መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 16, 2025

ለበጀት አመት FY 2026 የቀረበ የስራ ማስኬጃ በጀት ዝርዝር።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ W. ቴይለር ለበጀት ዓመት (FY) 2026 የሥራ ማስኬጃ በጀት ዝርዝር አቅርበዋል። ይህ ሰነድ በበጀት አወጣጥ ሂደት ላይ ግልፀኝነትን ለማስፈን ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ በመሆኑ የበጀት ዝርዝሩ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ማህበረሰብ በኦንላይን እዚህ ቀርቧል።

የተሻሻለው የበጀት ዝርዝር በመጀመሪያ ዲሴምበር 18 በቀረበው በጀት ላይ የተገነባ ሲሆን፣ የታቀደው የስራ ማስኬጃ በጀት በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተደረጉ የበጀት ለውጦችን በዝርዝር አቅርቧል። በጀቱ በሚከተሉት ምድቦች የተዋቀረ ነው፦ የትምህርት ቤት ገቢ፣ የመሠረታዊ በጀት ለውጦች፣ የመሠረታዊ በጀት መስፈርቶች፣ ተጨማሪ ውሳኔ የማይጠይቁ እና ለውሳኔ የይቀርቡ ብሉፕሪንት እና የሚፀድቁ ወጪዎችን መስፈርቶች አስቀምጧል። እያንዳንዱ የባጀት ዘርፍ ዝርዝሮች አሉት። 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ስለ MCPS የበጀት አሠራር ሂደት ለማስረዳት የማህበረሰብ ስብሰባዎችን እያስተናገደ ነው። ስለ 2026 የስራ ማስኬጃ በጀት እና ቦርዱ ቅድሚያ ስለሚሰጣቸው ነገሮች መግለጫ፣ እና ጥያቄና መልስ ስለሚሰጥ የትምህርት ቦርድ ፕሬዘዳንት ጁሊ ያንግን እና ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴይለርን ይቀላቀሉ። 

የማህበረሰብ ስብሰባዎች መርሃ ግብር፦

የትምህርት ቦርድ ስለ ስራ ማስኬጃ በጀት የህዝባዊ ውይይት መድረኮችን እና የስራ ክፍለ ጊዜዎችን በሚከተሉት ቀናት ያካሂዳል፦

ቦርዱ ማክሰኞ ፌብሩዋሪ 4 በሚያካሂደው የቢዝነስ ስብሰባ የስራ ማስኬጃ በጀቱን በጊዜያዊነት ያፀድቃል፣ የመጨረሻ ማክሰኞ፣ ጁን 10 በሚያደርገው መደበኛ ስብሰባ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ስለቀረበው FY 2026 በጀት ዓመት የሥራ ማስኬጃ በጀት በዚህ ድረገጽ ላይ ይበለጥ ያንብቡ።   


ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ለመፍጠር በጋራ መስራት

የትምህርት ዓመቱን ሁለተኛ አጋማሽ ስንጀምር፣ ተማሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ብዙ ግብአቶች/ሪሶርሶች መኖራቸውን ማሳሰብ እንፈልጋለን። እነዚህ መገልገያዎች/ሪሶርሶች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ መከባበር የሠፈነበት እና አካታች የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ለማስፈን ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃሉ።

የዜግነት ተሳትፎ እና የሠለጠነ/ጨዋ አገላለፅ (የቋንቋ አጠቃቀም)
MCPS በተማሪዎቻችን መካከል ተሳትፎን እና ጨዋ/የሠለጠነ የቋንቋ አጠቃቀም/ንግግርን ለማስፈን ቁርጠኛ ነው። እነዚህ ወጣቶች በመከባበር እና በራስ በመተማመን የተለያየ አለም ለመቃኘት የሚያስችሏቸው አስፈላጊ ክህሎቶች እና ስልቶች ናቸው።

የተለያዩ ማህበረሰቦቻችንን መደገፍ
ብዝሃነታችን ለኛ ትልቅ ጥንካሬ ነው፣ እና እያንዳንዱ ግለሰብ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው/ያላት እና የሚደገፍ መሆኑን ማረጋገጥ የእኛ ግዴታ ነው። እባክዎ የሚከተሉትን መገልገያዎች/ሪሶርሶች ያስታውሱ፦

የጥላቻ አመለካከትን እና ፀረ ዘረኝነትን መፍትሔ መስጠት
MCPS የተለያየ እርከን ያላቸው ድንጋጌዎች/ፕሮቶኮሎች የጥላቻ እና አድሏዊ ጉዳዮችን ለመፍታት ወሳኝ ናቸው፣ እነዚህ ሁኔታዎች ሲከሰቱ በጥንቃቄ እና በብቃት ምላሽ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን።


የትምህርት ቦርድ (BOE) የሥራ ግብረኃይል የላቀ ብቃት ፖሊሲ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፈልጋል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ስለ MCPS ሰራተኞች ጥልቅ፣ ስልታዊ፣ እና ተከታታይነት ያለው የሙያ እድገት ሂደቶችን ለመገንባት በቀረበው Policy GAA, Workforce Excellencee ላይ የህዝብ አስተያየት ይፈልጋል። ፖሊሲው አንድ ሰራተኛ ባለ(ች)በት የስራ መደብ ላይ ውጤታማነትን እና የክህሎት እድገትን እንዲሁም MCPS ውስጥ የሙያ እና የክህሎት እድገት እንዲዳብር ማቀድ ላይ ቅድሚያ ይሰጣል። እነዚህ ስልቶች የሰራተኞችን ክህሎት ያዳብራሉ፣ ይገነባሉ፣ ተሰጥኦቸውን በሥራ እንዲተረጉሙ እና የማያውቁትን ወይም ፈታኝ ሁኔታዎችን ምናባዊ ምላሽ የመስጠት አቅምን እንዲያሳድጉ በማድረግ—MCPS ጽኑ አቅም ያለው ድርጅት ያደርጉታል። 

ፖሊሲው ከጃንዋሪ 10, 2025 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት የቀረበ ስለሆነ የህዝብ አስተያየት መስጫ ጊዜው እስከ ሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 3 ክፍት ሆኖ ይቆያል።

የግምገማ መመሪያ GAA
አስተያየቶችን ያቅርቡ

ቦርዱ ከሞንጎመሪ ካውንቲ ጀነራል ኢንስፔክተር ፅህፈት ቤት ምክረሃሳብ በመጠየቅ ባዘጋጀው አዲስ ፖሊሲ GCB፥ የሰራተኛ ስነምግባር ጉድለት ምርመራ ላይ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፈልጋል። MCPS የሰራተኞቹን የስነ ምግባር ጉድለት ይመረምራል፥ ፖሊሲው የሠራተኛን የስነምግባር ጉድለት/ጥፋቶችን ለመመርመር ያለው አላማ የሚወስደው እርምጃ እና አካሄድ ያብራራል። ከዲሴምበር 10, 2024 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት የቀረበ ሲሆን የአስተያየት መስጫ ጊዜው እስከ ፌብሩዋሪ 3, 2025 ክፍት ይሆናል።

የግምገማ መመሪያ GCB
አስተያየቶችን ያቅርቡ


ሠመር ራይዝ የተማሪዎች ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

ለሠመር ራይዝ 2025 የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ፌብሩዋሪ 18 ድረስ ክፍት ነው። 

ሠመር ራይዝ ከንግድ ተቋማት፣ ከመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር በሙያ ላይ ያተኮረ የትምህርት ልምድ ይሰጣል። ፕሮግራሙ በሠመር ወቅት ተጨባጭ የሥራ ልምድ ማግኘት ለሚፈልጉ የሁለተኛ ደረጃ ሶፎሞር እና ጁንየር ተማሪዎች ክፍት ነው።

ተሳታፊ ተማሪዎች ከጁን 23 እስከ ጁላይ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 50 ሰአታት በአካል፣ ቨርቹዋል፣ ወይም ሁለቱንም አጣምረው በኢንዱስትሪ ምርጫዎቻቸው መሰረት የሙያ ልምድ ወደሚሰጧቸው ተቋማት ጋር ይመደባሉ። ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፦

የበለጠ ለማወቅ፣ የተማሪ እና የወላጅ/አሳዳጊ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎች አንዱን ይሳተፉ ወይም www.MCPS-SummerRISE.org ይጎብኙ።

ምዝገባ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 18 ይዘጋል።


የ ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Wootton High School ተማሪ በሙዚቃ እንቅፋቶችን በመሰባበር ችሎታው በብዙዎች ተደንቋል።

በቶማስ ኤስ ውተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Thomas S. Wootton High School ጁንየር ተማሪ የሆነው ማክስ ንጉየን/Max Nguyen የፈጣን ስርጭት ትኩረት ያገኘው "Stick Season" የተሰኘው ዝግጅቱ በሙዚቀኛ Noah Kahan አማካኝነት በኢንስታግራም ከተሠራጨ በኋላ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን አግኝቷል። የሴሬብራል ፓልሲ ጉዳተኝነት ጋር የተወለደው ንጉየን/Nguyen አካላዊ ተግዳሮቶቹን በመቋቋም ሙዚቃን በመከታተል፣ ከፒያኖ ጀምሮ እንደ ቴራፒ በመጠቀም እና በኋላም በደጋፊ መምህር እርዳታ በጊታር የመጫወት ችሎታውን አዳብሯል። በአሁኑ ጊዜ አፍቃሪ ሙዚቀኛ እና የተነቃቃ ፍላጎት ያለው የባዮሜዲካል ኢንጅነር የሆነው ንጉየን/Nguyen ልምዱን ሌሎችን ለማነሳሳት፣ ለጀማሪዎች የጊታር ትምህርቶችን በመቅረጽ እና በአካባቢው gigs ላይ በመጫወት ላይ ይገኛል። የቀስቃሽ ጉዞውን ሙሉ ታሪክ አንብቡ!


የፍጅት/እልቂት/ሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን፣ የጥቁር ታሪክ ወር

ለተማሪዎች፣ለሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት የሚከተሉት ዝግጅቶች ክፍት ናቸው። ተማሪዎች በአንድ ዝግጅት እስከ ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።

ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የፍጅት/እልቂት/የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን ዌብናር/Webinar
የኦሽዊትዝ ማጎሪያ እና የፍጅት ካምፕ 80ኛ አመት የነጻነት መታሰቢያ በአል ማክበር
ሐሙስ፣ ጃኑዋሪ 30፣ 5-6፡30 ፒ.ኤም
መመዝገቢያ/Registration Link
በራሪ ጽሑፍ 


የጥቁር ነፃነት ትግል፡ Black Communities in Montgomery County Post Civil War to Today
የደራሲ ሰለስተ ዊንስተን/Celeste Winston ሃወንዶች እንዴት ማጣት እንደተቻለ፥ ማሩን ጂኦግራፊ እና ከፖሊስ አገልግሎት ባሻገር ያለ ዓለም/How to Lose the Hounds: Maroon Geographies and a World Beyond Policing እይታ
ሐሙስ፣ ፌብሩዋሪ 6, 6-7፡30 ፒ.ኤም
መመዝገቢያ/Registration Link
በራሪ ጽሑፍ


MoCo ለታሪክ ውድድር ቀን ዳኞችን ይፈለጋሉ

ለማህበረሰብ አባላት እና የታሪክ ተመራማሪዎች የቀረበ ጥሪ፡ የአካባቢ ተማሪዎች የእርስዎን እርዳታ ይፈልጋሉ! 2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ታሪክ ቀን ውድድር ቅዳሜ፣ ማርች 8 ይካሄዳል።

የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ዋነኛ ምንጮችን ዘልቀው በመግባት ጥናትና ምርምር ሲያካሂዱ ቆይተዋል፣ አቀራረቦችን ተዘጋጅተዋል። ውድድሩ ቢያንስ 18 አመት እና ከዚያ በላይ የሆናቸው በጎ ፍቃደኞች የተማሪዎችን ስራ በመገምገም ዳኞች ሆነው እንዲያገለግሉ ይፈልጋል። ግቡ የታሪክ ትውስታን ማበረታታት እና ማሳደግ ነው።

ዝግጅቱ የሚካሄደው ሲልቨርስፕሪንግ በስላይጎ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት "Sligo Middle School, 1401 Dennis Avenue in Silver Spring" ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ 2 p.m. ድረስ ነው። የቀድሞ ልምድ አስፈላጊ አይደለም። ዳኛ ለመሆን ይመዝገቡ

ትምህርት ቤቶቻቸውን ለመወከል የተመረጡ ተማሪዎች በካውንቲው ዝግጅት ላይ ይወዳደራሉ፣ ከፍተኛ ውጤት ያመጡት በዳኞች የተመረጡ ተወዳዳሪዎች በሜይ ወር በባልቲሞር ካውንቲ የሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ በሚካሄደው የሜሪላንድ ታሪክ ቀን የስቴት ውድድር ላይ ይሳተፋሉ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት Kelli Champagne ከቅድመ መዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የማህበራዊ ጥናት ባለሙያ፣ ወይም Abbie Lamb፣ የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ኢሜይል ይላኩ።


እንዳያመልጥዎ…

ታሪካዊ የጥቁር ኮሌጆች እና ዩንቨርስቲዎች (HBCU) አውደርዕይ፦ ዓርብ፣ ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ the Universities at Shady Grove (USG). ይህ ዝግጅት 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው/ለአሳዳጊዎቻቸው ከ 50 በላይ HBCU ተወካዮች ጋር ለመገናኘት እና በአውደ ጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣቸዋል። ተጨማሪ መረጃ


FAFSA/MHEC One Application Completion Event፦ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8:30 p.m. በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ USG ይህ ዝግጅት ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ነው። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል


መጪዎቹ የተማሪዎች ዝግጅቶች እና እድሎች

2025 የጌትስበርግ መጻሕፍት ፌስቲቫል "Gaithersburg Book Festival" አመታዊ የግጥም ውድድር ለማቅረብ ክፍት ነው። የዘንድሮው የመወዳደሪያ ጭብጥ “የዜግነት ግዴታ/Civic Duty” ነው። ይህ ውድድር ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ክፍት ነው የማቅረቢያ የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ፌብሩዋሪ 21 እኩለ ሌሊት ነው። አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሶስተኛ ደረጃ ያገኙ እና በደጋፊዎች ተወዳጅ የሆኑ አሸናፊዎች በቅደም ተከተል $250፣ $100፣ $50 እና $25 ያገኛሉ። አሸናፊዎች ቅዳሜ፣ ሜይ 17 በፌስቲቫሉ ላይ ይፋ ይደረጋሉ። 2025 GBF የግጥም ውድድር ጽሑፍ

Division of Sustainability and Compliance ስለ ተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃና ዘላቂነት፣ ስለ ኃይል/ኢነርጂ ቁጠባ፣ የቆሻሻ ቅነሳ እና እንደገና ጥቅም ላይ ማዋልን አስፈላጊነት ግንዛቤ ለማስፋት ዓመታዊ የፖስተር ዝግጅት ውድድር ያካሄዳል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ሰራተኞች በሙሉ እንዲሳተፉ እና በስፕሪንግ ወቅት አሸናፊዎችን ለመወሰን በኦንላይን ድምጽ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል። የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ኤፕሪል 4 ነው።

2025 የተፈጥሮ አካባቢ ዘላቂነት ፖስተር የውድድር መግቢያ ቅጽ
የውድድር መመሪያዎች


በጃኑዋሪ ወር የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) እድሎች ይኖራሉ፡_


የሠመር ካምፕ ምዝገባ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 21 ይከፈታል፦የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛደህንነቱ የተጠበቀ፣ አዝናኝ እና አስደሳች የሠመር ካምፖችን ያስተናግዳል። ለካውንቲው ነዋሪዎች የካምፕ ምዝገባ ማክሰኞ ጃንዋሪ 21 ከቀኑ 6፡30 a.m. ይጀምራል። ከመመዝገቢያ ቀን በፊት የዲጂታል ፕሮግራም መመሪያውንይመልከቱ።

2025 Rec Assistማመልከቻዎችን እየተቀበሉ ነው፣ይህም ብቁ ለሆኑ ነዋሪዎች የመዝናኛ ፕሮግራሞች ስኮላርሺፕ የማግኘት እድል ይሰጣቸዋል።ስለ ሠመር ካምፕ ምዝገባ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ድረ ገጹን ይጎብኙ ወይም 240-777-6840 ይደውሉ።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)