ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ
አገልግሎታችን እንዴት ነው? እውነተኛ መሻሻል ሊመጣ የሚችለው የእርስዎን ምክር በማድመጥ ስለሆነ የሚሰጡንን ምክረ ሀሳብ መስማትና ማወቅ እንፈልጋለን።
ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች የሚጠቅሙ የአገልግሎት አሰጣጥ ለውጦችን ለማድረግ የትምህርት ቤት አጠቃላይ የዳሰሳ ጥናት ቅጽ አሻሽለን አቅርበናል።
ከተማሪዎች እና የት/ቤት ደህንነት እና ግንኙነት እስከ መማር እና ማስተማር – የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አጠቃላይ የትምህርት አገልግሎት አሰጣጥን መቃኘት አድርገው ያስቡት። በደንብ የሚሰራውን እና ምን ማሻሻል እንደምንችል በመረዳት፣ ለሁሉም ተማሪዎቻችን የበለጠ አጋዥ እና አሳታፊ ሁኔታዎችን መፍጠር እንችላለን።
ወላጅ፣ አሳዳጊ፣ ወይም የተከበሩ የማህበረሰባችን አባል ቢሆኑ፣ እርስዎ የሚያጋሩን ልዩ አመለካከት፣ይህን ሂደት ለማስፈፀም ወሳኝ የሆነ ግንዛቤ ይሰጠናል።
ይሄኛው እንደተለመደው አይነት ረጅም የዳሰሳ ጥናት አይደለም። ---አድርገናል፦
የእርስዎን ጊዜ ለመቆጠብ ጥያቄዎቹን አጭር፡ አድርገናል።
ጥልቅ ሀሳብ፡ የበለጠ ዝርዝር ግብረመልስ ማካተት እንዲችሉ ጥያቄዎቹ ክፍት ተደርገዋል።
ተግባር ተኮር፡ከዚህ ሠመር ጀምሮ ማሻሻያዎችን በማድረግ የመጀመሪያ እርምጃዎች ላይ እውነተኛ ለውጥ መተግበሩን እና እድገቱን ለመከታተል በዓመት ሁለት ጊዜ እናካሂዳለን።
የሁሉም ተሳትፎ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። ከእርስዎ ካላዳመጥን፣ የምናገኘው ምስል የተሟላ አይሆንም፣ እና መፍትሄዎቹም የተሟሉ አይሆኑም።
የትምህርት ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ የዳሰሳ ጥናት ማለት ነገሮች እንዴት እንደሆኑ ማወቅ ብቻ አይደለም — እኛ ተባብረን በጋራ እንዴት እንደምናሻሽል መረዳት/ማወቅ ማለት ነው።
የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ሲመልሱ የሰጡትን ግብረ መልስ ከት/ቤቱ ጋር ማገናዘብ እንድንችል የልጅዎ መታወቂያ ቁጥር እን ዲፅፉበት ያስፈልጋል። የተማሪዎን የመታወቂያ ቁጥር (student ID number) ParentVue ያገኛሉ።
ቶማስ ቴለር (ዶ/ር)
ሱፐርኢንተንደንት
Thomas Taylor
Superintendent
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org