አበይት ጉዳዮች

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃዎች
ጁን 26, 2026

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጁን 25 ባካሄደው ስብሰባ ላይ የተማሪዎችን አስደናቂ ስኬት ያከበረ ሲሆን ተጠያቂነትን፣ ግልጽነትን፣ እና ማህበረሰብ ተሳትፎን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ በርካታ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ዋና ዋና ነጥቦቹ $437 ሚሊዮን ዶላር በላይ የትምህርት ስኮላርሽፕ ዕድል ያስገኘለትን የ 2026 ተመራቂዎች እውቅና መስጠት፣ በዲስትሪክቱ ውስጥ ቀጣይ የትምህርት ዕድገት፣ ለተማሪዎች የሠመር የምግብ አቅርቦትን ማስፋት፣ የገንዘብ ቁጥጥርን ለማጠናከር የተደረጉ ማሻሻያዎች እና የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስን የወደፊት ሁኔታ ለመቅረጽ የሚረዱ አዳዲስ የተማሪዎች እና የማህበረሰብ መሪዎችን መሰየም ይገኙበታል።


ስለ ትምህርት ዓመት ማጠቃለያ | ስለ ፋይናንስ ቁጥጥር | ስለ ሥነ ምግባር ፓነል | ስለ ተማሪዎች አመራር | ስለ ሠመር የምግብ አቅርቦት | ስኬትን ማክበርና እውቅና መስጠት


MCPS የዚህን አመት የተማሪዎችን ስኬት እና የወደፊት ዝግጁነት አክብሯል

ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ቶማስ W. ቴይለር MCPS ውስጥ ጠንካራ የትምህርት ውጤት እና የተማሪዎች ስኬት የታየበትን ዓመት በማጉላት ገልጸዋል።

ጉልህ ስኬቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • ከትምሕርት አመት 2026 ተማሪዎች መካከል 12,937 ተመራቂዎች ነበሩ።
  • $437 ሚሊዮን ዶላር በላይ የትምህርት ስኮላርሽፕ ዕድል ተገኝቷል
  • 2 ሚሊዮን በላይ የማህበረሰብ አገልግሎት ሰዓታት ተከናውነዋል
  • በሜሪላንድ አጠቃላይ ግምገማ ፕሮግራም (MCAP) ግምገማዎች ላይ ቀጣይ እድገት ተመዝግቧል
  • የጣምራ ምዝገባ እድሎች ተዘርግተዋል
  • የብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪነት ፕሮግራም ውስጥ የተሳትፎ መጠን በሪከርድ ደረጃ አድጓል

ወደፊት ስንመለከት፣ MCPS በወደፊት ዝግጁነት ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ አማካኝነት በአካዳሚክ ልህቀት፣ በተማሪዎች ሥነ ምግባር፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ላይ አፅእኖት በመስጠት ይቀጥላል።

ስለ 2025–2026 የትምህርት ዓመት ማጠቃለያ የቀረበውን ዘገባ ሙሉ ያንብቡ።


አዲሱ የኦዲት ቻርተር ተጠያቂነትን ያጠናክራል

ቦርዱ የውስጥ ኦዲት ክፍል ቻርተር አጽድቋል፣ ይሄውም MCPS ውስጥ ያሉ የፋይናንስ አጠቃቀምን እና ስራዎችን የመገምገም ኃላፊነት ያለበትን ቡድን በገለልተኛነት የመስራት ሁኔታ ያጠናክራል።

ቻርተሩ የኦዲት ክፍሉን ስልጣን፣ በነፃነትና በገለልተኛነት የመሥራት አቅም እና በቀጥታ ለቦርዱ ሪፖርት የማድረግ ኃላፊነትን ያጎናፅፋል። ይህ ማለት ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ ለሠራተኞች እና ለታክስ ከፋዮች፣ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ የመገልገያ ሪሶርሶች/ሀብት እንዴት እንደሚተዳደር የበለጠ ግልጽነት እንዲኖር፣ ተጠያቂነትን እና የበለጠ ግልጽነት ያለበትን አሰራር ማስፈን ማለት ነው።

የቦርዱን ውይይት ይመልከቱ እና በውስጣዊ የኦዲት ክፍል ቻርተር ላይ ድምጽ ይስጡ።


ቦርዱ አዲስ የሥነ ምግባር ፓነል አባል መርጧል።

ቦርዱ የሥነ ምግባር ደረጃዎችን እና የህዝብን አመኔታን ለመጠበቅ ወሳኝ ሚና የሚጫወተውን የሥነ ምግባር ፓነል ክፍት የሥራ ቦታ በሚመለከት ውይይት አድርጓል። ፓናሉ የፋይናንስ መግለጫዎችን ይገመግማል፣ በሥነ ምግባር ጉዳዮች ላይ ምክር ይሰጣል፣ እና ከቦርዱ የሥነ ምግባር ፖሊሲዎች ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን ይመረምራል።

ከማህበረሰቡ የቀረቡትን ማመልከቻዎች ከገመገመ በኋላ፣ ቦርዱ ብሪያን ጄ. ሶንፊልድ/Brian J. Sonfield ከጁላይ 1, 2026 ጀምሮ ለሦስት ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ሰይሟል።


በኮሙኒኬሽን እና በማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ ውስጥ የተማሪ አባል መሾም

ቦርዱ 2026–2027 የትምህርት አመት የተማሪ ተወካዮችን ለኮሚኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ አባልነት ሰይሟል።

ይህ ኮሚቴ ቦርዱ ከቤተሰቦች እና ከማህበረሰብ አባላት ጋር ያለውን ግንኙነት እና ተሳትፎ ለማሻሻል ምክረሃሳብ ይሰጣል። በሚቀጥለው ዓመት ኮሚቴው በዲስትሪክት አቀፍ የተሳትፎ ጥረቶች እና በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የወሰን ጥናት ላይ አስተያየቶችን እና ምክረሃሳቦችን ያቀርባል።

ተወዳዳሪ የማመልከቻ ሂደትን ከመረመረ በኋላ፣ አሌክሲያ ሮቢንሰን/Alexsia Robinson እና ናታሊ ሜንዶዛ/Natalie Mendoza ከማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ሆነው እንዲያገለግሉ እና እነዚህን አስፈላጊ ውይይቶች በሚመለከት የተማሪዎችን አስተያየት እና አመለካከት እንዲያቀርቡ ተመርጠዋል።

ስለ ኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ የበለጠ ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ።


አርባ ዘጠነኛው ተማሪ የቦርድ አባል ጁላይ 6 የተመረጠበትን ኃላፊነት እንዲያከናውን ይሰየማል

አርባ ዘጠነኛው ተማሪ የቦርድ አባል

የኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነ ልዑል ዳዊት፣ ጁላይ 6 ቀን የትምህርት ቦርድ (SMOB) 49ኛው ተማሪ የትምሕርት ቦርድ አባል በመሆን ይሾማል።

ልዑል በስልጣን ዘመኑ በተማሪዎችና በካውንቲው አመራር መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፣ የተማሪዎች ቅሬታዎች እንዲሰሙ እና እንዲፈቱ ለማረጋገጥ እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ የተማሪዎች ድጋፍ እድሎችን ለማስፋት ያለውን እቅድ ለመተግበር ይሠራል።

በትምሕርት አመት 2026 የሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂ የሆነችውን አኑቫ ማሉን/Anuva Maloo በመተካት የሚሠራ ሲሆን፤ ለተማሪዎችና ለማህበረሰቡ የሚሰጠው አገልግሎት በሚሰየምበት ሥነ ሥርዓት ወቅት እውቅና ይሰጠዋል።

ጁላይ 6 ቀን 15 W. Gude Drive በሚገኘው ቢሮ ሥነ ሥርዓቱ የሚካሄደው ከቀኑ 4:00 p.m. ላይ ነው። የሚደረገው የሹመት ስነ ስርአት ለሕዝብ ክፍት ስለሆነ የተወሰነ መቀመጫ ያለ በመሆኑ MCPS ድረ ገጽ ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል እንዲሁም Comcast Channel 34፣ Verizon FIOS Channel 36 እና RCN Channel 89 ላይ ይተላለፋል።


12,000 በላይ ተማሪዎችን ለመደገፍ በሠመር ወቅት ነፃ የምግብ አቅርቦት ፕሮግራም ይካሄዳል

አርባ ዘጠነኛው ተማሪ የቦርድ አባል

በሺዎች የሚቆጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጆች በዚህ ሠመር MCPS በሠመር ወቅት የምግብ አገልግሎት ፕሮግራም አማካኝነት ነፃ እና ገንቢ የሆኑ አልሚ ምግቦችን ያገኛሉ።

ፕሮግራሙ በአሜሪካ የግብርና መምሪያ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ሲሆን 18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች እና ብቁ ለሆኑ የአካል ጉዳተኞች ያለምንም ክፍያ ምግብ ያቀርባል። MCPS በሠመር ወቅት በመላው ካውንቲ ውስጥ ከ 100 በላይ የምግብ ማደያ ቦታዎች ላይ የተዘጋጁ ምግቦችን ያቀርባል።

ቤተሰቦች "Maryland SUN Bucks" የግሮሰሪ ጥቅም ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ይህም ለአንድ ብቁ ልጅ $120 የግሮሰሪ ጥቅማ ጥቅም የሚሰጥ ሲሆን ከሌሎች የእርዳታ ፕሮግራሞች ጋር አብሮ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

  • ከ 18 ዓመት እድሜ በታች ለሆኑ ህጻናት ነፃ ምግብ
  • በሞንትጎመሪ ካውንቲ ከ 100 በላይ ቦታዎች
  • ጁን 23 ቀን ጀምሮ አገልግሎቱ ይሰጣሉ።
  • "Maryland SUN Bucks" አማካይነት ተጨማሪ ድጋፍም ይኖራል

ስለ ምግብ ቦታዎች እና የብቁነት መረጃ ለማግኘት የሠመር ምግብ ድረ ገጽ ይጎብኙ


ሥነ ሥርዓቶች እና የተሰጡ እውቅናዎች

ማርክ ማን የልህቀት ሽልማት Mark Mann Excellence Award

ማርክ ማን የልህቀት ሽልማት

በየዓመቱ ማርክ ማን ልህቀት እና ሃርመኒ ሽልማት የሚሰጠው ለአካዳሚክ ልህቀት፣ አዎንታዊ የሰዎች ግንኙነት እና የማህበረሰብ ተደራሽነትን ለማጎልበት ቁርጠኛነት ለሚያሳዩ መምህራን ነው። የዚህ ዓመት አሸናፊ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት ብራንዲ ኬ. ኦቨርተን መሆናቸውን የቦርድ አባል ካርላ ሲልቬስትሬ ገልፀዋል። ይህ ሽልማት የሚወክለው ፍትሃዊነትን እና የተማሪዎችን ስኬት ማሳደግ፣ የተማሪዎችን ተሰጥኦ ማጎልበት፣ እና ትምህርት ቤቱ MLK ጁንየር ለተማሪዎች ያላቸውን ግንዛቤ በማስፋት ረገድ ለዚህ ትልቅ ሽልማት በቅተዋል። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ። ቦርዱ ወ/ሮ ኦቨርተን "Mark Mann Excellence and Harmony Award." ሽልማት በማግኘታቸው ላሳዩት አስደናቂ አመራር እውቅና እና ክብር ሰጥቷል።

ትምህርት ቤቶቻችንን እና ተማሪዎቻችንን ማክበር የትምሕርት አመት 2026 ካፒ እጩዎች

ትምህርት ቤቶቻችንን እና ተማሪዎቻችንን ማክበር የትምሕርት አመት 2026 ካፒ እጩዎች

ቲያትር ተማሪዎቻችን የፈጠራ ችሎታቸውን፣ የችግር አፈታት ክህሎቶቻቸውን፣ እና የትብብር ክህሎቶቻቸውን ለማዳበር እጅግ በጣም ጥሩ ዘዴ/ስልት ነው። 2026 የትምሕርት አመት "Cappies of the National Capital Area Gala" ሽልማት በመድረክ ላይም ሆነ ከመድረኩ ውጪ ልዩ ችሎታቸውን እና ተሰጥኦአቸውን የሚያሳዩ ተማሪዎችን እውቅና ይሰጣል። በዚህ ዓመት የቦርድ አባል ላውራ ስቱዋርት ለሽልማቶቹ ከተመረጡት አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አራቱን - የክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት - እውቅና ሰጥተዋቸዋል። ስተዋርት የሽልማቱን ሁለት አሸናፊዎች እውቅና ሰጥተዋል፤ እነሱም የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የድምፃዊነት ሚና ካፒስ ሽልማት በማሸነፋቸው የዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የራያን ሳውየር ሮቢንስ እና የኩዊንስ ኦርቻርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካርፒስ ሽልማት በሙዚቃ የኮሚክ ተዋናይነት ሽልማት በማሸነፋቸው የቲሞ ሲልበርማን እውቅና ሰጥተዋል።

በኩራት የሚዘከር ወር

የመምህራን አድናቆት ሳምንት

ጁን ወር በኩራት የሚዘከር ወር ሲሆን፣ ሰፊ እና የተለያዩ LGBTQIA+ ማህበረሰብ - ስኬቶቹን እና ታሪክ - በአሜሪካም ሆነ በዓለም ዙሪያ ይከበራል። በዚህ ሳምንት በቦርድ ስብሰባ ወቅት፣ የቦርዱ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን ለሞኮ ፕራይድ ሴንተር ላደረጉት አስደናቂ የማቀንቀን፣ የተደራሽነት፣ የትምህርት እና የታዋቂነት ስራ እውቅና ሰጥተዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው ፊሊፕ አሌክሳንደር ዳውኒ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ማኬዳ ሪቻርድሰን የሞንትጎመሪ ካውንቲ LGBTQIA+ ማህበረሰብን በማክበር ረገድ ላደረጉት ጥረት ቦርዱ አክብሮት ሰጥቷቸዋል።


ቀጣይ ስብሰባዎች

ሰኞ፣ ጁላይ 6ተማሪ የቦርድ አባል/SMOB የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት ይከናወናል (4፡00 p.m)
ሐሙስ፣ ጁላይ 16፣ የቦርድ የሥራ ስብሰባ (4፡00 p.m.)
ሐሙስ፣ ኦገስት 20፣ የቦርድ የሥራ ስብሰባ (4፡00 p.m.)


ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

በህዝባዊ የውይይት መድረኮች ላይ አስተያየት ለመስጠት ይሳተፉ። 

FacebookInstagramBluesky፣ እና X ላይ ይከታተሉን

ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org