እንኳን ወደ 2024-2025 የትምህርት አመት በደህና መጡ/መጣችሁ!
ወደ አዲሱ የትምህርት አመት እንኳን ደህና መጣችሁ ስንል የላቀ ደስታ ይሰማናል! ሰኞ፣ኦገስት 26 ወደ 160,000 የሚጠጉ ተማሪዎች የትምህርት አመቱን ለመጀመር በተከፈቱ በሮች ይገባሉ። MCPS የላቀ ትምህርት ለመስጠት ቁርጠኛ ስለሆነ ከትምህርት ቤተሰቦች እና ከማህበረሰቡ ጋር በአጋርነት በመስራት፣ለሁሉም ተማሪዎቻችን ወደ ብሩህ ተስፋ የሚያደርሳቸው የጥርጊያ መንገድ እናዘጋጃለን። ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ ምሽት ዝርዝርን ጨምሮ ወደ ትምህርት ቤት ስለመመለስ የመረጃ ምንጭ እንድትጎበኙ እናበረታታዎታለን።
የበዓል ቀናትን፣ የሙያ ማዳበር ቀናትን፣ እና ሌሎችንም ከትምህርት ቤት ካላንዳር/የቀን መቁጠርያ ያገኛሉ።
2024-2025 መደበኛ የትምህርት ዓመት ቀን መቁጠሪያ/ካላንደር
español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / ማርኛ
2024-2025 የኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤት ካላንደር (አርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ)
español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / ማርኛ
አመታዊ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደርዕይ - በመጪው ቅዳሜ፣ ኦገስት 24 ይካሄዳል።
ቅዳሜ፣ ኦገስት 24 ዓመታዊው MCPS ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ አውደ ርዕይ ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 1 p.m. በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ ማዕከል የሚካሄድ ስለሆነ ከእኛ ጋር ይቀላቀሉን። ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤቶች ስርዓትአቀፍ መረጃ እና ስለ ካውንቲ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች የሚያውቁበት ጥሩ ዝግጅት ስለሆነ አጋጣሚውን ይጠቀሙ። የቤተሰብ እንቅስቃሴዎች፣ሙዚቃ፣ መዝናኛዎች እና ስጦታዎች በነጻ ይቀርባሉ። የዚህ አመት አቅራቢዎች KID ሙዚየም፣ ግሌንስቶን ሙዚየም፣ ኢማጂኔሽን ስቴጅ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት የማህበረሰብ ኦፒኦይድ መከላከል ትምህርት ተንቀሳቃሽ ማስታወቂያዎችን ጭምር ያካትታሉ። ተማሪዎች እና ቤተሰቦች "ParentVue" አካውንት ለመክፈት ድጋፍ ያገኛሉ። ነፃ የክትባት ክሊኒክም ይኖራል።
ነጻ መጓጓዣ ከፈለጉ ከስድስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 9፡00 a.m. ጀምሮ ይገኛሉ። የማመላለሻ ቦታዎችን እና የመነሻ ሠአቶችን ለማየት የአውደርዕዩን ድረ ገጽ ይመልከቱ።
ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ነዎት? "ParentVUE" አካውንት ለመክፈት ይመዝገቡ
ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ የሆኑ ቤተሰቦች "ParentVUE" አካውንት እንዲመዘገቡ እናበረታታለን። ParentVUE (ፓረንትቩ) የትምህርት ውጤቶችን ለማወቅ፣ የተማሪ ትምህርት ላይ መገኘትን ለመከታተል፣ የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ፣ myMCPS የትምህርት ክፍል ተደራሽነት እና ሌሎችንም በተመለከተ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ለት/ቤቶች እንደ ዋና የመገናኛ መዘውር ሆኖ የሚያገለግል የበይነመረብ የወላጅ ፖርታል ነው። ስለ "ParentVUE" ፈጣን መግለጫ English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ |
|
ለሁሉም ተማሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መጓጓዣ መሰጠቱን እንድናረጋግጥ ያግዙን
የሁሉንም ተማሪዎች ደህንነት ለማረጋገጥ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ቀላል መመሪያዎችን እና ምክሮችን በመከተል የትምህርት አመቱን በተረጋጋ ሁኔታ እንድንከፍት ሊረዱን ይችላሉ። በትምህርት ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ ላይ ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ፣ የት/ቤት አውቶቡስ መስመሮች እና ሠዓቶች ("የአውቶቡስ መስመሮች/bus routes የሚለውን ከፍተው ያንብቡ)፣ ደንብ አክብሮ መጓዝ እና የትምህርት ቤት አውቶቡስ ስለ ማሽከርከር እና ደህነታቸው የተጠበቀ የጉዞ መንገዶች የመሳሰሉ መረጃዎችን MCPS ድረገጽ ላይ ያገኛሉ።
ስለ ምሳ ማወቅ ያለብዎትን ነገር ሁሉ ያገኛሉ
ለ 2024–2025 የትምህርት አመት የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦች (FARMS) ማመልከቻ እዚህ ይገኛል። ምንም እንኳን ባለፈው አመት የነፃ ወይም የቅናሽ ዋጋ ምግብ ለማግኘት ልጃቸው ብቁ ቢሆንም/ብትሆንም ቤተሰቦች በየትምህርት አመቱ FARMS ማመልከቻቸውን ማደስ ይጠበቅባቸዋል።
በማህበረሰብ ብቁነት አቅርቦት (CEP) የሚሳተፉ በትምህርት ቤቶች ያሉ ተማሪዎች ነጻ ምግብ ለማግኘት ብቁ ስለሆኑ አሁን FARMS ማመልከት አያስፈልጋቸውም። CEP ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች ሁሉም የነጻ እና የቅናሽ ዋጋ የምግብ ማመልከቻ ሞልተው እንዲያቀርቡ እናበረታታለን። ለፕሮግራሙ ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች ሁሉም ምግቦች ነፃ ናቸው።
ስለ ምግብ ዋጋ መረጃ ምግብ እና የአልሚ ምግብ አገልግሎት ክፍል ድረ ገጽ ይጎብኙ ፣ የተሻሻለ የምግብ ዝርዝር የያዘ ሠንጠረዥ፣ የተማሪዎችን ምርጫ እና የቬጀቴሪያን አማራጮችን የሚገልፅ አዲስ የምግብ ዝርዝር ጨምሮ በኦንላይን ወደ ልጅዎ "MySchoolBucks" የምግብ አካውንት ገንዘብ እንዴት እንደሚያስገቡ ተጨማሪ መረጃዎችን ያገኛሉ።
የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ፎተግራፎችን ያጋሩ!
እነዚያን ፈገግታዎች ማየት እንፈልጋለን!
MCPS ወላጆች/አሳዳጊዎች ሰኞ፣ ኦገስት 26 የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀን ምስሎቻቸውን እንዲያጋሩ ይጋብዛል። ከሰኞ ጠዋት ጀምሮ ምስሎች በዲስትሪክቱ ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ ይለጠፋሉ። ፎቶ መስጠት ማለት MCPS ድረ ገጽ ላይ ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እንደሚታተም ተስማምተዋል ማለት ነው። pio@mcpsmd.org ላይ በኢሜል በመላክ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለእኛ ምልክት አድርገው ፎቶ ማስገባት ይችላሉ።—#MCPSFirstDay or #MCPSForward
በዚህ ሠመር ወቅት ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህንን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000. ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
በኢሜይል እና አጫጭር ጽሁፍ የሚተላለፉ መልዕክቶችን እና የ MCPS ዘገባዎችን ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኤሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89 ይመልከቱ።
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org