መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ሜይ 15, 2025

የድንበር ጥናት ተሳትፎ ክፍለ-ጊዜዎች ሜይ እና ጁን ላይ ይደረጋሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ ስለ ቻርልስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዳግም መከፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መከፈት፣ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፋፋት ላይ ያተኮሩ ቀጣይ የተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። እነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች ስለ እያንዳንዱ ጥናት የመጀመሪያ አማራጮችን ይመለከታሉ፤ እና የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ባሏቸው ቤተሰቦች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ለውጦች ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ውይይት ይደረጋል። የስብሰባዎቹ ጊዜያት ለአንድ ሰዓት ያህል የሚቆዩ ናቸው። 

ቨርቹዋል ወይም በአካል ክፍለ ጊዜ ላይ ለመሳተፍ ያሉትንእድሎች ይቃኙ።


ኤዥያን አሜሪካውያን እና የፓሲፊክ ደሴት ታሪካዊ ቅርስ ወር ይከበራል

አንዳንድ ጊዜ፣ የህይወት ጥልቅ ጉዞዎች የሚጀምሩት በሆነ አጋጣሚ ነው። ሎርደስ ፌረር (Lourdes Ferrer) በአቋራጭ መንገድ የጀመረችው — አቋራጭ የምዝገባ እጋጣሚ — የእርሷን ዕድል ብቻ ሳይሆን የምታስተምራቸውን እና የምታስጠናቸውን ህይወት ጭምር የቀረጸ የእድሜ ልክ ጥሪ ሆኗል። ኤዥያውያን አሜሪካውያን እና የፓሲፊክ ደሴት ታሪካዊ ቅርስ የሚዘከርበት ወር፣ ስለ ፈረር ታሪክ የተረጋጋና ድፍረት የተሞላበት እርምጃ፣ ጥልቅ እምነት፣ እና በሌሎች — እና በራስዎ የመተማመን የለውጥ ሃይል ነው። 


ጊዜው ደርሷል!

የመመረቂያ ቆቦችን መነሳነስ የመቀልበስ ጊዜ ተቃርቧል። የዚህ አመት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የምረቃ ስነስርአት እሮብ፣ ሜይ 28 በዊተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይጀመራል፣ በመቀጠል ሜይ 29 ዊንስተን ቸርችል እና ኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ RICA እና Blair Ewing የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርአቶች ይካሄዳሉ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርአቶች እስከ ሐሙስ፣ ጁን 12 ድረስ ይቀጥላሉ። ሥነ ሥርዓቱ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካምፓሶች፣በዋሽንግተን ዲሲ "DAR Constitution Hall"፣ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ XFINITY ሴንተር፣ በኮሌጅ ፓርክ፣ Mount St. Mary’s University፣ እና በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ባልቲሞር ካውንቲ ይደረጋል።

ስለ እያንዳንዱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤት የምረቃ ስነ ስርአት የሚካሄድባቸውን ቀኖች፣ ቦታዎችን፣ ሰዓቱን፣ እና ንግግር የሚያደርጉትን የክብር እንግዶች ዝርዝር ይመልከቱ። 


የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ሪፖርት የሚቀርብበት ቀነገደብ አርብ፣ ሜይ 30 ነው።

ከጁን 1, 2024 ጀምሮ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያጠናቀቁ ተማሪዎች አስፈላጊውን SSL እንቅስቃሴ ማረጋገጫ ቅጽ ለት/ቤታቸው SSL አስተባባሪ በሚፈለገው አርብ፣ ሜይ 30 የመጨረሻ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው።

ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል። የሠመር ዕረፍት ጊዜ ተማሪዎች በእነዚህ እድሎች የሚሳተፉበት ጥሩ ጊዜ ነው። ማቅረብ ስለሚጠበቅባቸው ማስረጃ የበለጠ ለማወቅ እና በአካል ተገኝተው የሚሠሩበት ወይም የቨርቹዋል/የርቀት SSL እድሎችን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ። የተተረጎሙ ቅጾች እዚህ ይገኛሉ። ተማሪዎች የተመዘገበላቸውን SSL ሪከርዳቸውን፣ ቅጾችን፣ መመሪያዎችን እና ሌሎች ሪሶርሶችን MCPS SSL Hub for Students/Families ላይ ማግኘት ይችላሉ። 


B-CC የኩሩ ማህበረሰብ ቀን ጁን 1 ይካሄዳል።

የኩሩ ማህበረሰብ ቀን እሁድ፣ ጁን 1 ቤተስዳ-ቼቪ ቼዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ 1-4 p.m. ይካሄዳል።

ለሁሉም ዕድሜ ክፍት ነው። በዚህ ዝግጅት ላይ የተለያዩ ተግባራት ይቀርባሉ፦ ትራንቪያ፣ ቢንጎ፣ አርት እና እደ ጥበባት፣ እንዲሁም ለወጣት ተማሪዎች የታሪክ ክፍለጊዜ (በመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያነብላቸዋል)።(variety of activities፡ trivia, bingo, arts and crafts, and story time for younger students) በሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ጤና አገልግሎት የሚቀርቡ "Live In Your Truth, Team DC, MoCo Pride Center and SMYAL" ጭምር በማህበረሰብ ድርጅቶች የሚቀርቡ የተለያዩ የመርጃ ጽሑፎችም ይኖራሉ።

ዝግጅቱ የሚካሄድበት አድራሻ፦ Bethesda-Chevy Chase is located at 4301 East-West Highway in Bethesda.

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የኩሩ ማህበረሰብ ቀን "MCPS Pride Community Day"


ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

MCPS በትምህርት ቤቶች ቅጥር ግቢ ላይ እና MCPS በሚያካሄዳቸው የተለያዩ ዝግጅቶች ወቅት ተማሪዎች የግል ሞባይል መሳሪያዎችን—ሞባይል ስልኮችን፣ ኢ-አንባቢዎችን፣ ስማርት ሰዓቶችን፣ ታብሌቶችን፣ በሰውነት የሚጣበቁ ቴክኖሎጂዎችን፣ ቪዲዮ እና ኦዲዮ መቅረጫዎችን፣ እና የመጫወቻ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው የሚገልጽ መመሪያን አሻሽሏል። የተሻሻለው ደንብ 2025-2026 የትምህርት አመት ላይ ተግባራዊ ይሆናል። ምናልባት ካመለጠዎት፣ ሜይ 9 ለህብረተሰቡ የተላከውን መልእክት ያንብቡ። 


የስፕሪንግ/ፀደይ የወላጅ አካዳሚ መርሃ ግብር አሁን ተዘጋጅቷል።

ቤተሰቦች እና ተማሪዎች በትምህርት ዓመቱ በሙሉ ከፓረንት አካዳሚ-Parent Academy TO GOጋር ተጎዳኝተው መቆየት አለባቸው። ፓረንት አካዳሚ-"Parent Academy TO GO" ማለት ቤተሰብ እቤታቸው እንዲመለከቱ በቪድኦ የሚቀርብ ቨርቹወል ውይይት ነው።

የሜይ እና ጁን ዌብናር የወላጅ አካዳሚ ድረገጽ ላይ ይገኛሉ። እዚህይመዝገቡ።


10 ደቂቃ ውስጥ ስለ ሕይወት አድን CPR ይማሩ።

CPR መማር እየፈለጉ ነገር ግን ለመማር ጊዜ አላገኙም? የሜድስታር የጤና ባለሙያዎች፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ መከላከያ አገልግሎት ሠራተኞች፣ እና MCPS የአትሌቲክስ አሰልጣኞች በእጅ-ብቻ CPR እና AED ወርክሾፕ ቅዳሜ፣ ጁን 14ከጠዋቱ 11 a.m.-1 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነጻ ስልጠና ይሰጣል። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ CPR በመማር ድንገት ሰዎችን ለመርዳት እንዲችሉ ይምጡና ይሰልጥኑ ማህበረሰብዎን ይርዱ! ምንም የምስክር ወረቀት አያስፈልግም — ህይወት አድን ክህሎት ለመማር 10 ደቂቃ ብቻ ይውሰዱ። በሜድስታር የጤና አገልግሎት፣የሞንትጎመሪ ካውንቲ የእሳት አደጋ መከላከያ፣MCPS እና Alpha Kappa Alpha Sorority, Inc., Theta Omega Omega Chapter በትብብር የተዘጋጀ የአጭር ደቂቃዎች ስልጠና ፕሮግራም ነው። እባክዎ ለመሳተፍ ይመዝገቡ


ማሳሰቢያ

የኬኔዲ ብሎክ ፓርቲ፦ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅዳሜ፣ ሜይ 17 ቀን ከቀትር እስከ 4 p.m. ድረስ የብሎክ ፓርቲ አዘጋጅቷል። አድራሻው፦ John F. Kennedy High School at 1901 Randolph Road in Silver Spring. በዝግጅቱ ላይ ለመሳተፍ ነፃ ነው (አቅርቦቱ እስከሚያልቅ ድረስ በነፃ ምግብ እና መጠጦች ይኖራሉ)፣የማህበረሰብ መገልገያ ሪሶርሶች፣ ጨዋታዎች፣ እና አዲስ የተሾሙትን ርዕሰ መምህር ካርላ ሎፔዝ-አሪያስ ጋር መገናኘት እና ሰላምታ የመለዋወጥ ጊዜ ይኖራል።

የጌይተርስበርግ የመፅሀፍ አውደርዕይ፦ ለቅዳሜ፣ ሜይ 17፣ ከ 10 a.m. to 6 p.m. ድረስ ተዘጋጅቷል፣ በቦህረር (Bohrer) ፓርክ፣ 506 ኤስ. ፍሬድሪክ ጎዳና፣ በጌይተርስበርግ። ከሼዲ ግሮቭ ሜትሮ ስቴሽን እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፌርግራውንድስ የሚመጡ ሻትል መጓጓዣዎች ነፃ ናቸው። ይህ ዝግጅት ከ 100 በላይ ፀሀፊዎች ለንግግሮች፣ ፓናል ውይይቶች፣ ፕሮግራሞች፣ ለህፅናት፣ ለታዳጊዎች፣ ለአዋቂዎች አውደ ጥናቶች፣ እና ማንበብ፣ መፃፍ እና በስዕል መግለፅን የሚያበረታቱ ተግባራይን ያካተተ ነው።

ስለ ልዩ ትምህርት የዳሰሳ ጥናት/Special Ed Survey፦በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የልዩ ትምህርት አገልግሎት የሚሰጠው/የሚሰጣት ልጅ ካለዎት፣ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት እስከ አርብ፣ ሜይ 30 ድረስ ከእርስዎ መስማት ይፈልጋል።


ዜና ገፃችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)