ጉዳዩ፡ በትምህርት ቤት የጊዜ ሰሌዳ ላይ የተደረገ አስፈላጊ ማሻሻያ/ ለውጥ

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ስለ 2025–2026 የትምህርት ዓመት ቀሪ ጊዜ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ዓመት የጊዜ ሰሌዳ ላይ የተደረገውን አስፈላጊ ማሻሻያ እንደገና ለማካፈል እየጻፍንላችሁ ሲሆን ከስፕሪንግ የእረፍት ጊዜ በፊት ስለ ትምህርት ጊዜ ሰሌዳችን/ካለንደር እንደገና ሌላ መልዕክት ሊኖር ይችላል።

ከሜሪላንድ የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) ጋር በመመካከር፣ MCPS የትምህርት ጊዜውን መጠበቅ በሚያስችል ሁኔታ የጊዜ ሰሌዳውን የትምህርት ቀናት ለማሟላት በቅን መንፈስ እየሰራ ነው፤ ስለሆነም ወደ ትምህርት ዓመቱ መጨረሻ ላይ ተጨማሪ ቀናትን እንዳይጨምሩ ከመንግስት ልዩ ፈቃድ (waiver) እንዲሰጥ እየጠየቅን ነው።

ይህንን በሚመለከት የምናስተላልፍላችሁ ዜና

አሁን የምንተገብራቸው የጊዜ ሰሌዳ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፦

  • ኤፕሪል 15፣ ከዚህ በፊት የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ መጨረሻ ላይ ለአስተማሪዎች የትምህርት ውጤት መስጫ እና ለእቅድ ዝግጅት ስራ የተመደበ ለተማሪዎች ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ነበር፣ አሁን ግን ለተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ይሆናል

  • የማርክ መስጫ ክፍለ ጊዜው እንደተወሰነው ኤፕሪል 14 ይያበቃል፣ ነገር ግን የትምህርት ውጤት ሪፖርት እስከ ኤፕሪል 20 ድረስ ይዘገያል።

  • ፌብሩወሪ 19 ቀን በተደረገው የትምህርት ቦርድ ውሳኔ መሠረት፣ ማርች 20 ለተማሪዎች ትምህርት የማይሰጥበት ቀን ይሆናል።

በትምህርት ዓመቱ የመጨረሻ ቀን ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ
እንደምታውቁት፣ የዚህ ክረምት ከባድ የአየር ሁኔታ ለብዙ ቀናት ትምህርት ቤቶችን እንድንዘጋ አስገድዶናል። በአሁኑ የሜሪላንድ ሕጎች መሠረት፣ቀደም ሲል በካሌንደሩ ውስጥ በተወሰኑት የትምህርት ማካካሻ ቀናት ወይም ካስፈለገ የትምህርት ዓመቱን በማራዘም ትምህርት የተቋረጠባቸው ቀናት እንዲሟሉ ተደንግጓል። በዚህ ምክንያት ነው፣ በቅርቡ እንደተገለጸው የትምህርት ካሌንደራችንን በማሻሻል የትምህርት ዓመቱን የመጨረሻ ቀን ወደ ጁን 26 እንዲራዘም ትምህርት የሚሰጥበት ቀናት የተጨመሩት።

የዚህ ማስተካከያ ግቡ የትምህርት ማሟያ ጊዜ ማራዘሙን በተያዘው የትምህርት ዓመቱ ቀናት ውስጥ እንዲሆን እና ለቤተሰቦች እና ለሰራተኞች ካሌንደሩ ወደ ጁን እንዳይረዝም የመንግስትን ፍቃድ ለመጠየቅ ነው።

በትምህርት ካሌንደር ላይ የሚደረግ ማንኛውም ለውጥ እና በተደጋጋሚ የሚደረጉ ለውጦች የቤተሰቦችን ጊዜ እና የሰራተኞች ዕቅድ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፣ እና ቀጣይ ማሻሻያ ደግሞ ተፈላጊ አይሆንም። የሆነ ሆኖ፣ የትምህርት ዓመቱን በታለመው ጊዜ የማጠናቀቅ እድል ሲኖር በትምህርት ማህበረሰቦቻችን ውስጥ ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ እና ለሰራተኞች በሚገባ ድጋፍ እንደሚሰጥ እናምናለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools


በዚህ አድራሻ ኢሜል ላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org