አበይት ጉዳዮች
ዲሰምበር 18, 2025
|
|
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የወደፊት ዝግጁነት ራዕይ በመጀመሪያ ሩብ አመት ተስፋ ሰጪ በሆኑ ድሎች ተጠናክሮ ቀጥሏል
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ MCPS የወደፊት ዝግጁነት፡ የትምህርት አመት 2025–2030 የስትራቴጂክ ዕቅድ እና የትምህርት ዓመት 2025–2026 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እድገት ላይ በተገለጸው የዲስትሪክቱን መረጃ ለትምህርት ቦርድ ዲሰምበር 11 አቅርቧል። ይህ ዓመት እያንዳንዱ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ ተመራቂዎች ለማደግ ዝግጁ እንዲሆኑ የጋራ ቁርጠኝነትን የሚገልጽ የስትራቴጂክ ዕቅዱ የመጀመሪያ ሙሉ የትግበራ ውጤት ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
እንዲሁም የትምህርት አመት 2024–2025 MCPS አመታዊ ሪፖርት ቀርቧል
MCPS የትምህርት አመት 2024–2025 ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ይህም ወሳኝ የሆነ የሽግግር ዓመት መሆኑን ይገልጻል — MCPS የወደፊት ዝግጁነት ስትራቴጂክ ዕቅድ ማዘጋጀትን ያካትታል፣ከአሁን በኋላ የእድገት አቅጣጫችንን የሚመራ እና የመከታተል ግቦችን አስቀምጧል።
|
|
|
ሱፐርኢንቴንደንት $3.775 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት አቅርበዋል።
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ W. ቴይለር/Thomas W. Taylor ዲሰምበር 17 ቀን የበጀት ዓመት (FY) 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት አቅርበዋል፣ ይህም ለሰዎች ቅድሚያ የሚሰጡ ኢንቨስትመንቶች፣ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ተመዝጋቢ ቁጥር መቀነስን በሚመለከት፣ ትምህርት ቤቶችን የሚያጠናክሩ ግልጽ የሰራተኞች መመዘኛዎች እና በሂሳብ እና በማንበብ ላይ የሚያተኩሩ የማስተማሪያ ድጋፎችን ያካትታል።
ዶ/ር ቴይለር ባቀረቡት የበጀት እቅድ ከበጀት ዓመት 2026 ጋር ሲነጻጸር $179.7 ሚሊዮን ዶላር (5%) ጭማሪ ያለው $3.775 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት አቅርበዋል። ጭማሪው፣ ከቀዳሚው ዓመት በእጅጉ ያነሰ ሲሆን፣ የተማሪዎችን ትምህርት ቅድሚያ በመስጠት፣ መዋቅራዊ የበጀት ጫናዎችን በመፍታት እና ሪሶርሶችን ከውጤት ጋር በማጣጣም የአሁኑን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያገናዘበ መሆኑን ያንፀባርቃል። በጀቱ የማዕከላዊ አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ $11.5 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ እና አነስተኛ ኮንትራቶችን እና ዜሮ-ተኮር የጀት አጠቃቀምን ጨምሮ፣ ከሰራተኛ ማህበራት ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን ማክበር እና ለት/ቤቶች ቀጥታ ድጋፍ በመስጠት የክፍል ተማሪዎች ቁጥርን ማመጣጠን ጭምር ያካትታል። ይበልጥ ያንብቡ
የበጀት ማቴሪያሎች
|
|
|
አራት ወራት፣ በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት — ደህንነትን በሚመለከት MCPS ዳግም የማጣራት ተግባሩን አጠናቋል።
ለአራት ወራት ያህል ጠንክሮ ከሰራ በኋላ፣ MCPS የሁሉም ትምህርት ቤት ሰራተኞች የበፊት ታሪካቸውን/ዳራ በማጣራት፣ የጣት አሻራ፣ እና አዲስ ባጅ የመስጠት ሂደት አጠናቋል። ይከታተሉ፡ በትምህርት ቤት ለማይሰሩ ሰራተኞች የበፊት ታሪካቸውን/ዳራ የማጣራት፣ የጣት አሻራ መውሰድ፣ እና አዲስ ባጅ የመስጠት ሂደት በቅርቡ ይጀመራል። ይበልጥ ያንብቡ።
በአጠቃላይ በትምህርት ቤት የሚገኙ ሰራተኞች የበፊት ታሪካቸውን/ዳራ እንደገና የማጣራት ተግባር ተጠናቋል። |
8,012 |
በአጠቃላይ ከትምህርት ቤት ውጭ የሚሠሩ ሰራተኞች የበፊት ታሪካቸውን/ዳራ እንደገና የማጣራት ተግባር ተከናውኗል |
1,101 |
|
|
|
ልብን የሚያሞቅ የተማሪዎች ተሰጥኦ፣ የፈጠራ ችሎታ፣ እና ተስፋ ሰጪ ብቃት
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከኖርዝዌስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከሮቤርቶ ክሌሜንቴ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተውጣጡ ተማሪዎች MCPS ውስጥ የወደፊት ዝግጁነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያበስር፣በተማሪዎች የሚመራ "Unleashing Potential" የተሰኘ ኦሪጅናል የሙዚቃ ቪዲዮ በኩራት አቅርበዋል። ይህ ከፍተኛ የቪድኦ ፕሮዳክሽን MCPS ውስጥ ስለ አዳዲስ ነገሮች ፈጠራ፣ ትብብር፣ እና የፈጠራ እድገትን አጉልቶ ያሳያል። ከፅንሰ-ሀሳብ እስከ አፈፃፀም፣ ይህ ፕሮጀክት የተማሪዎቻችንን አስደናቂ ተሰጥኦ እና የሚደግፏቸውን ቁርጠኛ አስተማሪዎች ጥረት ያሳያል።
ቪዲዮውን ይመልከቱ.
|
|
|
ጃኑዋሪ 5 ለቦርዱ የህዝብ አገልግሎት ሽልማቶች እጩዎችን ማቅረብ ይጀመራል።
የትምህርት ቦርድ ሰኞ፣ ጃኑዋሪ 5, 2026 ለሕዝብ ትምህርት የላቀ አገልግሎት ለሚሰጡ የትምህርት አመት 2026 ሽልማቶች እጩዎችን መቀበል ይጀምራል።
ዘርፎቹ የቢዝነስ አጋር፣ የማህበረሰብ አጋር፣ የትምህርት ቤት አገልግሎት በጎ ፈቃደኛ እና የተማሪ አገልግሎት ሽልማቶችን ያካትታሉ። የማህበረሰብ አባላት ብቁ የሆኑ ግለሰቦችን፣ ድርጅቶችን፣ እና ተማሪዎችን ማሰብ እንዲጀምሩ እና ሂደቱ ሲጀመር እጩዎችን ለማቅረብ ዝግጁ እንዲሆኑ ይበረታታሉ።
ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
የሰራተኞች ሽልማቶችን ለማግኘት የጊዜ ገደቦች ተዘርዝረዋል፤ እጩዎችን ይጠቁሙ!
ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሽልማቶች እጩዎችን ለመጠቆም የተቀመጡት የጊዜ ገደቦች ሊጠናቀቁ የተቃረበ ስለሆነ — የጥቆማ ቅጾችን ማቅረብዎን ያረጋግጡ! ምርጥ አስተዳዳሪዎችን፣ ምርጥ ርእሰ መምህራንን፣ እና ድንቅ አስተማሪዎችን ለማክበር የጥቆማ ቅጾችን ሞልተው ያቅርቡ። ስለ ሁሉም ሽልማቶች እዚህ ያንብቡ።
|
|
|
አሁን ያውቃሉ፡ የሥራ ማስኬጃ በጀት — እንዴት ግብዓት ማቅረብ እንደሚችሉ
ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት እቅድ ለትምህርት ቦርድ አቅርበዋል፣እናም በሂደቱ ውስጥ የእርስዎን ድምጽ እንፈልጋለን። ቦርዱ እና የካውንቲው ምክር ቤት የመጨረሻውን የማጽደቅ ውሳኔ ከመስጠታቸው በፊት እያንዳንዳቸው የሥራ ክፍለ ጊዜዎችን እና የሕዝብ አስተያየት መቀበያ ውይይትችን ያካሂዳሉ። የእርስዎ ግብዓት እና ለትምህርት ሥራችን ተሟጋችነት የዚህ ሂደት ወሳኝ አካል ናቸው።
Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
|
|
|
ሥራ እየፈለጉ ነው? የአውቶቡስ አሽከርካሪዎችን እንቀጥራለን!
MCPS ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 22 (ጃንዋሪ 29 የበረዶ ቀን) ከጠዋቱ 10:30 a.m. እስከ 12:30 p.m. ለአውቶቡስ አሽከርካሪዎች የሥራ ትርኢት ያዘጋጃል። ትርኢቱ የሚካሄደው በዚህ አድራሻ ነው፦ Division of Transportation Services’ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ይበልጥ ያንብቡ።
የስራ ትርኢት፣ ጃኑዋሪ 22, 2026
|
|
|
የክረምት ጃኬት/ ኮት እርዳታ መሰብሰብ በመካሄድ ላይ ነው - መጠናቸው ትላልቅ ጃኬቶች ያስፈልጋሉ።
ዓለም አቀፍ የተማሪዎች ምዝገባና መቀበያ ቢሮ (በተለይም "McKinney-Vento Unit" ቤት አልባ ለሆኑ ወይም ቋሚ የመኖሪያ ቤት ለሌላቸው ተማሪዎች የሚረዳ) ለተቸገሩ ተማሪዎች አዲስ የጃኬት/ኮት ልገሳ እየጠየቀ ነው። (መጠናቸው እስከ 5X የሚደርስ) መካከለኛና ትላልቅ መጠን ያላቸው የወንዶችና የሴቶች ጃኬት/ኮት ልገሳ በጣም ያስፈልጋል። የሚያስፈልጉትን እቃዎች በአማዞን ዝርዝር ላይ ማግኘት ይችላሉ።
እቃዎቹን ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 9 a.m.–4 p.m., ድረስ በዚህ አድራሻ፦ Rocking Horse Road Center, 4910 Macon Road, Room 149 in Rockville ሮኪንግ ሆርስ ሮድ ሴንተር ማስረከብ ወይም በኦንላይን ማዘዝ እና በቀጥታ ወደ ሮኪንግ ሆርስ ሮድ ሴንተር ለ Heidi LeMond እንዲደርስ ማዘዝ ይችላሉ።
|
|
|
ለሁሉም ሲንየር ተማሪዎች፡ የትምህርት ፋውንዴሽን ስኮላርሺፖች አሉት
MCPS የትምህርት ፋውንዴሽን (MCPSEF) የሙያ እና የትምህርት ግቦችን ለመከታተል ለሚጓጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና እነዚያን ግቦች ለማሳካት የእድል ክፍተቶች ላጋጠሟቸው ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት ዕድሎች እና ሽልማቶች ክፍት ናቸው።
ዛሬውኑ ያመልክቱ በአንድ ማመልከቻ ለማቅረብ፣ ከአሁን ጀምሮ እስከ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 20, 2026 ድረስ ክፍት ነው። የስኮላርሺፕ ሽልማቶቹ $250 እስከ $20,000 ይደርሳሉ። ተጨማሪ መረጃ
ጥያቄ ካለዎት፣ኢሜይል ይላኩ ወይም 240-740-3216 ይደውሉ።
|
|
|
ማሳሰቢያ፦ የጸደቁትን የትምህርት አመት 2026-2027 የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያዎች ይመልከቱ
የትምህርት ቦርድ የትምህርት አመት 2026–2027 መደበኛ እና የኢኖቬቲቭ ት/ቤት የቀን መቁጠሪያዎችን ዲሰምበር 11 አጽድቋል። እዚህ ማየት ይችላሉ።
|
|
|
ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
-
"HBCU Fair" ዝግጅት ምዝገባ በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል አርብ፣ ፌብሩዋሪ 13, 2026ከቀኑ 6-8:30 p.m. አድራሻ፦ The Universities at Shady Grove, 9630 Gudelsky Drive in Rockville.
-
በግልጽ ይናገሩ፤ ሕይወት ያድኑ፦ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የኦፒዮይድ/ፌንታኒል አላግባብ መጠቀምን እና ከመጠን በላይ የመውሰድን አደጋዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ኦሪጅናል ቪዲዮ በመፍጠር ሕይወት አድን ትምህርት ሰጪ የሆነ ማስገንዘቢያ ያቅርቡ። የመጨረሻው ቀነገደብ፦ እሁድ፣ ጃኑዋሪ 4, 2026ነው።
-
ሲ-ስፓን ተማሪካም ውድድር "C-SPAN StudentCam Competition"፡ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ከውድድሩ ጭብጥ ጋር በተያያዘ "ከነፃነት መግለጫ ጋር በማነጻፀር የአሜሪካን ታሪክ ማሰስ"/“Exploring the American Story through the Declaration of Independence.” በሚል ርዕስ ላይ የቪዲዮ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ከፍተኛው ሽልማት $5,000 ነው። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 20, 2026 ነው።
-
ስለ ጥቁሮች ታሪክ የሚቀርብ ውድድር፡ ይህ የድርሰት ጽሑፍ ውድድር 9ኛ–12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ክፍት ነው። ሃያ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች የሽልማት ገንዘብ ለማሸነፍ ድርሰቶቻቸውን በቀጥታ ታዳሚዎች ፊት እንዲያነቡ ይጋበዛሉ። የመጨረሻ ቀነገደብ፡ እሑድ ጃንዋሪ 25, 2026ነው።
-
አክብሮትን ይምረጡ የተሰኘ የቪድኦ ውድድር/"Choose Respect Video Contest" ለመለስተኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ይህ ውድድር በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች የፍቅር ጓደኝነት ጥቃትን በተመለከተ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ኦርጅናል ቪዲዮ ፈጥረው/ቀርጸው እንዲያቀርቡ የተዘጋጀ ውድድር ነው። ቪዲዎችን የሚያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 15, 2026 ነው።
-
የጌትስበርግ የመጽሐፍ ፌስቲቫል የግጥም ውድድር፦ የዘንድሮው ጭብጥ "ሰብአዊነት ምንድን ነው?" በተሰኘ ርዕስ የሚቀርብ ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆን አለባቸው። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 20, 2026ነው።
-
የቀጣዩ ትውልድ የአመራር ቀን "Next Generation Leadership Day" ይህ ዝግጅት 4ኛ እና 5ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የዎርክሾፕ ቀን ነው። ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11, 2026 በሚካሄደው ዝግጅት ላይ ወርክሾፖችን ለመፍጠር ለማዘጋጀት እና አቅራቢ ለመሆን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን እንፈልጋለን። እስከ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 13, 2026 ድረስ ወርክሾፕ ለመፍጠር/ለማዘጋጀት ያመልክቱ። እስከ ሰኞ፣ ማርች 9, 2026 ድረስ ዎርክሾፕ ለማቅረብ ያመልክቱ።
-
አስተማማኝ የቪዲዮ ውድድር "Keeping It Safe Video Contest"፡ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከ 21 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ተማሪዎች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና አስከፊ ጉዳቶች 30 ሰከንድ ቪዲዮ ፈጥረው/አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ ማክሰኞ፣ ማርች 31, 2026ነው።
-
"Sustainability Poster Contest"፡ ሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች በዚህ አመታዊ ውድድር ላይ የኢነርጂ ቁጠባ፣ የቆሻሻ ቅነሳ፣ እና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ግንዛቤን ለማሳደግ መሳተፍ ይችላሉ። አዲሱን የዲጂታል አርት ይመልከቱ! የግዜ ገደብ - አርብ ኤፕሪል 3 2026.
|
|
|
ሠመር ራይዝ "Summer RISE 2025" አስተናጋጅ ለመሆን ምዝገባ አሁን ክፍት ነው።
የወደፊት ተነሳሽነት! ተማሪዎችን በሙያ ጉዞአቸው ይምሯቸው! MCPS ከጁን 22 እስከ ጁላይ 24, 2026 ለሚካሄደው 2026 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም አስተናጋጆችን ይፈልጋል። የስራ ቦታዎን ለታዳጊ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጁንየር እና ሲንየር ተማሪዎች 50 ሰዓታት ተግባራዊ ትምህርት እንዲያገኙ—በቨርቹዋል፣ በአካል፣ ወይም በጣምራ ተሞክሮ ልምድ እንዲቀስሙ ክፍት ያደርጉ።
የመረጃ ስብሰባ ላይ በመሣተፍ የበለጠ ይወቁ፣ www.MCPS-SummerRISE.org ድረ ገጽ ይጎብኙ ወይም በስልክ ቁጥር 240-740-5599 Mr. Davida Gurstelle ያነጋግሩ።
|
|
|
በዚህ ሠመር ወቅት ለልጆችዎ የሚያደርጉትን ነገር ይፈልጋሉ?
የሞንትጎመሪ ካውንቲ መዝናኛ ማዕከል በጃንዋሪ ወር ሁለት የሠመር ካምፕ ትርኢቶችን ያስተናግዳል። እነዚህ ዝግጅቶች ቤተሰቦች የካውንቲውን የካምፕ ፕሮግራሞች እንዲጎበኙ እድል ይሰጣቸዋል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡-
-
ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 10፣ ከቀኑ 1-4 p.m., ጀርመንታወን የማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል/Germantown Community Recreation Center18905 Kingsview Road, Germantown
-
እሁድ፣ ጃንዋሪ 11፣ ከቀኑ 1-4 p.m., Marilyn J. Praisner Community Recreation Center 14906 Old Columbia Pike, Burtonsville
ከዓርብ፣ ዲሰምበር 19 ጀምሮ ActiveMONTGOMERY.org ላይ የካምፕ ዝርዝሮችን ማየት ይችላሉ። ዲጂታል የሠመር ካምፖች መመሪያ "Digital Summer Camps GUIDE" አርብ፣ ጃንዋሪ 2 ይወጣል።
|
|
|
ከዜና አምዳችን
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
|
|