መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኤፕረል 3, 2025

ሜይ 6 የላቀ የትምህርት አገልግሎት ላበረከቱ እውቅና በሚሰጥበት ሥነ-ስርዓት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። 

2025 — የላቀ የሕዝባዊ ትምህርት አገልግሎት ላበረከቱት እውቅና ለመስጠት — ማክሰኞ ሜይ 6 በሚካሄድ ዝግጅት ላይ መላው ማህበረሰብ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድን እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል። ይህ ዝግጅት ስለ ህዝባዊ ትምህርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚዘከርበት ነፃ ዝግጅት ነው።

በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ አስተማሪዎች፣ ለተማሪዎች፣ እና የማህበረሰብ አጋሮች  የላቀ እውቅና የሚሰጥበት ትልቅ ዝግጅት ነው። በዚህ ልዩ የሆነ የዘንድሮው ዝግጅት ላይ ከፍተኛ አገልግሎት ያበረከቱ ሰራተኞችን እውቅና ይሰጣል፤ እንዲሁም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱ ምርጥ መምህር፣ የአመቱን የድጋፍ አገልግሎት ሰራተኛ፣ እና የትምህርት ቦርድ የተማሪ አገልግሎት ሽልማቶችን ይሰጣል። 

ቀኑን ያስታውሱ እና ስትራትሞር የሙዚቃ ማዕከል ተገኝተው እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል፦ The Music Center at Strathmore, 5301 Tuckerman Lane in North Bethesda 6:15 p.m በሮች ይከፈታሉ፣ 6፡30 p.m. ላይ ፕሮግራሙ ይጀመራል።

ዝግጅቱ ለህዝብ ክፍት ነው። ይመዝገቡ/RSVP


ስለ ትምህርት ቤቶች የድንበር ጥናቶች የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ላይ ይቀላቀሉን።

በድንበር ጥናቶች ላይ በቅርቡ የሚደረጉ የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ቻርለስ ደብሊው ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ለመክፈት የተዘጋጁ ናቸው። በነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች ስለ ድንበር የወሰን ጥናት ሂደት እና የወደፊት ተሳትፎ እድሎች ላይ ጠቃሚ ዝርዝሮች ይቀርባሉ። ተጨማሪ መረጃ

የቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለመክፈት የሚደረግ የድንበር ጥናት

የክራወን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈቻ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የወሰን ጥናት

ምዝገባ የማያስፈልግ ቢሆንም፣ ዲስትሪክቱ እንዲዘጋጅ ለማገዝ ተሰብሳቢዎች RSVP እንዲመዘገቡ MCPS ይጠይቃል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የድንበር ጥናት ድረ ገጽ አሁን ግለሰቦች ከስምንት ቋንቋዎች በአንዱ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ ኢሜይል እንዲያደርጉ፣ እና ምላሽ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ጥያቄዎችን እዚህያቅርቡ።


የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ኤፕሪል 9 ስለ ሙያ ሥራ ቨርቹዋል የመረጃ ልውውጥ ክፍለጊዜ ያስተናግዳል።

የፌዴራል ሰራተኞችን ለመደገፍ የሚደረገውን ጥረት መሠረት በማድረግ MCPS እሮብ፣ ኤፕሪል 9 ከቀኑ 2–4 p.m. ቨርቹዋል የሙያ ስራ መረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ ያካሄዳል። ፍላጎት ያላቸው የፌደራል ሰራተኞች በዲስትሪክቱ ስለሚገኙ የስራ እድሎች የበለጠ ለማወቅ ይህንን ቨርቹዋል ስብሰባ መቀላቀል ይችላሉ። በክፍለ-ጊዜው MCPS ሪሶርሶችን ይሰጣል እና ጥያቄዎችን ይመልሳል። 

ለመሣተፍ ይመዝገቡ።


ሠመር ራይዝ መጀመር እና ደማቅ የጎልፍ ውድድር "Inaugural Summer RISE & Shine Golf Tournament" ይቀላቀሉን።

ሠመር ራይዝ እና ደማቅ የጎልፍ ውድድር "Summer RISE & SHINE Golf Tournament"ሰኞ፣ሜይ 5 የሚካሄድ ስለሆነ MCPS እና የአጋርነት ማስተባበሪያ መምሪያን በዚህ አድራሻ ይቀላቀሉ፥ አድራሻ፦ Montgomery Country Club in Laytonsville። በዚህ ዝግጅት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጁንየር እና ሲንየር ተማሪዎች በሙያ ላይ የተመሰረተ የሠመር ትምህርት እድል ለመስጠት ለሠመር ራይዝ ፕሮግራም ገንዘብ ይሰበሰባል። የጎልፍ ውድድር ከካውንቲ መሪዎች፣ ከአካባቢው የንግድ ማህበረሰቦች፣ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች እና ከተሳታፊ የሠመር ራይዝ ድርጅቶች ጋር አስደሳች የሆነ የጎልፍ ጨዋታ እና የግንኙነት መረብ ለመዘርጋት መልካም እድል የሚገኝበት ጊዜ ነው።

የቲኬት ግዢው ጎልፍ በዙር መጫወት እና ለሠመር ራይዝ ፕሮግራም ልገሳ፣ እንዲሁም የአረንጓዴ እና ክልል ጊዜን መለማመድ፣ ጎልፍ የሚጫወቱበትን ተርታ፣ የቁርስ ምግቦችን፣ ምሳ እና ከጨዋታ በኋላ የሚደረግ የሽልማት አሰጣጥ ዝግጅት ላይ መሳተፍን ያካትታል። በጊዜው ከሱፐርኢንቴንደንት የሚቀርብ ውድድር ይኖራል፣ እንዲሁም ወደ ፒን ረጅሙ ርቀት እና በጣም ቅርብ ምትን ጨምሮ ተጨማሪ ጨዋታዎችም ይኖራሉ። ዛሬውኑ ይመዝገቡ።

ድጋፍ/ስፖንሰርሽፕ ይኖራል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት የአጋርነት ማስተባበሪያ ክፍልን በስልክ ቁጥር 240-740-5599 ደውለው ይጠይቁ ወይም ለኬቪን ብራንክ/Kevin Brunk ኢሜይል ያድርጉ።

Summer RISE and SHINE


ስለ ተማሪ የአገልግሎት ትምህርት ማሳሰቢያ፦

ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአት ማግኘት አለባቸው፤ ስለዚህ የስፕሪንግ እረፍት ለተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት ሰአታትን ለማስመዝገብ አመቺ ጊዜ ነው! የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ቨርቹዋል/የርቀት እና/ወይም በአካል እየተገኙ አገልግሎት የመስጠት (SSL) እድሎችን ሞንትጎመሪ ካውንቲ የበጎ ፈቃደኞች ማዕከል ድረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ። ተማሪዎች SSL ቅጾችን፣ መመሪያዎችን፣ ሪሶርሶችን እና ሌሎችንም መረጃዎችየተማሪዎች/ቤተሰቦች SSL Hubላይ ማግኘት ይችላሉ። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክብር አገልግሎት ሰርተፍኬት (240 ወይም ከዚያ በላይ SSL ሰዓት ያላቸው ሲንየር ተማሪዎች) ወይም የሱፐርኢንተንደንት SSL ሽልማት (75-ሰዓት SSL የመመረቂያ መስፈርቶችን ያጠናቀቁ የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች) ተማሪዎች MCPS ቅጽ 560-51 ለትምህርት ቤታቸው SSL አስተባባሪ እስከ ኤፕሪል 4 ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ሌሎች SSL ቅጾች በሙሉ በተከታታይ መቅረብ አለባቸው፣ ነገር ግን አርብ፣ ሜይ 30 በኋላ መሆን የለበትም።


መጪው KID ሙዚየም ፕሮግራሚንግ

KID ሙዚየም በዚህ የስፕሪንግ/ፀደይ ወቅት ለተማሪዎች፣ ከትምህርት ቤት ሠዓት በኋላ ትምህርት እና የስፕሪንግ እረፍት ካምፕ እድሎችን ይሰጣል። እየደረሰ ነው፦

በስፕሪንግ/ፀደይ ከመደበኛው የትምህርት ሠዓት በኋላ ከ 6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የሚሰጥ ትምህርት፦ 3 Bethesda Metro Center, Bethesda, Wednesdays, 4:30-6 p.m., Invent the Future Clubበየሳምንቱ እሮብ፣4:30-6 p.m., ይካሄዳል።

የስፕሪንግ ዕረፍት ካምፕ፦ ሰኞ፣ ኤፕሪል 14 እስከ ሐሙስ፣ ኤፕሪል 17 ከጠዋት 9 a.m.- 4 p.m., KID Museum, 3 Bethesda Metro Center, Bethesda ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register


ከዜና ገፆቻችን የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ፡

በዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት "Wheaton KnightRiders" ከሮቦቶች የተሻለ የመሪነት፣ የቡድን ስራ፣ እና ችግር ፈቺ ክህሎቶችን እያዳበሩ ነው። 5115 ጋር ይገናኙ።

የትዊንብሩክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማህበረሰብ እንክብካቤ ቀን እንዴት የትምህርት ቤቱን ውጫዊ ገጽታ ለመለወጥ ወላጆችን፣ ተማሪዎችን፣ እና የአካባቢ ድርጅቶችን በጋራ እንዳሰባሰበ ይመልከቱ። ታሪኩን ያንብቡ።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)