አሁን ክፍት ነው፦

ስለ ትምህርት ቤት ያለዎትን ተሞክሮ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን

MCPS ሰራተኞችን፣ ቤተሰቦችን፣ እና የማህበረሰብ አባላትን ከኤፕሪል 20 እስከ ሜይ 10 ባለው ዓመታዊ የዳሰሳ ጥናት አማካኝነት ልምዶቻቸውን እና አስተያየታቸውን እንዲያካፍሉ ይጋብዛል።

ቀደም ሲል ይሄ "የትምህርት ቤት ድባብ እና ባህል ጥናት" ተብሎ ይጠራ ነበር፣ ነገር ግን ምንም ስለ አየር ሁኔታ የሚመለከት አይደለም። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ስላለዎት ልምድ እና እንዴት ማሻሻል እንደምንችል ግብረመልስ ለማግኘት ነው።

የእናንተን አስተያየት ስናገኝ—ትምህርት ቤቶቻችንን የተሻለ ለማድረግ ይረዳናል። 10 ደቂቃ በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ፣ ከትምህርት እና ከግንኙነት ጀምሮ እስከ አጠቃላይ የትምህርት ቤት ተሞክሮ በጥሩ ሁኔታ እየሰራ ያለውን እና የትኞቹን ማሻሻል እንደሚኖርብን ሀሳብዎን ያጋሩናል። እንዲሁም ትምህርት ቤቶቻችን በሚገባ የሚደገፉ መሆናቸውን እና ተማሪዎች ለመማር ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳናል። 

በዚህ ዓመት አዲስ ነገር፡ የተማሪ መታወቂያ ቁጥር መግለጽ አያስፈልግም!

ተሳትፎን ቀላል ለማድረግ፣ በዚህኛው የራስዎን ሀሳብ ለይተው ማወቅ ይችላሉ—የተማሪ መታወቂያ ቁጥር ማስገባት አያስፈልግም። ሁሉም ግብረመልሶች በሚስጥራዊነት ይጠበቃሉ።

የተማሪዎችን እና የቤተሰቦችን ተሞክሮዎች በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት እና ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት እቅድ እና ውሳኔ አሰጣጥን መመሪያ እንዲሆነን የሚሰጡት ግብረመልሶች በትምህርት ቤት እና በዲስትሪክት መሪዎች በአጠቃላይ ይገመገማሉ።


በዚህ አድራሻ ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org