የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትንተና እና የድንበር ጥናት ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የተለያዩ የመረጃ ክፍለ ጊዜዎችን ያስተናግዳል።
ይህ ለምን አስፈላጊ ሆነ?
እነዚህ ሁለት ጥረቶች—የአካዳሚክ መርሃ ግብር ትንተና እና የድንበር ጥናቶች - ለእያንዳንዱ ተማሪ ለማደግ የሚያስፈልጋቸውን ግብአቶች እና እድሎችን የማግኘት ተደራሽነት መኖሩን ማረጋገጥ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰፊ የቁርጠኝነት አካል ናቸው። በ 2025–2030 የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስትራተጂክ እቅዳችን መሠረት ለስራዎች፣ ለፋሲሊቲዎች እና የሰው ሃይል ማሟላት ላይ የበጀት ድልድል ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት፣ እና እለት ተእለት የትምህርት ቤቶችን ሥራ እና ህይወት በሚቀርጹ ፖሊሲዎች፣ ደንቦች፣ እና መመሪያዎች ላይ በመመርኮዝ MCPS ተማሪዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ድጋፍ የሚያገኙበት፣ እና ተግዳሮቶችን በመቋቋም ለወደፊታቸው እንዲዘጋጁ የማድረግ ስራውን ይቀጥላል። የጠንካራ ፕሮግራሞችን ተደራሽነት ማስፋት፣ የትምህርት ቤቶችን የተማሪዎች ምዝገባ ማመጣጠን ወይም ቀጥታ ትምህርት ቤት ላይ ያተኮሩ ድጋፎችን መስጠት በሚመለከቱ ጉዳዮች MCPS — እና ተማሪዎቻችንን — "MCPS የወደፊት ዝግጁነት" ለማጠናከር የተቻለንን ስራ በመስራት ላይ እናተኩራለን።
እኛ እያደረግን ያለነው፡ MCPS ብዙ ተማሪዎች፣ በካውንቲው ለመኖሪያ ቤት ቅርብ በሆኑ የተለያዩ አካባቢዎች ጠንካራ ፕሮግራሞች ኖረው እንዲሳተፉ ለማድረግ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን ሪጅናል ሞዴል ንድፍ እያዘጋጀን ነው። ግባችን የላቀ ትምህርት እና ፍትሃዊነትን ማስፈን ነው። በሪጅን ደረጃ በማስፋፋት ፈጣን ፕሮግራሞችን እና ጥንካራ የትምህርት ፕሮግራሞችን እያበለፀግን ውስንነትን እና በርቀት ምክንያት ያሉትን መሰናክሎች መቀነስ እንችላለን። ዲሴምበር 2025 የትምህርት ቦርድ የመጨረሻ እርምጃ እንደሚወስድ ይጠበቃል።
አስፈላጊነቱ ለምድንድነው፡ MCPS ሁሉም ተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የትምህርት እድሎች እንዲያገኙ ለማስቻል ዲስትሪክት አቀፍ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትንተና እያካሄድን ነው። ግቡ ፕሮግራሞችን ከተማሪዎች ፍላጎቶች፣ ከማህበረሰብ ፍላጎቶች፣ ከኢንዱስትሪ ፍላጎቶች፣ እና ሪሶርሶችን ከውጤታማ አጠቃቀም ጋር ለማመጣጠን/ለማሳለጥ ነው። ይበልጥ ያንብቡ
እንዴት መሳተፍ እንደሚቻል፡ ለመሳተፍ የተለያዩ መንገዶች አሉ። ለእርስዎ ፍላጎት እና የጊዜ ሰሌዳ የሚስማማውን የመረጃ ክፍለ ጊዜ መርጠው ይቀላቀሉ።
NEC ቤተሰቦች 6ኛ እና 7ኛ ክፍል፡ ሴፕቴምበር 29 ከቀኑ 1:30-2:30 p.m. እና 6-7 p.m. (ቨርችዋል)
DCC ቤተሰቦች 6ኛ እና 7ኛ ክፍል፡ ሴፕቴምበር 30 ከቀኑ 12-1 p.m. እና 6-7 p.m. (ቨርቹዋል)
6ኛ እና 7ኛ ክፍል የሚገኙ ቤተሰቦች በሙሉ፡ ኦክቶበር 22 ከቀኑ 12-1 p.m. እና 6-7 p.m. (ቨርቹዋል)
6ኛ እና 7ኛ ክፍል ያሉ ሁሉም ቤተሰቦች፡ ኦክቶበር 27 ከቀኑ 12-1 p.m. እና 6-7 p.m. (ቨርቹዋል)
ለተጨማሪ መረጃ ይህንን በይነመረብ (ድረ ገጽ) ይመልከቱ፦ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትንተና ድረ ገጽ/Academic Programs Analysis webpage
እኛ እያደረግን ያለነው፡እርስዎ የነገሩንን አድምጠናል። በኦክቶበር ወር የድንበር ጥናት አማራጭ ስብሰባ ላይ ለመገኘት እቅድ ይያዙ። ስለ ቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን መከፈት፣ ስለ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት፣ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ማስፋፋት በሚመለከት ለህብረተሰብ መረጃ የማጋራት ስብሰባዎች ላይ ስለ ትምህርት አመት 2027-2028 የተጣሩ የድንበር አማራጮችን በተመለከተ ለማህበረሰቡ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል። ተሰብሳቢዎች ትርጉም ያለው አስተያየት መስጠት እንዲቀጥሉ MCPS ስለ እያንዳንዱ የድንበር ጥናት የተከናወኑ የዳሰሳ ጥናቶችን ያጋራል።
አስፈላጊነቱ ምንድነው፡ የውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገና መከፈት፣ አዲሱ የክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መስፋፋት ጥናቱ ባካተታቸው አካባቢዎች ያሉ በርካታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን መጨናነቅ ለማቃለል ይረዳል።
እንዴት መሳተፍ እንደሚቻል፡ ለመሳተፍ ብዙ መንገዶች አሉ። ለእርስዎ ፍላጎት እና መርሐግብር የሚስማማውን የመረጃ ክፍለ ጊዜ መርጠው ይቀላቀሉ።
ለበለጠ መረጃ፣ MCPS የድንበር ጥናት ድረ ገጽ ይጎብኙ።
በዚህ አድራሻ ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org