አበይት ጉዳዮች
ጁላይ 31, 2025
|
|
በብሔራዊ የምሽት እለት ይቀላቀሉን! MCPS ጋር ማህበረሰቡን ያክብሩ
ማክሰኞ፣ ኦገስት 5 በሚካሄደው የብሔራዊ ምሽት መውጫ ቀን MCPS ይቀላቀሉ፦
- አድራሻ፦ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ጀርመንታወን ካምፓስ፣Montgomery College, Germantown Campus, 20200 Observation Drive, Germantown።
ሠዓት፡ 5–8 P.M.
- Mt. Calvary Baptist Church, 608 North Horners Lane, Rockville
ሠዓት፡ 6–8:30 P.M.
ብሔራዊ ውጪ የማምሸት ፕሮግራም ለማህበረሰብ አጋሮች እውቅና እና አክብሮት ይሠጣል፣ እና የመኖሪያ ሰፈሮች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ሳቢ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሆኑ ለማድረግ ወዳጅነትን ያጠናክራል። ዝግጅቶቹ ዝናብ ወይም ብራ ቢሆንም ይካሄዳሉ፣ ምግብ የሚያከፋፍሉ ተሽከርካሪዎች ይኖራሉ፣ በአካባቢው ሻጮችን እና ለሁሉም ዕድሜ አስደሳች እና አዝናኝ እንቅስቃሴዎችን ያካትታሉ።
|
|
|
የሽግግር ቀን ኦገስት 25 እየመጣ ነው - ይህ ምን ማለት ነው?
የተማሪ የሽግግር ቀን ማለት በ 2025-2026 አመት የትምህርት ካላንደር ሙሉ ቀን የሚከናወን አዲስ ተነሳሽነት ነው። ይህ ማለት ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳቸው በፊት የት/ቤት ባለድርሻ አካል መሆናቸውን፣ የእርስ በርስ ትውውቅ፣ እና ለትምህርት ዝግጁነትን በማጎልበት ወደ አዲሱ ትምህርት ቤታቸው ወይም ህንፃዎች የሚገቡትን ተማሪዎች ሽግግር ለማመቻቸት የተቀየሰ የሽግግር ተግባር ነው።ይበልጥ ለማወቅ ይህን በይነመረብ ይመልከቱ፦
Learn More
|
|
|
ጨዋታ ላይ ይግቡ! የአትሌቲክስ ምዝገባ አሁን ተጀምሯል፣ ማጣሪያ ኦገስት 13 ይጀመራል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል ወቅት/የበልግ ጊዜ ስፖርት ምዝገባ ክፍት ነው። ወላጆች ተማሪዎቻቸውን በዚህ በይነመረብ ኦንላይንParentVue ማስመዝገብ አለባቸው። የፎል ወቅት/የበልግ ጊዜ ስፖርቶች ማጣሪያ እሮብ፣ ኦገስት 13 ይጀምራሉ። የተለያዩ ስፖርቶችን በሚመለከት መረጃ ለማግኘት፣ በትምህርት ቤትዎ የሚገኘውን የአትሌቲክስ ዳይሬክተር ያነጋግሩ።
ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
የሠመር ወቅት ገና አላበቃም፣ ስለዚህ SSL ሰዓቶችን ለማግኘት ጥረታችሁን ቀጥሉ!
በኦገስት ወር ያሉ ዕድሎች በስቴት የምረቃ መስፈርት መሠረት 75-ሰአት ለማግኘት አሁንም ተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ለማስመዝገብ ማገልገል ይችላሉ።
አምስተኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች SSL ሰዓቶችን ማግኘት መጀመር ይችላሉ። MCPS SSL ድረ-ገጽ ላይ የተለጠፉትን መመሪያዎች የሚከተሉ አንዳንድ በአካል ተገኝተው ወይም ከርቀት አገልግሎት መስጠት የሚችሉበት እድሎች አሉ።
|
|
|
የማወቅ ጉጉት! ኦገስት 16 ወደ STEM ፌስቲቫል ይምጡ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ ከቀትር እስከ 3 ፒ.ኤም ድረስ " ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ STEM ፌስቲቫል" ያስተናግዳል።
ቀን፦ ቅዳሜ፣ ኦገስት 16
አድራሻ፦ East County Community Recreation Center, 3310 Gateshead Manor Way in Silver Spring. ይህ ዝግጅት ሳይንስን፣ ቴክኖሎጂን፣ ምህንድስናን፣ እና ሂሳብን የሚቃኙ የተግባቦት ኤግዚቢሽኖችን ያካትታል።
ለተጨማሪ መረጃ እና ለመገኘት ይመዝገቡ።
|
|
|
MCPS ዜናዎችን ይከታተሉ
የሠመር ራይዝ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት፡ ከ 1,000 በላይ ተማሪዎችን እና 230 አጋር ድርጅቶችን ለአምስት ሳምንታት በአውታረ መረብ ግንኙነት አድርገዋል እና የስራ ፈለጎችን አክብረዋል።
የትምህርት ቤት ቁሳቁስ አቅርቦቶች!ከ1,100 በላይ ሰዎች በፓርክላንድ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በተካሄደው አመታዊ "Drive for Spply" ዝግጅት ላይ ተገኝተው የትምህርት ቁሳቁሶችን ወስደዋል።
ወቅታዊ ዘገባዎችን በዚህ በይነመረብ ላይ ይከታተሉ።
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
ከ MCPS የበለጠ መረጃ
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|