና ምርጫዎች እንዲረዱ በማገዝ ረገድ ከማህበረሰብ የተገኘው አስተያየትና ግብአት የቀን መቁጠሪያውን በማዘጋጀት አንጻር ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።
ስለ ትምህርት አመቱ የቀን መቁጠሪያ የበለጠ ለማወቅ፣ እና ስለ እቅዱ ሁሉንም አስፈላጊ ቀናት ጭምር፣ የዝግጅት አቀራረቡን ይመልከቱ።
ዶ/ር ቴይለር E3 የመግቢያ እቅድ - ስለ ተሳትፎ፣ ግምገማ፣ እና ተሳትፎን ስለማጎልበት የመጀመሪያዎቹን ስድስት ወራት ሪፖርት አቅርበዋል። ዶ/ር ቴይለር “የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን (MCPS) ወደፊት ለማራመድ በመሠረታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር አለብን” ሲሉ ገልፀዋል። እነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ዶ/ር ቴይለርያቀረቡትን ሪፖርት ይመልከቱ።
ቦርዱ የሚከተሉትን አፅድቋል፦
ለ ክራውን/Crown እና ውድዋርድ/Woodward ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፕሮጀክቶች FLO Analytics መጪውን የወሰን ጥናቶችን እንዲያከናውን መርጧል።(የዝግጅት አቀራረብ)
የቦርድ ፖሊሲ GCB,የሰራተኞች የስነምግባር ጉድለት ክሶች ምርመራ፣ በፖሊሲው ላይ የህዝብ አስተያየት መስጫ (የቀረበ ቦርዱ የወሰደው ጊዜያዊ እርምጃ።)
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የአስተዳዳሪዎች እና የርእሰ መምህራን ማህበር/የሞንትጎመሪ ካውንቲ የንግድ እና ኦፕሬሽን አስተዳዳሪዎች ስምምነት 2023-2025 የትምህርት አመት ውል (ተዘጋጅቶ የቀረበ) ማሻሻያ።
አጀንዳዎችን እና የስብሰባ ውይይቶችን ለመከታተል በቀጥታ ስርጭት ወይም የተቀዳ የስብሰባ ውይይት ለመመልከት የእኛን ድረ ገጽ ይጎብኙ።
ዲሴምበር 10 - የስትራቴጂክ እቅድ ኮሚቴ ስብሰባ
ጃኑዋሪ 9 - የሥራ ስብሰባ
ማህበረሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍ እና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org
ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org