ሰኞ፣ ኦገስት 25 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተማሪዎች የሽግግር ቀን ያካሂዳሉ፤ ወደ አዲስ የትምህርት ደረጃ ለሚሸጋገሩ ወይም ወደ አዲስ የት/ቤት ህንፃዎች ለሚገቡ ተማሪዎች የሚያደርጉትን ሽግግር ለማቃለል ቀኑን ሙሉ ትምህርት የማይሰጥበት የትምህርት ቤት ክንውን ነው። የትምህርት ቤትን ውሎ ለመሞከር ጥሩ ቀን ነው።
ተማሪዎች አዲሱን ትምህርት ቤታቸውን በመቃኘት ይጀምራሉ። ከማክሰኞ፣ ኦገስት 26 ኦፊሴላዊ የትምህርት መጀመሪያ ቀን በፊት ርእሰ መምህራንን እና አስተማሪዎችን ያገኛሉ፣ ህንፃዎችን ይጎበኛሉ፣ የስራ ሁኔታዎችን ይቃኛሉ፣ እና ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ/ይገናኛሉ።
ወደ መዋእለ ህጻናት፣ 6ኛ ክፍል እና 9ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች በሙሉ ይሳተፋሉ።
ወደ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መጪዎቹ 3ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች (3ኛ እስከ 5ኛ ክፍል)።
ለ MCPS አዲስ የሆኑ ወይም ወደ አዲስ ትምህርት ቤት የተዛወሩ ማናቸውም ተማሪዎች።
አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ የትምህርት ቤት ጉብኝት፣ ከአስተዳዳሪዎች እና ከአስተማሪዎች ጋር መገናኘት እና ሰላምታ መለዋወጥ፣ አይን ገላጭ ተግባሮችን ይመለከታሉ፣ የተለዩ ነገሮችን ያጤናሉ።
መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ ከፕሮግራሞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ፣ ሎከሮቻቸውን ይለማመዳሉ፣ ቴክ መግቢያዎችን፣ የአትሌቲክስ እና የክለብ ቅድመ እይታ እና በተማሪዎች-የሚመሩ ጉብኝቶችን ያደርጋሉ።
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፡ ከፕሮግራሞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ፣ የክፍል ሽግግሮችን ይመለከታሉ፣ ከአትሌቲክስ እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ የሚከናወኑ ትዕይንቶችን እና የተማሪ መብቶች እና ኃላፊነቶችን የሚመለከቱ መመሪያዎች ጋር ይተዋወቃሉ።
ለሁሉም ደረጃዎች፡ት/ቤት የመድረሻ/የመሰናበቻ ጊዜ፣ የዕለት ተዕለት ተግባራት አጠቃላይ እይታ፣ ስለ ስነምግባር ደንብ እና አማራጭ የወላጅ/አሳዳጊ መረጃ ክፍለ ጊዜዎች መግለጫ ይኖራል።
የአውቶቡስ ማቆሚያዎን ለማወቅ ይህ ጥሩ አጋጣሚ ነው። የትምህርት ቤት አውቶቡሶች በመደበኛው የመጀመሪያ ቀን መርሃ ግብር መሠረት ይሰራሉ - መርሃ ግብሩ እዚህ ይገኛል።
ምሳ በግዢ ይኖራል፣ ወይም ተማሪዎች የራሳቸውን ይዘው መምጣት ይችላሉ።
ከትምህርት ሠዓት በፊት እና በኋላ የልጆች እንክብካቤ የሚኖረው እንደየትምህርት ቤቱ ይለያያል - ለዝርዝሩ ትምህርት ቤትዎን ያነጋግሩ።
ስለ ሽግግር ቀን እና ስለ መጀመሪያው የትምህርት ቀን ተጨማሪ መረጃ ከትምህርት ቤትዎ እና ከ MCPS ይመልከቱ።
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org