የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት አመት ወደ ጁን 17 በአንድ ቀን ተራዝሟል። በዚህ መሠረት የትምህርት ዓመቱ የመጨረሻ ሶስት ቀናት ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀናት ይሆናሉ።

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ

የጸደይ/የስፕሪንግ ወቅት መምጣቱ እና የሙቀት መጠን እየጨመረ መሄዱን ማየት በጣም ያስደስታል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንዳንድ ጊዜ ማህበረሰባችንን የበረዶ ክምችት እና ቅዝቃዜ ያጋጥመን እንደነበር ይታወሳል። በዚያ ከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የትምህርት ቤቶች መዘጋት፣ ዘግይቶ መክፈት፣ እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ መካሄድ የነበረባቸውን እንቅስቃሴዎች መሰረዝ ግዴታ ነበር። በእርግጥ ሁኔታው ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች፣ እና ለቤተሰቦች ሁሉ የሚከብድ እና የሚያበሳጭ እንደነበር ይታወቃል።  

በተፈጠረው አራት ጊዜ የት/ቤቶች መዘጋት ምክንያት እና የስቴቱን 180 የትምህርት ቀናት መስፈርት ለማሟላት፥ የትምህርት አመቱ አሁን ወደ ማክሰኞ፣ ጁን 17 የተራዘመ ሲሆን፤ የመጨረሻዎቹ ሶስት የትምህርት ቀናት ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀናት ይሆናሉ። ይህ መርሐግብር ሰራተኞቻችን የዓመቱን ስራ ለማጠናቀቅ ጊዜ ይሰጣቸዋል። 

ለማስታወስ ያህል፦ ሰኞ፣ ጃንዋሪ 6, 2025፣ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 7, 2025፣ እሮብ፣ ጃንዋሪ 8, 2025 እና እሮብ፣ ፌብሩዋሪ 12. ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ተዘግተው ነበር። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2024–2025 የትምህርት አመት 182 የትምህርት ቀኖች ያሉት ሲሆን ይህም በሜሪላንድ ስቴት ከተደነገገው ቢያንስ 180 የትምህርት ቀናት በሁለት ቀን ብልጫ አለው። በዚህ መሠረት ጃንዋሪ 6 እና 7 የተዘጉት ቀናት የትምህርት ቀን መቁጠሪያችንን አይነኩትም። ቀደም ሲል እንደተገለጸው፣ ጃንወሪ 8 በመዘጋቱ ምክንያት የትምህርት አመቱ ወደ ጁን 16 ተራዝሞ ነበር፣ ፌብሩዋሪ 12 አንድ ተጨማሪ የትምህርት ማካካሻ ቀን ተይዞ ነበር፥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ቀሪውን ቀን የማሟላት መስፈርት እንዲቀር ለሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት ጥያቄ ቢያቀርብም ጥያቄው ተቀባይነት አላገኘም።

ስለዚህ አሁን የመጨረሻ የትምህርት ቀን ማክሰኞ፣ ጁን 17 ስለሚሆን አርብ፣ ጁን 13፣ ሰኞ፣ ጁን 16 እና ማክሰኞ፣ ጁን 17 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀናት ይሆናሉ። ይህ ለውጥ የተደረገበት ምክንያት በትምህርት አመቱ የመጨረሻ ቀናት ሰራተኞች መርሃ ግብሮችን እና የሴሚስተር የመጨረሻ ክፍለጊዜ ሪፖርት እንዲያጠናቅቁ እና የሙያ እድገት መስፈርቶችን ለማከናወን አስፈላጊ ስለሆነ ነው። በዚህ መሠረት ለተማሪዎች እና ለአስተማሪዎች የመጨረሻው የትምህርት ቀን ማክሰኞ፣ ጁን 17 ነው። የትምህርት አመቱ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ለመርዳት፣የማካካሻ/የማሟያ ስራዎች በሙሉ ከዓርብ፣ ጁን 13 በፊት ለመምህራን እንዲቀርቡ እንጠይቃለን። ምንም እንኳን ሙሉ በሙሉ ያልተጠበቀ ባይሆንም ይህ ለውጥ መሆኑን እናውቃለን፣ እና ቤተሰቦች አስቀድመው እቅድ አውጥተው ሊሆን እንደሚችልም እንገነዘባለን።

የፀደይ/የስፕሪንግ እረፍት በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል። ይህንን ጊዜ ለመዝናናት፣ ለመነቃቃት፣ ከጓደኞች እና ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ፣ እረፍት ለማድረግ እና ራስን ለማስደሰት እንድትጠቀሙበት እናበረታታለን።

Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ


በዚህ አድራሻ ኢሜል አድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org