MCPS 2024 ወደ ት/ቤት የመመለሻ አውደ ርዕይ ላይ ለመገኘት ቀኑን ያስታውሱ
ቅዳሜ፣ ኦገስት 24, 2024
ጠዋት 10 A.M. እስከ 1 P.M.
ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ወደ ት/ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ ላይ ተገኝተው አዲሱን የትምህርት አመት እንዲያስጀምሩ ተጋብዘዋል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ስርዓቱ እና የካውንቲ ፕሮግራሞች እንዲሁም ካውንቲው ስለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች፣ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎች፣ መዝናኛዎች፣ ነጻ የክትባት ክሊኒክ እና ሌሎችንም እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው።
አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road, Wheaton.
ነጻ መጓጓዣ አለ፡ MCPS ከዝግጅቱ ቦታ ወደሚከተሉት MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ደርሶ መልስ ነጻ የማመላለሻ አውቶቡሶችን ያቀርባል።
የመጀመሪያው ማመላለሻ አውቶቡስ/ሸትል ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች 9፡00 a.m. ይነሳል። እና የመጨረሻው ማመላለሻ አውቶቡስ ከዌስትፊልድ ዊተን 2 p.m. ላይ ይወጣል።
ማሳሰቢያ፦ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 26 ነው
የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ፎቷችሁን አጋሩ
ለህጻናት መዋዕለ ሕፃናት የመጀመሪያ ቀንም ሆነ ሲንየር ተማሪዎችም ቢሆኑ፣ የትምህርት የመጀመሪያ ቀን ምንጊዜም ልዩ ነው። የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀን ጊዜዎን በማጋራት ደስታ እንድንላበስ ያግዙን! ሰራተኞች፣ ወላጆች እና ተማሪዎች የሚወዷቸውን የት/ቤት የመጀመሪያ ቀን ቅጽበተ-ፎቶዎችን ሰኞ ኦገስት 26 እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። የተመረጡ ፎቶዎች ከሰኞ ጥዋት ጀምሮ በዲስትሪክቱ ድረ-ገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይጋራሉ። ፎቶ መስጠት ማለት MCPS ድረ ገጽ ላይ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎች ላይ እንደሚታተም ተስማምተዋል ማለት ነው። በኢሜል በመላክ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መለያ በመስጠት ፎቶ ማጋራት ትችላላችሁ።
MCPS በባህል ልውውጥ ፕሮግራም ከፊሊፒንስ የመጡ 42 የትምህርት ባለሙያዎችን ተቀብሏል
በዲስትሪክቱ ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተመደቡ J-1 ቪዛ ያላቸው 42 መምህራንን ያቀፈ ቡድን በዩ.ኤስ. ማስተማር የሚያስችል የባህል ልውውጥ ፕሮግራም አካል ነው።
Foreign Cultural Exchange Consultants, Inc ጋር በመተባበር ለእነዚህ የፊሊፒንስ ታዋቂ መምህራን የመኖሪያ ቤት እና ምግብ፣ የቤት እቃዎች፣ መጓጓዣ እና ደህንነትን የመሳሰሉ አስፈላጊ ነገሮችን በማዘጋጀት አጠቃላይ ድጋፍ ይሰጣቸዋል። ይህ ድጋፍ ያለምንም ጭንቀት የሽግግር ጊዜ እንዲኖራቸው ለማድረግ የታለመ ሲሆን ይህም ከመጀመሪያው የትምህርት ቀን ጀምሮ ተማሪዎቻችንን ለማስተማር በዝግጅት ላይ እንዲያተኩሩ ያስችላቸዋል። "Foreign Cultural Exchange Consultants, Inc." በተጨማሪም በማስተማር ሥራ ላይ ተሰማርተው የባህል ልውውጥ ለማድረግ ለመጡት አስተማሪዎች በዩ.ኤስ. በሚቆዩበት ጊዜ አወንታዊ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲያስችላቸው የገንዘብ እና የመረጃ ድጋፍ ይሰጣቸዋል።
የባህል ልውውጥ አስተማሪዎቹ የትምህርት ደረጃቸው እና የሥራ ልምዳቸው እየታየ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መምህራን ጋር በተመሳሳይ የክፍያ ሠንጠረዥ ይከፈላቸዋል። ለ MCPS መምህራን የሚሰጣቸውን ተመሳሳይ ጥቅማ ጥቅሞችም ያገኛሉ።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ማህበር (MCEA) ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዳኒሊ ዊልሰን/Danillya Wilson "እንደነዚህ ያሉ ፕሮግራሞች ለአዳዲስ አመለካከቶች በሮችን ስለሚከፍቱ በጣም አስፈላጊ ናቸው" በማለት አስረድተዋል ።
የልዩ ትምህርት ክፍት ቦታዎች ባለፈው ዓመት በተለይ ተግዳሮቶች ነበሩ። MCPS ይህንን አዲስ የአጋርነትና የወዳጅነት እድል በመጠቀም በዚህ አመት ቁጥሩን በእጅጉ መቀነስ ችሏል።
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org