ለረጅም ጊዜ በሕክምና ለሚቆዩ ተማሪዎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተቀናጀ የትምህርት ፕሮግራም ማመልከቻ አሁን ይገኛል።

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ለረዥም ጊዜ በህክምና ለሚቆዩ ተማሪዎች አዲሱየተቀናጀ የትምህርት ፕሮግራም የማመልከቻ ቅጽአሁን ተዘጋጅቷል። ይህ ፕሮግራም በተቀናጀ እና ባልተቀናጀ ቨሩዋል የትምህርት አውድ በህክምና ምክንያት በአካል ትምህርት ቤት ተገኝተው ለመማር እንደማይችሉ ፈቃድ ባለው የህክምና ባለሙያ ለተረጋገጠላቸው ተማሪዎች፣ እስከ አንድ አመት ድረስ አጠቃላይ ትምህርታዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። 

ቤተሰቦች ማመልከቻውን ከዛሬ ኦክቶበር 1, 2024 ጀምሮ በኦንላይን ማግኘት ይችላሉ። ፍላጎት ያላቸው በተቻለ ፍጥነት እንዲያመለክቱ እናበረታታለን። ፕሮግራሙ ኖቬምበር 6, 2024 በይፋ ይጀምራል።

ከፕሮግራሙ ምን እንደሚጠበቅ የሚያሳዩ አንዳንድ ፍንጮችን እነሆ።

  • ተማሪዎች በየእለቱ በተለያዩ ክፍለጊዜዎች በሳምንት ቢያንስ ለአራት ቀናት የተቀናጀ ትምህርት ያገኛሉ።

  • በሚቻልበት ጊዜ በመደበኛው የትምህርት ቀን ትምህርት የሚሰጥ ሲሆን፣ነገር ግን የተቀናጀ ትምህርት የሚሰጠው ከትምህርት ቀን ውጭ ሊሆን ይችላል።

  • ልዩ ትምህርት፣ሰክሽን 504፣እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማዳበር ትምህርት አገልግሎቶች ይሰጣሉ።

  • የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች (K እስከ 5ኛ ክፍል) እንግሊዝኛ/የቋንቋ ስነጥበብ፣ ሂሳብ፣ ሳይንስ፣ እና ማህበራዊ ጥናት/ሶሻል ስተዲስ የመሳሰሉ ዋና ዋና ትምህርቶች ሳምንታዊ የተቀናጁ ትምህርቶችን ያገኛሉ።

  • የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች (6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል) ዋና ዋና ትምህርቶችን እና የተወሰኑ ተመራጭ ትምህርቶችን ሳምንታዊ የተቀናጀ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ይኖራቸዋል። 

  • የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመመረቅ በሚያስፈልጉ ዋና ዋና ኮርሶችን ከተወሰነ የኮርስ ምርጫ ጋር የተቀናጀ ትምህርት ይሰጣቸዋል። አብዛኛው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተቀናጀ ትምህርት የሚሰጠው ከመደበኛ የትምህርት ሰዓት ውጭ ነው።

ጠቃሚ ማሳሰቢያዎች

  • አመልካቾች የተሞላ የማመልከቻ ቅጽከህክምና ባለሙያ የተሠጠ የህክምና ማረጋገጫ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

  • ተማሪዎች በሜሪላንድ ስቴት ውስጥ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚኖሩ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

  • እድሜአቸው ከ 12 አመት በታች ያሉ ተማሪዎች በትምህርት ሰአት የጎልማሳ ሰው ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል። ዕድሜያቸው 12 አመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተማሪዎችም የወላጅ ቁጥጥር እንዲደረግላቸው ይመከራል።

  • በሌሎች ቋንቋዎች የተተረጎመ የዚህ ማመልከቻ ቅጂ በቅርቡ ይኖራል።

ለዚህ ፕሮግራም የተፈቀደላቸው ተማሪዎች የህክምና አገልግሎት በሚሰጣቸው ባለሙያ ሲረጋገጥላቸው ወደ መደበኛ ትምህርት ቤታቸው ሊመለሱ ይችላሉ።

የማመልከቻ ቅጹን እዚህ ማግኘት ይችላሉ።


M. Brian Hull, Chief Operating Officer Montgomery County Public Schools


በዚህ አድራሻASKMCPS@mcpsmd.orgኢሜል ይላኩልን፦