መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 5 ቀን 2024

የትምህርት ቦርድ አዳዲስ ኦፊሰሮችን መርጧል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አባላት ዛሬ ዲሴምበር 5 ጁሊ ያንግ/Julie Yang ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የመረጣቸው ሲሆን ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን/Grace Rivera-Oven ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ ተመርጠዋል። የሁለቱም ኦፊሰሮች የአገልግሎት ዘመን አንድ አመት ነው። የኦፊሰሮቹ ምርጫ በየዓመቱ በዲሴምበር ወር የመጀመሪያ የሥራ ስብሰባ ላይ ይካሄዳል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አዳዲስ የቦርድ አባላት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፍርድ ቤት ፀሐፊ ካረን ቡሼል/Karen Bushell ፊት ቀርበው ሶስቱ አዳዲስ የቦርድ አባላት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። ላውራ ስተዋርት/Laura Stewart የተመረጡት ከዲስትሪክት 4፣ ናታሊ ዚመርማን/Natalie Zimmerman የተመረጡት ከዲስትሪክት 2 እና ሪታ ሞንቶያ/ Rita Montoya የተመረጡት ከዲስትሪክት At-Large ተመርጠዋል፤ ሶስቱም የቦርድ አባላት በኖቬምበር ወር የተመረጡ ሲሆን ዲሴምበር 2 ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።


ስለ MCPS እድገት የዶክተር ቴይለር ራዕይ  

አዲሱ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ደብሊው. ቴይለርየመግቢያ እቅዳቸው አካል በሆነው ስድስት ወራት የሚጠጋ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ካካሄዱ በኋላ ዲሴምበር 5 ለትምህርት ቦርድ የሚቀርብ ስትራቴጂያዊ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅተዋል።

አስፈላጊነቱ ለምንድነው፦ የመግቢያ እቅድ ሪፖርት ይህ በተሳትፎ፣ በግምገማ እና ሀሳብን ማጎልበት ላይ የተገነባው ስትራቴጂያዊ እቅድ በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉትን ማህበረሰቦች በቀጥታ በማሳተፍ ቁልፍ ጉዳዮችን ማለትም የደህንነት፣ የሞራል፣ የእኩልነት፣ እና የማስተማር ተግዳሮቶችን እውቅና ይሰጣል። የሊተርሲ እና የሂሳብ ትምህርቶች ማሻሻያ፣ የልዩ ትምህርት ድጋፍ፣ የመድብለ ቋንቋ ትምህርት ድጋፍ፣ እና የት/ቤቶች ደህንነት እና ሠላም የመሳሰሉ አስፈላጊ የሆኑ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጣል።

ትልቁን ምስል መመልከት፦እነዚህ ግንዛቤዎች በትምህርት ልማት ላይ ያለውን የዲስትሪክቱን አዲስ ስትራቴጂያዊ እቅድ እና የመጪውን 2026 የበጀት አመት ከሱፐርኢንተንደንት የሚቀርብ የስራ ማስኬጃ በጀት፣ በመሰረታዊ ነገሮች ላይ የሚደረግ ትኩረት እና በፍትኃዊነት የሚከናወን የት/ቤቶችን ድጋፍ ለማሳወቅ ይጠቅማል።

ቀጣዩስ ምንድን ነው፦ ዶ/ር ቴይለር በውስን የባጀት አቅም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ስልታዊ ጉዳዮች መከናወን እንዳለባቸው አስታውቀዋል። በጀቱ የተማሪዎችን የአካዳሚክ ስኬት ለማሳካት ትምህርት ቤቶችን በቀጥታ ለመደገፍ፣ ግብዓቶችን/ሪሶርሶችን ይበልጥ አስፈላጊ ወደሆነ ቦታ በማዞር፣ ቢሮክራሲን በመቀነስ እና በመሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ ላይ ያተኩራል።

ዲሴምበር 18 ከሱፐርኢንተንደንት የሚቀርበውን የበጀት እቅድ የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ 

ዶ/ር ቴይለር የበጀት አመት 2026 የስራ ማስኬጃ ባጀት ዝርዝር እሮብ፣ ዲሴምበር 18 ከቀኑ 6 p.m. ላይ ያቀርባሉ። የሚያቀርቡትን የባጀት ዝርዝር ማህበረሰቡ MCPS ድረገጽ ላይ ወይም MCPS-TV YouTube ቻናል ላይ በቀጥታ እንዲመለከት ተጋብዟል።


ቦርዱ 2025-2026 የትምህርት ቤቶች ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር አፅድቋል።

የትምህርት ቦርድ 2025-2026 የትምህርት አመት መደበኛ እና የኢኖቬቲቭ ት/ቤት የትምህርት አመት ቀን መቁጠሪያዎችን/ካላንደሮችን አጽድቋል።

ቁልፍ የሆኑ ፍንጮች

ካላንደሮቹን ይመልከቱ፦


2023-2024 አመታዊ ሪፖርት ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ስለ 2023–2024 የትምህርት ዓመት ለማህበረሰብ የሚቀርብ ዓመታዊ ሪፖርት አሁን ቀርቧል።

ሪፖርቱ ስለ ዲስትሪክቱ — የተማሪዎች የትምህርት አፈፃፀም መረጃ፣ የሥራ አፈፃፀም መረጃ፣ እና ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ራዕይ እና ተልዕኮ ለማሳካት ዲስትሪክቱ የወሰዳቸውን እርምጃዎች ለህብረተሰቡ ያቀርባል።

በዓመታዊ ሪፖርት ውስጥ የተካተቱት፦

ዓመታዊ ሪፖርት እዚህይገኛል።


ያገለገሉ መኪናዎች፣ እና የኮምፒውተሮች አመታዊ ሽያጭ ዲሴምበር 14 ይካሄዳል

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች አውቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን (ATF) እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (ITF) ጥገና የተደረገላቸው ያገለገሉ መኪናዎች እና ኮምፒውተሮች ቅዳሜ፣ዲሴምበር 14 ከጠዋቱ 9-11 a.m. ጀምሮ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይሸጣሉ። ት/ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ፡ The school is located at 101 Education Blvd. በጌትስበርግ (የሱሚት አቬኑ መግቢያ/Summit Avenue entrance ይጠቀሙ፤ ሽያጩ በመኪና ጥገና ክፍል ውስጥ ይከናወናል)።

መኪናዎቹ እና ኮምፒውተሮቹ የክፍል እና የላቦራቶሪ ጥናት አካል ሆነው በተማሪዎች ጥገና ተደርጎላቸዋል። ሽያጩ ተማሪዎች የሽያጭ ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ፣ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰአት እንዲያገኙ እና ለማህበረሰብ ተሳትፎ ጥልቅ አድናቆት እንዲያዳብሩ እድል ይሰጣቸዋል።

ATF አሁንም መኪናዎችን በልገሳ ማግኘት ይፈልጋል፤ ይህም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ያገለገሉ መኪናዎችን እንዴት መፈተሽ፣ መጠገን፣ እና ማደስ እንደሚችሉ እንዲማሩ ይረዳቸዋል። ATF አመቱን በሙሉ ከሰኞ እስከ አርብ 8 a.m.–3 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ በደማስከስ፣ በጌትስበርግ፣በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቀጠሮ ስጦታዎችን ይቀበላል። በልገሳ የሚሰጡ ስጦታዎች ታክስ ይቀነስላቸዋል። ለበለጠ መረጃ ወደ Mike Snyder ኢሜል ያድርጉ፥ ወይም 240-740-2050 ይደውሉ።

የኣውቶሞቢሎች ንግድ ስራ ፋውንዴሽን (Automotive Trades Foundation)
የመረጃ ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (Information Technology Foundation)


ካውንቲው ነፃ የማህበረሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ ያቀርባል
ዲሴምበር 8

የሞንትጎመሪ ካውንቲ እሁድ፣ ዲሴምበር 8 ከቀኑ 1-4 p.m. በዚህ አድራሻ፦ Executive Office Building in Rockville ነጻ የማህበረሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ ያቀርባል። የተባበሩት የማህበረሰብ ሪሶርስ ድጋፍ እና አገልግሎት የሪሶርስ አውደ ርዕይ ለነዋሪዎች ስለ ማህበረሰብ ጤና እና ደህንነት የተለያዩ መረጃዎችን ይሰጣል፣ ስለ መራባት መብት፣ የስራ ክህሎት ስልጠና፣ ኮንትራት እና ነዋሪዎች መብቶቻቸውን እንዲረዱ የሚያግዙ ቁሳቁሶችን ያቀርባል። በፌዴራል ደረጃ የሚመጡ ለውጦችን በመጠባበቅ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሁሉም ነዋሪዎች አስፈላጊ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን መረጃ እንዲያገኙ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም የግብአት አቅራቢ ወይም የማህበረሰብ አጋር አውደ ርዕዩን ለመቀላቀል የሚፈልጉ ከሆነ ወደ Lucia Jimenez በኢሜል ማሳወቅ ያስፈልጋል።

አውደ ርዕዩ የሚካሄደው በዚህ አድራሻ ነው፦ Executive Office Building cafeteria, 101 Monroe Street in Rockville. በአውቶቡስ እና በሜትሮ አገልግሎት ወደ ሕንፃው መድረስ ይቻላል። ሜትሮ ቀይ መስመር የሮክቪል ጣቢያ ቅርብ ማቆሚያ ነው። 


የትምህርት ፋውንዴሽን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች ስኮላርሺፕ ይሰጣል

ከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል እቅድ ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች ለስኮላርሺፕ እና MCPS የትምህርት ፋውንዴሽን ለሚሰጡት ሽልማቶችእንዲያመለክቱ ይበረታታሉ

የፋውንዴሽኑ ስኮላርሺፕ እና ሽልማቶች ዋና ግብ ትምህርታዊ ግቦችን መከታተል ለሚወዱ ነገር ግን እነዚያን ግቦች ለማሳካት የገንዘብ እጥረት ለሚያጋጥማቸው ተማሪዎች ገንዘብ መስጠት ነው።

ስላሉት እድሎች እና ስለ ብቁነት የበለጠ ለማወቅ ድረገጹን ይጎብኙ። ከአሁን እስከ አርብ፣ ጃንዋሪ 24, 2025 ድረስ ማመልከቻ ለማቅረብ ክፍት ነው።

ጥያቄ ለማቅረብ እዚህ ኢሜል ይላኩ ወይም 240-740-3216 ይደውሉ።


FAFSA እና MHEC One-Ap ለፋይናንሺያል እርዳታ/Financial Aid ያመልክቱ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች፡ ኮሌጅ ለመግባት እያሰቡ ከሆነ፣ የገንዘብ ድጋፍ እድሎች እንዳያመልጥዎት! ጁን 20, 2025 ለፌዴራል እና ለስቴት ዕርዳታ ያመልክቱ።

ለፌዴራል ዕርዳታ፣ ብድር፣ እና የሥራ ጥናት ፕሮግራሞች ነፃ የፌደራል የተማሪ እርዳታ (FAFSA) ለማግኘት በዚህ በይነመረብ ላይ studentaid.gov ማመልከቻ ሞልተው ያቅርቡ። ለሜሪላንድ ስቴት ስኮላርሺፕ፣ በሜሪላንድ የከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን (MHEC) በኩል ለሚጥ የገንዘብ ድጋፍ እና የብድር ፕሮግራሞች፣ ሰነድ ለሌላቸው ተማሪዎች የሚሰጥ ድጋፍን ጨምሮ፣ ቤተሰቦች MDCAPS መግለጫ አዘጋጅተው MHEC One-App. መተግበሪያ ላይ ማቅረብ ይችላሉ።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፣ የፌደራል የተማሪ እርዳታ/Federal Student Aid MHEC Financial Aid Descriptions እናMHEC One-Appይመልከቱ።


የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት እስከ ጃንዋሪ 3, 2025 መቅረብ አለበት

ከጁን 1, 2024 ጀምሮ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያጠናቀቁ ተማሪዎች SSL የተሳተፉበትን ማረጋገጫ ቅጽ ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ በተወሰነው ጃኑዋሪ 3, 2025 የማቅረቢያ ቀን ማስገባት አለባቸው።ነገር ግን ከሜይ 30, 2025 ከሚፈለገው የጊዜ ገደብ በኋላ መዘግየት የለበትም።

ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶች ማስመዝገብ አለባቸው። የዊንተር (ክረምት) ዕረፍት ለተማሪዎች SSL እድሎችን ለመጠቀም የሚሳተፉበት አመቺ ጊዜ ነው። የበለጠ ለመረዳት፣ እዚህ ይመልከቱ። የተተረጎሙ ሠነዶች እዚህ ይገኛሉ።

ተማሪዎች SSL ሪከርዳቸውን፣ ቅጾችን፣ መመሪያዎችን እና ሌሎች ሪሶርሶችን MCPS SSL Hub for Students/Families ላይ ማግኘት ይችላሉ።


ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች ደህንነት የመጠበቅ እርዳታ

ፓዝፋይንደርስ ፎር ኦቲዝም ለቤተሰቦች እና ተንከባካቢዎች ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ላለባቸው ልጆች ደህንነት ለመጠበቅ ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ የደህንነት ኪት/መገልገያዎችን ያቀርባል። የደህንነት ኪቶች/መገልገያዎች እዚህ ይገኛሉ። ይህ ድረ ገጽ ልጅዎ ከቤት ወይም ከትምህርት ቤት ወጥቶ(ታ) የሚንከራተት/የምትንከራተት ከሆነ ምን ማድረግ እንዳለብዎት፣የመጀመሪያ እርዳታ ምላሽ ሰጪ ጥሪዎችን እና 911 የመደወል መመሪያን በመሳሰሉት ርዕሶች ላይ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል።

የፓዝፋይንደር የኦቲዝም፣የደህንነት ኪት/መገልገያ
ሜሪላንድ የአእምሮ ዝግመት ተጠቂዎች ህብረት/MD Autism Coalition፣ 911 ይደውሉ
ሜሪላንድ የአእምሮ ዝግመት ተጠቂዎች ህብረት/MD Autism Coalition፣ 911 ይደውሉ ስፓንሽኛ
ሜሪላንድ የአእምሮ ዝግመት ተጠቂዎች ህብረት/MD Autism Coalition፣ 911 ይደውሉ፣ ማንደሪን ቻይንኛ
ሜሪላንድ የአእምሮ ዝግመት ተጠቂዎች ህብረት/MD Autism Coalition፣ 911 ይደውሉ፣ ኮርያንኛ
ሜሪላንድ የአእምሮ ዝግመት ተጠቂዎች ህብረት/MD Autism Coalition፣ 911 ይደውሉ፣ አማርኛ


የላቲን የዳንስ ትርኢት አውደ ርዕይ

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተደገፈ፣ 24ኛው አመታዊ ከትምህርት ሠዓት በኋላ የሚካሄድ የዳንስ ፈንድ "After School Dance Fund Baila4Life" የላቲን ዳንስ ውድድር በመቶዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በስትራትሞር የሙዚቃ ማእከል ለአንድ ቀን አስደናቂ ችሎታ እና ብቃት አሳይተዋል። ተጨማሪ ያንብቡ፤ የፎተግራፍ ክምችት ይመልከቱ


ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)