መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኤፕረል 10, 2025

የትምህርት ቦርድ (BOE) ሶስት የመጨረሻ እጩዎችን ለተማሪዎች አገልግሎት ሽልማት ሰይሟል። ሽልማቶች በሚሰጡበት ምሽት ከእኛ ጋር ይሁኑ!

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ሶስት ተማሪዎችን ለመጨረሻ የተማሪ አገልግሎት እጩ ተሸላሚነት ሰይሟል። ይህ ሽልማት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፕሮግራሞች ከፍተኛ ጊዜ እና እውቀት ያበረከቱ፣ አርአያ የሆኑ ፕሮግራሞችን ወይም ፕሮጀክቶችን ያዘጋጁ እና/ወይም ተግባራዊ ያደረጉ፣ እና መላውን የትምህርት ስርዓት የሚጠቅም አስተዋጾ የሚያደርጉ የአሁን ተማሪዎችን በማክበር እውቅና ይሰጣል።

የመጨረሻዎቹ እጩዎች፡- German Diaz-Peña በሮክቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪ፣ Samantha (Sam) Ross፣ በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪ፣ እና Kylie Zhang በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሶፎሞር ተማሪ ናቸው።

ታሪኮቻቸውን ያንብቡ

የተማሪ አገልግሎት ሽልማት አሸናፊው ማክሰኞ፣ ሜይ 6 ቤተስዳ በስትራትሞር የሙዚቃ ማእከል በሚካሄደው የትምህርት አገልግሎት እውቅና በሚሰጥበት ፕሮግራም ላይ ይገለጻል።

ቀኑን ለማስታወስ ቀን መቁጠሪያ ላይ ምልክት አድርጉ! ህዝባዊ ትምህርት የሚሰጠውን ሃይል እና ከፍተኛ የማስተማር ባለሙያዎችን፣ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን፣ እና የማህበረሰብ አጋሮችን ለማክበር በተሰናዳው በዚህ የነጻ ዝግጅት ላይ ሁሉም የማህበረሰብ አባላት እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ዝግጅቱ የሚካሄድበት አድራሻ ኖርዝ ቤተስዝዳ ስትራትሞር የሙዚቃ ማዕከል ነው፦ The Music Center at Strathmore, 5301 Tuckerman Lane in North Bethesda. 6:15 p.m. በሮች ይከፈታሉ፤ ፕሮግራሙ 6:30 p.m. ላይ ይጀምራል።

ይመዝገቡ/RSVP


ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በነበረው ከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት፣ 2024–2025 የትምህርት አመት ወደ ማክሰኞ፣ ጁን 17 ይራዘማል፣ አርብ ጁን 13፣ ሰኞ፣ ጁን 16 እና ማክሰኞ፣ ጁን 17 ሁሉም ተማሪዎች ከመደበኛው ሰዓት በቅድሚያ የሚለቀቁበት ቀናት ይሆናሉ። ለዝርዝር መረጃ እሮብ፣ ኤፕሪል 9 ለቤተሰቦች የተላከውን የማህበረሰብ መልእክት ያንብቡ


ቀጣዩ የፈጣን እድል ምልመላ ቀን ኤፕሪል 30 ነው!

ቀጣዩ MCPS የምግብ እና የአልሚ ምግብ አገልግሎት ክፍል የፈጣን እድል ምልመላ በዚህ አድራሻ ይካሄዳል፦ Division of Food and Nutrition Services (DFNS), 8401 Turkey Thicket Drive in Gaithersburg አዲሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተንቀሳቃሽ የሥራ ፈላጊዎች ምልመላ ተሽከርካሪ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 30 ከጠዋቱ 8፡30–11 a.m. ለምግብ አገልግሎት ክፍል (DFNS) እና የጥገና እና ኦፕሬሽንስ ክፍል ውስጥ ለሚሰሩ ስራዎች ሥራ ፈላጊዎችን ይቀጥራል። ፈጣን የሥራ ዕድል "ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ" ዲስትሪክቱ ያለውን የስራ ክፍት ቦታ ለማስተዋወቅ በካውንቲው ውስጥ የተለያዩ ቦታዎችን ይዞራል። ማስታወቂያውን ለጓደኞችዎ እና ለጎረቤቶችዎ ያሰራጩ፣ እና ኤፕሪል 30 በሚካሄደው አዲስ የስራ እድል ይቀላቀሉን!

"ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ" ኤፕሪል 30, 2025 ይካሄዳል።


የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ አሁን ተከፍቷል።

Summer School 2025 ምዝገባ ክፍት ነው። እባክዎ ለመመዝገብ የተማሪዎን ትምህርት ቤት ካውንስለር ያነጋግሩ። በአካል የሚገኙበት የሰመር ትምህርት ፕሮግራም በሁለት ክፍለ ጊዜዎች ይካሄዳል—ከጁን 30 እስከ ጁላይ 18 እና ከጁላይ 22 እስከ ኦገስት 8። —በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። በየቀኑ ከጠዋቱ 8 a.m.–12:30 p.m. ትምህርት ይሰጣል፥ ቨርቹዋል አማራጮችም አሉ። ተጨማሪ መረጃ

የሠመር ትምህርት ተማሪዎች በአካዳሚክ ትምህርት ላይ እንዲያተኩሩ ወይም ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ እድል ይሰጣል። ስለ ክፍያዎች፣ ስለ ሌሎች የሠመር ፕሮግራሞች፣ እና የትምህርት ክሬዲት የማሟላት አማራጮች ዝርዝሮችን ለማግኘት MCPS የሠመር ትምህርት ቤት ድረገጽ ይጎብኙ።


ቪዡዋል አርት ማዕከል 50ኛ አመቱን ሜይ 16 ያከብራል።

ቪዡዋል አርት ማዕከል (VAC) በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 50ኛ አመቱን አርብ፣ ሜይ 16 በትምህርት ቤቱ ካለው አመታዊ የስነጥበብ ትርኢት ጋር ያከብራል።

ዝግጅቱ 5-6 p.m. VAC የታሪክ ምሁር እና የቀድሞ VAC የስነጥበብ መምህር ጄን ዋልሽ/Jane Walsh ጋር የሰላምታ ጊዜን ያካትታል፣ እና የስነጥበብ ትርኢት እና 6-8 p.m. የቀድሞ ተማሪዎች ፕሮግራም ይቀጥላል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቪዥዋል አርት ማዕከል በካውንቲው ውስጥ በጣም ጥንታዊ እና ለብዙ ዘመናት የተካሄደ የማግኔት ፕሮግራም ነው። ይህ በአገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የፖርትፎሊዮ ዝግጅት ፕሮግራም Honors-AP level፣ ቅድመ-ኮሌጅ፣ የስነጥበብ ፖርትፎሊዮ ልማት ካውንቲ አቀፍ ፕሮግራም ነው። ከ 1974 ጀምሮ በ 50 ዓመት ታሪክ ሰባት አስተማሪዎች ብቻ አሉት።

ይመዝገቡ/RSVP


ሜይ 2 የግንባታ ሙያ ስራዎችን ይቃኙ

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጁንየሮች እና ሲንየር ተማሪዎች በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ እየተፈለፈለጉ ያሉ ሙያዎችን ለመቃኘት አርብ፣ ሜይ 2 ቀን እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ሞንትጎመሪ ኮሌጅ በጀርመንታውን ካምፓስ ከጠዋቱ 10፡30 a.m.–1፡30 p.m የሰለጠነ የንግድ ሥራ ቀንን ያስተናግዳል።

ዝግጅቱ MCPS እና Clark Construction በትብብር ያዘጋጁት ነው። ተማሪዎች እጅግ የሚጠቅም የስራ እድሎችን ማሰስ፣ የግንባታ ስራ ልምድ የመቃኘት እና ከኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር መገናኘት ይችላሉ።

ተማሪዎች እስከ ሰኞ፣ ኤፕሪል 28 ድረስ እንዲመዘገቡ ይጠየቃሉ። መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የትምህርት ቤታቸውን የኮሌጅ እና የስራ መረጃ አስተባባሪ (CCIC) ማነጋገር አለባቸው።

የሰለጠነ የንግድ ሥራ ቅኝት ቀን፣ ሜይ 2, 2025


የአእምሮ ጤና እና ደህንነት አውደ ርዕይ ለኤፕሪል 26 ተዘጋጅቷል።

MCPS ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 26 በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Montgomery Blair High School, 51 University Blvd. የጥቁሮች የአእምሮ ጤና እና ደህንነት አውደ ርዕይ ያካሄዳል። ሲልቨር ስፕሪንግ በስተምስራቅ East in Silver Spring. ዝግጅቱ ነፃ እና ለሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች፣ እና ሰራተኞች ክፍት ነው። ስለ አእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መረጃ ይሰጣል።

ዋና ተናጋሪው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ጤና አገልግሎት ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ኒና አሽፎርድ ናቸው። Dr. Nina Ashford, Chief of Public Health Services for Montgomery County. የዎርክሾፕ ርእሶቹ የሚያካትቱት፦ በወቅታዊ የማህበራዊ ሚድያ አውድ ወጣት የትምህርት ቤት ልጆችን የወላጅነት መርሆዎች፣ ራስን መንከባከብ መለማመድ + ጤናማ ልማዶች እና አበረታች እርዳታ የመፈለግ ባህሪ፣ ውጥረትን መቋቋም (ለተማሪዎች)፣ እና የዲጂታል አጠቃቀም የሚፈጥረው የአእምሮ ጭንቀት እና በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን ስለሚከሰት የአእምሮ ጤንነት ።

ይመዝገቡ/RSVP


ከዜና ገጾቻችን የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች እንዳያመልጥዎት


የካውንቲው የደህንነት ቀን ሜይ 10 ይካሄዳል።

የሞንትጎመሪ የትራንስፖርት መምሪያ ሁሉንም የ MCPS ቤተሰቦች ቅዳሜ፣ ሜይ 10ከጠዋቱ 11 a.m.–3 p.m. የደህንነት ቀን ለማክበር በካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማእከል እንዲገኙ ጋብዟል አድራሻ፦ Carver Educational Services Center parking lot, 850 Hungerford Drive in Rockville. የደህንነት ቀን ሳቅና ጨዋታ የተሞላበት ስለ ትራፊክ ደህንነት የበለጠ ለማወቅ ማህበረሰቡን የሚያሰባስብ ለቤተሰብ ተስማሚ የሆነ ዝግጅት ነው። ዝግጅቱ ለሁሉም ዕድሜ ተስማሚ ነው፣ በደርዘን የሚቆጠሩ እንቅስቃሴዎች እና የማህበረሰብ አጋሮች የተለያዩ ስጦታዎችን እና ሽልማቶችን ይዘው ይሳተፋሉ። ለተሳታፊዎች ነፃ የማመላለሻ አውቶቡሶች በሴኔካ ቫሊ፣ በጌትስበርግ፣ እና በጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። ተማሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት የተማሪ አገልግሎት የመማሪያ ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። ቅዳሜ፣ ሜይ 17 የዝናብ ቀን ነው።

ሜይ 10, 2025 የደህንነት ቀን


ቀኑን ያስታውሱ፦ ያገለገሉ መኪናዎች እና ኮምፒውተሮች ሽያጭ ሜይ 10 ስለሚካሄድ ቀኑን እንዳይረሱት ይመዝግቡ።

በትምህርት አመቱ የመጨረሻው ያገለገሉ መኪናዎች እና ኮምፒውተሮች ሽያጭ ቅዳሜ ሜይ 10 ከጠዋቱ 9–11 a.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል፡ አድራሻ፦ Thomas Edison High School of Technology, 12501 Dalewood Drive in Silver Spring

በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች አውቶሞቲቭ ትሬድ ፋውንዴሽን (ATF) እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (ITF) ያገለገሉ መኪናዎችን እና ኮምፒውተሮችን የትምህርታቸው እና የላብራቶሪ ጥናታቸው አካል አድርገው ይሸጣሉ። ሽያጩ እየተቃረበ ሲመጣ ተጨማሪ መረጃ እና ዝርዝር እዚህ ይለጠፋል።


ማሳሰቢያ

የተከታታይ ነጻ የኮሌጅ እና የሙያ ስራ እቅድ ዌብናሮች ይሰጣሉ፡ACT የእኔ የኮሌጅ ጉዞ እና የሙያ ስራ እቅድ በተከታታይ የሚሰጥ ነፃ ቨርቹዋል ዝግጅት ነው። ረቡዕ፣ ኤፕሪል 16 ከቀኑ 7:30 p.m. በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እየተማሩ የሚገኙትን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስኬት፣ ለኮሌጅ፣ እና ከዚያም በላይ ለሚተልሙ የኮሌጅ አቀፍ ዝግጅቶች ላይ ይሣተፉ። የበለጠ ይወቁ እና ይመዝገቡ

ACT የእኔ ጉዞ - የኮሌጅ እና የሙያ ስራ እቅድ ዝግጅት 2025

KID ሙዚየም ፕሮግራሚንግ፡ የተማሪዎች መጪ እድሎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

Ride On የሚከበርበት ቀን፡ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ 50 ዓመታት የራይድ ኦን አውቶብስ አገልግሎትን የሚያከብሩ የጥበብ ስራዎችን ማቅረብ ይችላሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት ውድድር ያካሄዳል። ተሳታፊዎች አምስት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰአት ያገኛሉ፣ እና ሶስት ምርጥ አሸናፊዎች የስጦታ ካርዶችን ያገኛሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። የመወዳደሪያ አርት መቅረብ ያለበት ቀነ ገደብማክሰኞ፣ ኤፕሪል 15እስከ 11:59 p.m. ነው።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)