መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 2, 2025

ስለ ሥራ ማስኬጃ በጀት በሚካሄድ የማህበረሰብ ውይይት ላይ ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ።

ሱፐርኢንተንደንት ቶማስ ቴይለር ለ 2026 የበጀት ዓመት $3.61 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት ንድፈሃሳብ፣ ፕሮፖሳል አቅርበዋል፣ ይህም የትምህርት ቤቶችን የአሠራር ሥርዓት ለማረጋጋት እና ለተማሪዎች ትምህርት እና ለት/ቤቶች የትምህርት መርጃ ግብዓቶችን ድጋፍ ቅድሚያ ለመስጠት ነው። ንድፈሃሳቡ፣ፕሮፖዛሉ በቀጥታ ወደ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚያተኩር፣ የተማሪዎችን ስኬት የሚደግፍ እና በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያሉ መዋቅራዊ ጉድለቶችን የሚፈታ ''በመሠረታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር'' የሚለውን አካሄድ ያንፀባርቃል። 

የትምህርት ቦርድ አሁን በበጀቱ ላይ ህዝባዊ ውይይቶችን እና የስራ ክፍለ ጊዜዎችን ያካሄዳል። የጊዜ ሠሌዳው እንደሚከተለው ነው፦

የሥራ ማስኬጃ ባጀት ድረገጽ/Fiscal Year 2026 Operating Budget website


መጪዎቹ ዝግጅቶች እንዳያመልጥዎት

የልዩ ትምህርት መርጃ አውደርዕይ እሮብ፣ ጃንዋሪ 15 ከቀኑ 5:30–7:30 p.m. ከዚህ ቀጥሎ ባለው አድራሻ ኦዲተሪየም ውስጥ ይካሄዳል፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville ይህ ዝግጅት ግላዊ የትምህርት ፕሮግራም (IEPs) የሚሰጣቸው ልጆች ላሏቸው ወላጆች ሁሉ ክፍት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ከትምህርት ሠዓት በኋላ ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣የሠመር ፕሮግራሞች፣ እና ተጓዳኝ ስልጠናዎች ከማህበረሰብ ድርጅቶች የበለጠ መማር ይችላሉ።

ታሪካዊ የጥቁር ኮሌጆች እና ዩንቨርስቲዎች (HBCU) አውደርዕይ፦ ዓርብ፣ ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ the Universities at Shady Grove (USG). ይህ ዝግጅት 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው/ለአሳዳጊዎቻቸው ከ 50 በላይ HBCU ተወካዮች ጋር ለመገናኘት እና በአውደ ጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣቸዋል። ተጨማሪ መረጃ

FAFSA/MHEC One Application Completion Event፦ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ USG ይህ ዝግጅት ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ነው። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል


በአየር ሁኔታ ምክንያት የሚደረጉ ለውጦችን መረጃ ማወቅ አለብዎት 

የክረምት አየር ሁኔታ እየመጣ ስለሆነ አንዳንድ ጊዜ የትምህርት ቤት መርሃ ግብሮችን እና ስራዎችን ለውጥ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። በከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት ት/ቤቶች ዘግይተው የሚጀምሩ ከሆነ፣ ወይም ት/ቤቶችን መዝጋት አስፈላጊ ከሆነ፣ የአሠራር ለውጦች ስለሚደረጉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ያለዎትን ግንኙነት መቀጠልእና Alert MCPSአገልግሎት ለማግኘት ተመዝግበው በቀለም ኮድ የምናስተላልፈውን የመረጃ ስርጭት ይከታተሉ።

እርስዎን ማግኘት የምንችልበት መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ

ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚደርሰዎት ለማረጋገጥ እባክዎ ParentVUE link በመጠቀም MCPS Community Tech Support ድረገጽ ላይ የእርስዎን ወቅታዊ መረጃ ያስገቡ።

ስለቀለም ኮዶች ይበልጥ ይወቁ
2024-2025 የትምህርት አመት ከባድ የአየር ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት ስለ MCPS የአሠራር ሁኔታ፣አማርኛ


"Dine with Dignity" ልግስና ይፈልጋል

MCPS ተማሪዎች በትምህርት ቤት ለመማር መዘጋጀታቸውን በማረጋገጥ ረገድ ለሁሉም ተማሪዎች ምግብ ያቀርባል። "Dine with Dignity" ፕሮግራም ቤተሰቦች ነፃ ምግብ የማግኘት ፍቃድ እስከሚሰጣቸው ድረስ የተጠራቀመ ዕዳ ለመክፈልና ለተማሪዎች ምገባ የገንዘብ እርዳታ ይሰበሰባል። ለ "Dine with Dignity" የሚደረግ ልገሳ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት እና ከእኩዮቻቸው ጋር አብረው መማር እንዲችሉ ይረዳል። ዛሬውኑ ይለግሱ


የተማሪዎች እድል

SMOB ለእጩነት የማመልከት ወቅት፦ ለተማሪ የትምህርት ቦርድ አባልነት (SMOB) ለመወዳደር የሚፈልጉ ተማሪዎች ሐሙስ፣ ጃኑዋሪ 2, 2025 እስከ 5 p.m. የእጩነት ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ። ማመልከቻ የሚቀርብበት ጊዜ ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 23 ያበቃል። ለእጩነት የሚወዳደሩ ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአሁኑ ጊዜ 10ኛ ወይም 11ኛ ክፍል ተማሪ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ ከሆኑ SMOB ለመወዳደር ብቁ ናቸው። ለእጩነት የመወዳደሪያ ቅጽ SMOB የምርጫ ፕሮቶኮል ገጽ 31-32 ላይ ይገኛል። የተሞሉት ቅጾች ስካን ተደርገው ወደ፦ Shella Cherry, director, Student Leadership & Extracurricular Activities በኢሜል መላክ አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ

የተማሪዎች ጉባኤ/ስብሰባ ለመሳተፍ ጊዜዎን ይቆጥቡ፦ ቅዳሜ፣ ጃኑዋሪ 4 ከጠዋቱ 10 a.m.-12:30 p.m. የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በዋልተር ጆንሰን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ ውስጥ በሚደረግ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። በስብሰባው ወቅት opioid እና fentanyl/ኦፒዮይድ እና ፈንታኒል መጠቀም ተማሪዎችን በጤናቸው ላይ ስለሚፈጥረው ተፅእኖ እና ጉዳት በማስተማር እና ከመጠን በላይ በመውሰድ ችግር በሚፈጠርበት ጊዜ Narcan/ናርካን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ስልጠና ይሰጣል። ተማሪዎች ለተሳትፏቸው ሶስት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን (SSL) ማግኘት ይችላሉ። ይመዝገቡ/RSVP. የዋልተር ጆንሰን አድራሻ፦ Walter Johnson is located at 6400 Rock Spring Drive in Bethesda. 

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት እስከ ጃንዋሪ 3, 2025 መቅረብ አለበት

ከጁን 1, 2024 ጀምሮ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያጠናቀቁ ተማሪዎች አስፈላጊውን SSL ክንውን የማረጋገጫ ቅጽ ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ በተወሰነው የማስረከቢያ ቀን ጃኑዋሪ 3, 2025 ማቅረብ አለባቸው።

ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማስመዝገብ አለባቸው። የበለጠ ለመረዳት፣ እዚህ ይመልከቱ። የተተረጎመ መረጃ እዚህ ይገኛል። 

ተማሪዎች SSL ሪከርዳቸውን፣ ቅጾችን፣ መመሪያዎችን እና ሌሎች ሪሶርሶችን MCPS SSL Hub for Students/Families ላይ ማግኘት ይችላሉ።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)