አበይት ጉዳዮች
ጁላይ 24, 2025
|
|
ሥራ ፈላጊዎችን እንቀጥራለን! – የወደፊት ዕጣዎ ከ MCPS ጋር ነው።
MCPS ጥልቅ ፍላጎት ያላቸው ለመልካም ዓላማ ጊዜና ጉልበታቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ግለሰቦችቡድናችንን እንዲቀላቀሉ ይፈልጋል ልምድ ያካበቱ አስተማሪም ይሁኑ ወይም አዲስ የስራ መስክ ፈላጊም ቢሆኑ ለእርስዎ የሚሆን ቦታ አለን።
ከችሎታዎ እና ከፍላጎትዎ ጋር የሚዛመዱ እና በተማሪዎች ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ተጽእኖ የሚፈጥሩ ልዩ አሠልጣኝ/አስተማሪ፣ ፓራዲኬተርን፣ የደህንነት እና የመጓጓዣ ሥራዎችን ጨምሮ ያሉትንእድሎች ይቃኙ።
|
|
|
ኮሌጅ ለማመልከት እገዛ ይፈልጋሉ? እዚህ ይጀምሩ
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው በዚህ ሠመርየኮሌጅ ዝግጁነት አውደ ጥናቶችን መቃኘት ይችላሉ።
ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁነት እቅድ የተለያዩ መረጃዎችን እና ግብዓቶችን ለመስጠት ነጻ አውደጥናቶች ኦገስት ላይ ይካሄዳሉ። የፋይናንሺያል እርዳታ ቅጾችን፣ SAT እና ACT strategies ለመሙላት እርዳታ ከፈለጋችሁ ወይም የኮሌጅ አፕሊኬሽን ጽሑፍ የመጻፍ ፍላጎታችሁን ለማሟላት የሚያስችል አውደ ጥናት ይካሄዳል።
|
|
|
ልጆች ነፃ የሠመር ምግብ መውሰድ ይችላሉ — የት መሄድ እንዳለብዎት እነሆ!
ዕድሜያቸው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በታች ለሆኑ ልጆች የሠመር ምግብ አገልግሎት ይሰጣል። ተማሪዎች ከሰኞ እስከ አርብ ምንም ወጪ የማይጠይቁ ጤናማ እና የተመጣጠነ ምሳ በካውንቲው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ማግኘት ይችላሉ።በ 2025 የሠመር ምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ጣቢያዎችን ዝርዝር ይመልከቱ። ምንም ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግም። ምግቦቹን በቦታው መመገብ አለባቸው።
የሠመር ምግብ ፕሮግራም ድረገጽ ይጎብኙ።
|
|
|
ለትምህርት ቤት ዝግጁ ነዎት? ክትባቶችን እንዳትዘነጉ/እንዳትረሱ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ (DHHS) እስከ ሴፕቴምበር ድረስ ወደ ትምህርት ቤቶች ለሚመለሱ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጆች በካውንቲው የተለያዩ ቦታዎች ክትባቶችን በነፃ ይሰጣል።
ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
የሚዝናኑበት አውደርዕይ እንዳያመልጥዎት — ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ አውደርዕይ እየተቃረበ ነው!
MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 23 ከጠዋቱ 10፡00 a.m እስከ 1 p.m. አመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ በሚከተለው አድራሻ ያስተናግዳል፦ Westfield Wheaton mall (11160 Veirs Mill Road in Wheaton) ስለ ትምህርት ስርዓቱ፣ ስለ ካውንቲ ፕሮግራሞች፣ እና ስለሚሰጡት አገልግሎቶች ጭምር ለማወቅ ይቀላቀሉን። ለልጆች የተዘጋጁ እንቅስቃሴዎች፣ ሙዚቃ፣ መዝናኛ እና ስጦታዎችን በመቀበል ይደሰቱ። የልጆች ክትባት የሚሰጥበት ክሊኒክ ይኖራል
በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ይከታተሉ።
|
|
|
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
ብሔራዊ የምሥጋና-ሽልማት ስኮላርሺፕ፡ አምስት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በኮሌጅ ወይም በዩኒቨርሲቲ የተደገፈ የመጨረሻውን ዙር ስኮላርሺፕ አግኝተዋል፣ይህም በዚህ የትምህርት አመት አጠቃላይ ከ MCPS በዚህ ዘርፍ ስኮርላሽፕ ያገኙ ምሁራንን ቁጥር 45 አድርሷል።
የወርቅ ሽልማት ወደ ቤት ማምጣት፦ Kian Dhawan፣በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ 2025 USA Biolympiad ብሔራዊ የፍጻሜ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።
ፓት ኦኔይልን መዘከር፦ የትምህርት ቦርድ "15 W. Gude Drive" አድራሻ የሚገኘውን የቦርድ መሰብሰቢያ ክፍል ለሟቿ ፓትሪሺያ ኦኔይል ክብር በመስጠት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ለሰፊው ማህበረሰብ ያበረከቱትን አስደናቂ አገልግሎት በአክብሮት ዘክሯል።
በዜና ገጻችን ላይ በዲስትሪክቱ ዙሪያ ያሉ ወቅታዊ ሁነቶችን ስለምናቀርብ፣ የቅርብ ጊዜውን መረጃ ለማግኘት ይህን ድረገጽ ይከታተሉ።
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
ከ MCPS የበለጠ መረጃ
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|