ሥራችን እንዴት ነው? ይንገሩን!
MCPS ስለ ትምህርት ቤት አውድ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ቤተሰብዎ በትምህርት ቤቶቻችን ስላለው ልምድ የበለጠ ማወቅ ይፈልጋል። እንደ አጠቃላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤት አውድ እይታ በማገናዘብ — ከደህንነት እና ግንኙነት እስከ መማር እና ማስተማር ያለዎትን ግንዛቤ ይግለጹልን። በደንብ የምንሰራውን እና ምን ማሻሻል እንደምንችል በመረዳት፣ ለሁሉም ተማሪዎቻችን የበለጠ አጋዥ እና አሳታፊ ሁኔታዎችን መፍጠር እንችላለን። የዳሰሳ ጥናቱ የሚዘጋው ሰኞ፣ ጁን 9 ስለሆነ እባክዎን ዛሬውኑ ሞልተው ይመልሱልን! (የዳሰሳ ጥናቱን መጠይቅ ለመሙላት፣ የተማሪዎ መታወቂያ ቁጥር ያስፈልግዎታል፣ ይህም ParentVue ላይ ይገኛል።) የትምህርት ቤት አውድ ነገሮች እንዴት እንደሚከናወኑ ብቻ ሳይሆን … በጋራ/በመተባበር እንዴት የበለጠ ማሻሻል እንደምንችል ነው።
የክራወኒግ ስኬት
በዚህ አመት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማ የሚያገኙ ወደ 13,000 የሚጠጉ ተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ተጀምሯል። ዊተን፣ ዊንስተን ቸርችል፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ አልበርት አንስታይን፣ ዛዶክ ማግሩደር፣ ደማስከስ፣ ሴኔካ ቫሊ፣ እና ሼርውድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፣ RICA እና Blair Ewing የምረቃ ሥነ ስርአት ካከናወኑት የመጀመሪያዎቹ ናቸው። የምረቃ ሥነ ስርአቱ እስከ ሐሙስ፣ ጁን 12 ድረስ ይቀጥላል።
የምረቃ ሥነ ስርአት በሚካሄድበት ወቅት ላይ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ፣ የ NBC ዜና ዘጋቢ፣ የቀድሞ NFL ተጫዋች፣ የችሎታ ቃለመጠይቅ አቅራቢ፣ የዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ እና ሞዴል፣ እውቅ የትምህርት ባለሙያዎች፣ የቢዝነስ ባለቤቶች እና ፖለቲከኞችን ጨምሮ የተለያዩ ተናጋሪዎች ይገኛሉ።
ከእንግሊዘኛ ቋንቋ የተለየ በአንድ ወይም በብዙ ቋንቋዎች ከፍተኛ ብቃት ያስመዘገቡ 2,500 በላይ ተመራቂዎች “Seal of Biliteracy” ሽልማት ያገኛሉ። ሰማንያ ሶስት ተመራቂዎች ባሳዩት የብዝሃ ቋንቋ ችሎታና ብቃት ሽልማት አግኝተዋል። በዚህ አመት ተማሪዎች ወደ 50 በሚጠጉ ቋንቋዎች ተፈትነዋል።
የምረቃ ቀናት፣ጊዜ/ሠአት፣ንግግር የሚያደርጉ እንግዶች፣ እና የምረቃ ሥነ ስርአት የሚካሄዱባቸው ቦታዎች ዝርዝር.
"GIVE Backpacks" ዘመቻ እየተካሄደ ስለሆነ ዛሬውኑ ይለግሱ
14ኛው አመታዊ GIVE BACKpacks ዘመቻ በመካሄድ ላይ ስለሆነ፥ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በጀርባ የሚያዝ የደብተር/የመጻህፍት ቦርሳዎችን እና የት/ቤት ቁሳቁሶችን በመግዛት የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው። በትንሹ $20 ዶላር በመለገስ፣ ወረቀት፣ እርሳሶች/ እስክሪብቶዎች፣ የእርሳስ መቅረጫ፣ የወረቀት ፋይል፣ እና ሌሎችም ቦርሳ ላይ የታጨቀ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለተማሪ መርዳት ይችላሉ።
ከ 70,000 በላይ ተማሪዎቻችን በገንዘብ ድህነት ውስጥ ይኖራሉ፤ በአዲሱ የትምህርት አመት መጀመሪያ ላይ ለመማር ዝግጁ እንዲሆኑ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለማግኘት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በሠመር ወቅት በተቻለ መጠን ለበርካታ ተማሪዎች በቦርሳ የታጨቀ የትምህርት ቤት ቁሳቁሶችን ለማቅረብ የታለመ ስለሆነ MCPS የትምህርት ቁሳቁስ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ይሰጣል። ጁን፣ ጁላይ፣ እና ኦገስት ገንዘብ ለማሰባሰብ እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ግዢ ለማቀላጠፍ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ወሳኝ ወራት ናቸው።
ስለ "MCPS GIVE Backpacks" በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችFAQs about MCPS GIVE BACKpacks
ከዲጂታል ብዝበዛ ልጆችን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ለማወቅ ይቀላቀሉን።
በዲጂታል ብዝበዛ ላይ ያተኮረ ዌቢናር ማክሰኞ፣ ጁን 10 ከቀኑ 6-7፡30 p.m. ይካሄዳል። ከሴክስቶርሽን ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን፣ ወቅታዊ አዝማሚያዎችን፣ የልጅዎን የኦንላይን አጠቃቀም ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ እና ልጅዎ ተጋላጭ እና ተጎጂ ከሆነ(ች) የሚወስዷቸውን እርምጃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል።
ይህ ዌቢናር MCPS፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት፣ ዩ.ኤስ የፍትህ ዲፓርትመንት፣ ዩ.ኤስ የአገር ውስጥ ደኅንነት መምሪያ፣ እና የጠፉ እና የተበዘበዙ ልጆች ብሔራዊ ማዕከል በትብብር የሚያካሄዱት ነው።
English | Spanish | Chinese | French | Portuguese | Korean | Vietnamese | አማርኛ
የሠመር የምንባብ ውድድር ጁን 14 ይጀመራል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ መፃህፍት አመታዊ የሠመር ምንባብ ውድድር ቅዳሜ፣ ጁን 14 ያካሄዳል። ልጆችን፣ ወጣቶችን እና ጎልማሶችን በመፃህፍት፣ በሙዚቃ፣ በቲያትር እና በኪነጥበብ ወደ “የዓለማችን ሕብረ-ቀለም/“Color Our World” ይጋብዛል። መርሃግብሩ እስከ እሑድ፣ ኦገስት 31 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ይህም ለሁሉም ዕድሜ የምንበብ እና የፈጠራ ስራዎችን እሳቤ እና ራስን የመግለጽ እድል ይሰጣል።
ለሁሉም ዕድሜ ተስማሚ ተግባራትን የሚያሳዩ ሶስት ዝግጅቶች ይኖራሉ።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት እና ለመመዝገብ MCPL ድረገጽ ይጎብኙ።
ማሳሰቢያ
የሥነ ምግባር ፓነል፡ የትምህርት ቦርድ አምስት አባላት ባሉት ፓነል ላይ አንድ ክፍት የስራ ቦታ አለው። ከጁላይ 1፣2025 ጀምሮ ክፍት ቦታው የሚሸፈነው ለሶስት አመት የአገልግሎት ጊዜ ነው። ለማገልገል የሚፈልጉ ግለሰቦች ደብዳቤ እና የስራ ልምድ መግለጫ/resumés እስከ ሰኞ፣ ጁን 9ከቀኑ 5 p.m. ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
Flick ጋር ይተዋወቁ፡ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከኢንጂነሮች እና አስተማሪዎች ጋር በመተባበር የገሃዱን ዓለም ችግሮችን ቢፈቱ ምን ይከሰታል? ከ Hallie Wells መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተውጣጡ ተማሪዎች የተነደፈ፣ የተገነባ፣ እና ፕሮግራም የተደረገለት AI የሚደገፍ የሂሳብ ትምህርት ያገኛሉ።
ከሥነ ሥርዓቱ በላይ፡የሮቤርቶ ክሌሜንቴ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 8ኛ ክፍል ብሎክ ፓርቲ ጋር ማህበረሰብን እንዴት እየገነባ እንዳለ ግንዛቤ ያግኙ።
በዜና ገጻችን ላይ በዲስትሪክቱ ዙሪያ ያሉ ወቅታዊ ሁነቶችን ስለምናቀርብ፣ የቅርብ ጊዜውን መረጃ ለማግኘት ይህን ድረገጽ ይከታተሉ።
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org