መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ማርች 6/2025

ድምፅዎን አሰሙ!

የሞንትጎመሪ ካውንስል ምክትል ፕሬዝዳንት ዊል ጃዋንዶ ስለ በጀት ዓመት 2026 የስራ ማስኬጃ በጀት ለመወያየት ተከታታይ መድረኮችን እያስተናገዱ ናቸው። ጃዋንዶ፣ የምክር ቤቱ የትምህርት እና የባህል ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን፤ ከ MCPS ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ ቴይለር እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጄርሜይን ዊሊያምስ ጋር አብረው ይቀርባሉ። 

ዝግጅቶቹ የሚከናወኑት በሚከተሉት ቀናት ነው፦

ይመዝገቡ/RSVP

የስፓንሽኛ እና የአሜሪካ የምልክት ቋንቋ ትርጉም ይኖራል።


የሊተርሲ፣ እና የሂሳብ ትምህርት ቡድኖች የስርዓተ ትምህርት ምሽቶችን ያስተናግዳሉ።

የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሊተርሲ ስርአተ ትምህርት ምሽት የመጨረሻው ክፍለጊዜ ዛሬ ማታ ሀሙስ፣ ማርች 6፣ ቤተሰቦችን ከአዲሱ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ሊተርሲ ስርአተ ትምህርት "Amplify Core Knowledge Language Arts" የቋንቋ ጥበብን ለማስተዋወቅ እየተካሄደ ነው። ይህ ክፍለ ጊዜ ከቀኑ 6፡30–8፡10 p.m. Zoom በዙም ይካሄዳል። ይመዝገቡ

የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሂሳብ ትምህርት ቡድኖች የሥርዓተ ትምህርት ምሽቶችን በማስተናገድ ላይ ናቸው፣ ይህም የሂሳብ ሥርዓተ-ትምህርት መርጃዎችን፣ ከመዋእለ ህጻባት እስከ አሥራ ሁለተኛ ክፍል (K-12ኛ) የኮርስ ፕሮግራሞችን፣ እና ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የተቀናጀ ሒሳብን በተመለከተ ወደፊት የሚመጡ ለውጦችን ያካትታል። ስለ "Eureka" ሒሳብ እና "Illustrative Math" ሒሳብ ሥርዓተ-ትምህርት ልምድ ለማጋራት የሒሳብ ትምህርት ባለሙያዎች ይሳተፋሉ።

ሁለት በአካል ተገኝተው የሚሳተፉበት ክፍለጊዜዎች ይከናወናሉ፦

ሰኞ፣ ኤፕሪል 7 ጀምሮ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የተቀረጹ መረጃዎች ሒሳብ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

2025 የትምህርት አመት የሒሳብ ሥርዓተ ትምህርት ምሽቶች


ቀኑን ያስታውሱ፥ የልዩ ትምህርት አውደ ርእይ ሜይ 10 ይካሄዳል።

ስለ ልዩ ትምህርት የቤተሰብ መርጃ አውደ ርዕይ ቅዳሜ፣ ሜይ 10 ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 1 p.m. በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። Seneca Valley High School, 19401 Crystal Rock Drive in Germantown. ይህ በነጻ የሚቀርበው ዝግጅት ከ 40 በላይ የማህበረሰብ ድርጅቶችን የሚያሳትፍ ሲሆን፣ ተማሪዎች ላሏቸው ቤተሰቦች (IEP) የድጋፍ አገልግሎቶችን፣ ግብዓቶችን፣ እና እንዲሁም አዝናኝ የልጆች እንቅስቃሴዎችን፣ የጨረቃ ዝላይ፣ ዲጄ፣ እና ፊት የመቀባት ጨዋታዎች ይቀርባሉ። ለበለጠ መረጃ ይጠብቁን።


"RespectFest" ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 5 ይካሄዳል።

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ወላጆች፡ ስለ ጤናማ ግንኙነት፣ የፍቅር ጓደኝነት ጥቃትን መከላከል፣ እና ስለ ስምምነት እና የማህበረሰብ መገልገያዎችን ለማወቅ ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 5 ቀን በሚካሄድ ፕሮግራም ለመሳተፍ ቀን መቁጠሪያዎ ላይ ያስታውሱ። "RespectFest" ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 5 ቨርቹዋል አውደጥናቶችን/ወርክሾፖችን እና በአካል ተገኝተው የሚሳተፉበት ፌስቲቫል እሁድ ኤፕሪል 6 ከቀኑ 1-4 p.m. በዊተን የማህበረሰብ መዝናኛ ማእከል ያቀርባል። በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ ለማዘመን ይመዝገቡ


ስለ ህይወትዎ ትንሽ ድራማ ይተውኑ!

በፀደይ ወቅት ለሚካሄድ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቲያትር እና የዳንስ ፕሮዳክሽን ቲኬቶችን አሁን ያግኙ። እነዚህ ምርጥ ትርኢቶች በዚህ ወር ጀምሮ እስከ ሜይ ወር ድረስ ይቀጥላሉ።

“Mean Girls” and “Shrek the Musical” to “Antigone” and “A Midsummer Night’s Dream,” ከመሳሰሉት ትእይንቶች ለሁሉም ሰው ፍላጎት የሚስማማ ነገር ይኖራል።

2024–2025 ስፕሪንግ ፕሮዳክሽን


ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች

የሴቶች ታሪክ የሚዘከርበት ወር ዌብናር/Webinar፡ MCPS እና ሞንትጎመሪ ፓርኮች በዙም የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) እድል ይሰጣሉ። ዌቢናር የሚካሄደው እሮብ፣ ማርች 12፣ከቀኑ 5-6፡30 ፒ.ኤም/p.m. ሲሆን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ሴቶች ህይወትን እንዴት እንደሚገፉ ለተሳታፊዎች ያጋራል። ተማሪዎች ሁለት SSL ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ። ስፓንሽኛ የትርጉም አገልግሎት ይሰጣል። መመዝገቢያ ሊንክ

ስለ ዘላቂነት የፖስተር ውድድር፡ ይህ አመታዊ ውድድር ስለ ተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት፣ የሃይል አጠባበቅ፣ የቆሻሻ ቅነሳ፣ እና በኃላፊነት ስሜት እንደገና ጥቅም ላይ ስለማዋል አስፈላጊነት ግንዛቤ ይሰጣል። ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ሰራተኞች እንዲሳተፉ እና አሸናፊዎቹን ለመወሰን በኦንላይን እንዲመርጡ ተጋብዘዋል። የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ኤፕሪል 4 ነው። 2025 ስለ ዘላቂነት የፖስተር ውድድር የመግቢያ ቅጽ እና የውድድር መመሪያ

NAACP ስኮላርሺፕ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ NAACP ቅርንጫፍ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂ ሲንየር ተማሪዎች $1,000 ስኮላርሺፕ እየሰጠ ነው። ማመልከቻ ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ማርች 21 ነው። አመልካቾች 3.0 ወይም ከዚያ በላይ GPA ሊኖራቸው ይገባል፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሳተፉ፣ እምነትን መሰረት ያደረገ፣ ሀይማኖታዊ፣ ወይም የበጎ ፍቃደኝነት ተግባራት ላይ መሳተፍ እና “The Fight for Justice Continues!”/“ለፍትህ ትግሉ ይቀጥላል!” በሚል መሪ ሃሳብ 300 ቃላት ድርሰት ማቅረብ አለባቸው። ማመልከቻዎችን ለትምህርት ቦርድ ቢሮ/Board of Education office,15 W. Gude Drive, Suite 100, Rockville, MD, 20850 ወደ Rebecca Gibson ያቅርቡ።

LEAAP ስኮላርሺፕ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአስተማሪዎች ሊግ (LEAAP) የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ኤዥያ እና ፓሲፊክ አሜሪካን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲንየር ተማሪዎችን በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርሱ ለመርዳት $3,000 ስኮላርሺፕ ይሰጣሉ። የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 1 ነው። ተጨማሪ መረጃ

ለሠመር ራይዝ አስተናጋጆች/Summer RISE Hosts ምዝገባ፦ ለቢዝነስ ተቋማት፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ተማሪዎችን በሠመር ራይዝ ፕሮግራም ተቀብለው ለማስተናገድ የቀረበላቸው ጥሪ Summer RISE 2025 የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ማርች 7 ይዘጋል። ይህ የአምስት ሳምንት መርሃ ግብር ለታዳጊ ወጣቶች እና ለሲንየር ተማሪዎች በሙያ ላይ የተመሰረተ የትምህርት ልምዶችን ይሰጣል፤ እና አሰሪዎች ባለተሰጥኦ ዝንባሌ ያላቸውን ለመምረጥ ይረዳቸዋል። ዛሬውኑ ይመዝገቡ! ጥያቄ ካለዎት ወደ Davida Gurstelle ኢሜይል ያድርጉ ወይም 240-740-5599 ይደውሉ።


በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜው ዘገባ እንዳያመልጥዎት

የቅርብ ጊዜውን MCPS የዜና ገጻችንን ያንብቡ፡


MoComCon ለማርች 22-23 ተዘጋጅቷል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ መፃህፍት አመታዊ ነጻ የኮሚክ ኮንቬንሽኑን MoComConጀርመንታወን ቤተ መፃህፍት እና በብላክሮክ የስነ ጥበባት ማዕከል ያስተናግዳል።

በዚህ አመት፣ MoComCon ወደ ሁለት ቀናት የሚዘልቅ በመሆኑ፣ ቅዳሜ ማርች 22፣ በብላክሮክ የስነ ጥበባት ማእከል፦ BlackRock Center for the Arts, at 12901 Town Commons Drive in Germantown ይካሄዳል። ከሠአት በኋላ 1-5 p.m., በዕለቱ ለታዳጊ ወጣቶች (13 እና ከዚያ በላይ) እና ለጎልማሶች የተለያዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉ። የኮስፕሌይ ውድድርን ጨምሮ ተሳታፊዎች ፓነሎች፣ ወርክሾፖች፣ እና ውድድሮች ላይ በጉጉት ሊሳተፉ ይችላሉ።

እሑድ፣ ማርች 23፣MoComCon በጀርመንታወን ቤተመጻሕፍት፦ Germantown Library at 19840 Century Blvd ይሄዳል። ከጠዋቱ 10 a.m. እስከ 2 p.m., ድረስ ቤተ መፃህፍቱ በሁሉም እድሜ ላሉ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች አመቺ በሚሆን ሁኔታ በድምቀት ይዘጋጃል። በዕለቱ የሚቀርበው ዝግጅት የአልባሳት ትርኢት እና መስተጋብራዊ ማሳያዎችን እና እንቅስቃሴዎችን ያካትታል።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)