እንግሊዝኛ/English፣ / ስፓንሽኛ/español፣ / ቻይንኛ/中文 / ፈረንሳይኛ/français፣ / ፖርቹጋልኛ/Português፣ / ኮርያንኛ/한국어 / ቬትናምኛ/tiếng Việt፣ / አማርኛ/Amharic።
ውድ የMCPS ቤተሰቦች፣
ይህንን የምጽፈው በመጪው የፌደራል አስተዳደር ቃል በተገባላቸው የኢሚግሬሽን እና ከሀገር የማስወጣት ጥረቶች ዙሪያ እየተካሄደ ባለው አገርአቀፋዊ ውይይት ምክንያት በማህበረሰባችን ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የማሳመን ንግግር እና ጭንቀቶች በተመለከተ ስጋቴን እና አንዳንድ መረጃዎችን ለማካፈል ነው። ይህ የፖሊሲ ክርክር ብቻ እንዳልሆነ ማረጋገጥ እፈልጋለሁ; ለብዙዎች፣ ስለ ወደፊቱ ጊዜ እርግጠኛ አለመሆንን እና ስጋትን የሚፈጥር ጥልቅ የሆነ የግል ጉዳይ ነው።
ለሁሉም ቤተሰቦቻችን፣ እባክዎን ይህንን ይወቁ፡ እርስዎ የMCPS ቤተሰብ አካል ነዎት ትምህርት ቤቶቻችን ማንኛውም ልጅ— የኢሚግሬሽን ሁኔታ ምንም ይሁን ምንም—መልካም አቀባበል የሚደረግለት፣ የሚከበርበት፣ እውቅና የሚሰጥበት፣ የሚከበርበት፣ እና የሚወደድበት ደህንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎች ናቸው እና ሆነውም ይቀጥላሉ።እያንዳንዱ ተማሪ በማንነቱ እንዲኮራ እንፈልጋለን፣ እና በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉትን በርካታ ባህሎች እናከብራለን። ቤተሰብዎን በት/ቤቶቻችን ሁልጊዜ በደስታ እንቀበላቸዋለን፣ እና አንድ ላይ፣ MCPSን የበለጠ ጠንካራ እናደርጋለን።
ትምህርት ቤቶቻችንን ለሁሉም ተማሪ እና ቤተሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ እና እንግዳ ተቀባይ እንዲሆን ማድረግ ከምንሰራቸው በጣም አስፈላጊ ስራዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው ምክንያቱም ጥሩ የመማር ተሞክሮዎችን ለመፍጠር ይረዳል። ተግዳሮቶች በሚፈጠሩበት ጊዜ፣ እንድናስብ፣ እንድንማር፣ እንድናድግ እና እንድናሻሽል ጠቃሚ እድሎችን ይሰጡናል።
ግልጽ ለማድረግ እና ለማጽናናት/ማረጋገጫ ለመስጠት፣ የእኛን የደህንነት፣ የማካተት እና በማህበረሰባችን ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ተማሪ እና ቤተሰብ ክብር የመስጠት እሴቶቻችንን የሚያንፀባርቁ አንዳንድ ጠቃሚ ማስታወሻዎች ከዚህ በታች ተቀምጠዋል።
ትምህርት ቤቶች ደህንነታቸው የተጠበቀ ቦታዎች ናቸው፡ ት/ቤቶች ተማሪዎች ደህንነት እንዲሰማቸው፣ የመደግፍ ስሜት እንዲሰማቸው፣ እና በትምህርታቸው ላይ ትኩረት ለማድረግ ነጻነት እንዲሰማቸው የሚያደርጉ ቦታዎች ናቸው። {የፌደራል መመሪያ ትምህርት ቤቶች መነካት የሌለባቸው ዘርፎች/sensitive areas እንደሆኑ ይገነዘባል፣ ይህም ማለት በስደተኞች ባለስልጣናት የሚወሰዱህግን የማስፈጸም እርምጃዎች በአጠቃላይ በት/ቤቶች ውስጥ ወይም በትምህርት ቤት ይዞታዎች ላይ አይፈቀዱም።
ትምህርትን ማግኘት መብት ነው፡ትምህርት፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ ለሁሉም ልጆች የተረጋገጠ መሠረታዊ መብት ነው። የU.S. ሕገ መንግሥት እና 1982 ጠቅላይ ፍርድ ቤት በPlyler v. Doe ላይ የሰጠው ውሳኔ እያንዳንዱ ልጅ በሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ የማደግ/የመጎልበት እድል እንዳለው ያረጋግጣል፣ ይህም ለእኩልነት እና ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ላይ ያለንን ቁርጠኝነት አጽንኦት ይሰጣል።
MCPS ስለኢሚግሬሽን ሁኔታ አይጠይቅም፡እያንዳንዱ ቤተሰብ ክብር እና የግል ገመናው እንዲከበርለት ማድረግ ይገባዋል። MCPS ስኢሚግሬሽን ሁኔታ አይጠይቅም ወይም የቤተሰብ መረጃን ለኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ሪፖርት አያደርግም። በተጨማሪም የMontgomery County ፖሊስ የፌደራል ኢሚግሬሽን ህጎችን አያስፈጽምም። እነዚህ ልምዶች ለሁሉም ቤተሰቦች እንግዳ ተቀባይ አካባቢን ለመፍጠር ይረዳሉ።
ትንኮሳን ወይም ማሸማቀቅን በምንም መልኩ አለመታገስ፡የደግነት፣ የመከባበር እና የደህንነት ባህልን ለማዳበር በቁርጠኝነት እንሰራለን። MCPS የኢሚግሬሽን ሁኔታን ጨምሮ፣ በማንኛውም ምክንያት ማሸማቀቅን ትንኮሳን፣ ወይም ማስፈራራትን አይታገስም። አንድ ተማሪ እንደዚህ አይነት ተግባር ካጋጠመው፣ እንደ የትምህርት ቤት አስተዳዳሪ ላለ ታማኝ አዋቂ ሰው እንዲያሳውቁ ይበረታታሉ።
እንዲሁም ከልጅዎ ትምህርት ቤት ጋር ግንኙነትዎ እንዲቀጥል ማድረግ አስፈላጊ ነው። በድንገተኛ/በአስቸኳይ ጊዜ ወይም ጠቃሚ/አስፈላጊ ወቅታዊ መረጃዎች ለማጋራት እርስዎን በፍጥነት ማግኘት እንደምንችል ማረጋገጥ እንፈልጋለን። እርስዎን የምናገኝበት አድራሻዎ ምስጢራዊነቱ የተጠበቀ ነው፣ ለማንም አይጋራም፣ እና የልጅዎን ደህንነት ለመደገፍ ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል። ይህ መረጃ በParentVUE ወይም በዚህ ቅጽ አማካኝነት ወቅታዊ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል።
ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ፣ እንቅስቃሴዎችን/ተግባሮችን እንዲቀላቀሉ፣ እና ያለ ፍርሃት ከጓደኞቻቸው ጋር ጊዜ እንዲያሳልፉ እናበረታታለን። እርስዎ የማህበረሰባችን ወሳኝ አካል ነዎት፣ እና እኛ እዚህ ያለነው እርስዎ እንዲማሩ፣ እንዲያድጉ እና ስኬታማ እንዲሆኑ ለመርዳት ነው።
እርስዎ ወይም ልጅዎ ስጋቶች/የሚያሳስቡ ጉዳዮች ካሎዎት ወይም ድጋፍ ካስፈለግዎት እባክዎን የእርስዎን የትምህርት ቤት ሰራተኞች ያግኙ። በጋራ በመሆን፣ MCPS ለሁሉም ቤተሰቦች እንግዳ ተቀባይ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ሆኖ መቀጠሉን እናረጋግጣለን።
ስለ እምነትዎ እናመሰግናለን።
ከልባዊ ሠላምታ ጋር
Thomas W. Taylor, Ed.D., M.B.A.
Superintendent
Montgomery County Public Schools
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org