ኦገስት 28, 2025
ማውጫ: እንኳን ደህና መጣችሁ | የተሻሻለ የደህንነት ፕሮቶኮል | Refrigerator Curriculum | የሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች ማሻሻያ | ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ምሽቶች | የበልግ (ፎል) ስፖርት ደህንነት እቅድ | በክብር መመገብ | የትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝር እና MySchoolBucks | ማሳሰቢያዎች | የዜና ገጽ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወደ 160,000 ለሚጠጉ ተማሪዎች ወደ 2025–2026 የትምህርት አመት እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ኦገስት 26 ቀን በሩን ከፍቷል። ከአንድ ቀን በፊት፣ MCPS በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተማሪ ሽግግር ቀን አድርጓል። የመጀመሪያው ቀንፎቶግራፎችን እና ቪዲዮ ይመልከቱ።
ከትምህርት ቤት ካላንደር (የቀን መቁጠሪያ) የበዓል ቀናት፣ ትምህርት የማይሰጥባቸው ቀናት፣ እና ሌሎችንም ማሻሻያዎች ይመልከቱ።
2025-2026 መደበኛ የትምህርት ዓመት ቀን መቁጠሪያ (ካለንደር)English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ
2025-2026 የኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤት ካላንደር (አርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ) English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ
አሁን ተማሪዎችን፣ ቤተሰቦችን፣ እና ሰራተኞችን ሊጎዱ ለሚችሉ የአደጋ ክስተት እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በብቃት ምላሽ ለመስጠት MCPS የተሻሻለ የደህንነት ፕሮቶኮል እየተጠቀመ ነው። ማወቅ ያለብዎት ነገር እነሆ፦
መደበኛ ምላሽ የመስጠት ፕሮቶኮል (SRP) አምስት መመሪያዎችን ያካትታል፡ ባሉበት መቆየት፣ ጽናት፣ መቆለፍ፣ ለቆ መውጣት፣ እና ከለላ መያዝ። ይህ ቪዲዮ ስለ (SRP) የበለጠ ያብራራል።
ምን አዲስ ነገር እንዳለ የበለጠ ይወቁ።
MCPS የሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም — ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ጊዜ ምን እንደሚማሩ የሚያመለክት ባለ አንድ ገጽ መግለጫ አስተዋውቋል። በማቀዝቀዣ ላይ ለመለጠፍ እንዲያመች የተነደፈው፣ይህ መመሪያ ቤተሰቦች ቁልፍ ጭብጦችን እና ጽሑፎችን እንዲያውቁ፣ የተማሪዎቻቸውን ትምህርት መከታተል እንዲችሉ እና፣ ካስፈለገም ጽሑፉ ከሃይማኖታዊ አመለካከቶች ጋር የሚፃረሩ ከሆነ አማራጭ የትምህርት ስራዎችን እንዲጠይቁ ይረዷቸዋል። 2025-2026 የትምህርት አመት የመጀመሪያ ሩብ ክፍለጊዜ ሰነዶችን ይመልከቱ።
MCPS በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፕሮግራሞች ላይ ለውጦችን ማድረግ ሲቀጥል፣ቤተሰቦች እና ተማሪዎች ጥያቄዎች ሊኖራቸው እንደሚችል ዲስትሪክቱ ይገነዘባል። MCPS በካውንቲው ውስጥ ፕሮግራሚንግ የበለጠ የተስፋፋ፣ ተደራሽነት ያለው፣ እና ፍትሃዊ ለማድረግ ለውጦችን ለማድረግ እያሰበ ነው። እርምጃው እያንዳንዱ ተማሪ የትም ቢኖር ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ፕሮግራሞች ውስጥ እንዲሳተፍ ተመሳሳይና ፍትኃዊነትን የጠበቀ እድል ይሰጣል።
ኦገስት 21 በተደረገ ስብሰባ የትምህርት ቦርድ የቅርብ ጊዜውን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መርሃ ግብር ትንተና ተመልክቷል። ውይይቱንእዚህ መመልከት ይችላሉ.
ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎችን በማንበብየበለጠ ይወቁ።
በመጪዎቹ ሳምንታት ሁሉም ትምህርት ቤቶች ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ምሽቶችን ያካሂዳሉ። ይህ ከአስተማሪዎችና ከሰራተኞች ጋር ለመገናኘት፣ ተማሪዎ በክፍል ውስጥ ምን እንደሚማር/እንደምትማር የበለጠ ለማወቅ እና ለበጎ ፈቃደኛነት አገልግሎት ለመመዝገብ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። የትምህርት ቤትዎን የዝግጅት ቀን እና ሰዓት ይመልከቱ።
አንድ ልጅ አስቀድሞ እንደተከፈለ በማወቅ የሚወደውን የትምህርት ቤት ምግብ መምረጥ ሲችል የሚሰማውን እፎይታ አስቡት። ለበርካታ ተማሪዎቻችን ይህ በቀላል የሚያገኙት ክብር የእለት ተእለት ጭንቀት ነው። "MCPS Educational Foundation's Dine with Dignity" ዘመቻ በመለገስ፣ ምንም ልጅ እንዳይራብ ወይም በትምህርት ቤት የምሳ ጊዜ ስለ ገንዘብ ክፍያ እንዳይጨነቅ በማድረግ ለተማሪዎች ወሳኝ የምግብ ሁኔታን በቀጥታ ማመቻቸት ይቻላል።
ፋውንዴሽኑ በዚህ አመት $500,000 ግቡን እንዲደርስ ይርዱት፣ ይህም እያንዳንዱ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልገው ኃይል እንዲኖረው ለማድረግ ይረዳል። ዛሬውኑ ይለግሱ
የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት መምሪያ የትምህርት ቤትዎን የቁርስ እና የምሳ ዝርዝር ለማየት እና የአመጋገብ ዝርዝሮችን ለማግኘት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቀላል አድርጎታል። MealViewer ድረ-ገጽ ይጎብኙ።
ቤተሰቦች MySchoolBucks በመጠቀም ወደ ልጃቸው አካውንት ገንዘብ እንዴት ማስገባት እንዳለባቸው ማወቅ ይችላሉ። ይህ አማራጭ በኦንላይን የመክፈል አገልግሎት ወላጆች/አሳዳጊዎች ለቁርስ፣ ለምሳ፣ እና à-la-carte ለተማሪ የካፊቴሪያ ሂሳብ በክሬዲት ወይም በዴቢት ካርድ ቅድመ ክፍያ እንዲፈጽሙ የተዘጋጀ ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
መመልከት ይፈልጋሉ? ማወቅ ያለብዎት ነገር እነሆ፦
Remind, ParentSquare, ParentVUE: ልዩነታቸው ምንድነው? የተማሪ የስነምግባር ደንብ፡ የተሻሻለውን ሰነድ ያንብቡ እና ቪዲዮውን ይመልከቱ። በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤትስለ ውጤት አሰጣጥ ስሌት የተደረጉ ለውጦች፡ ቪዲዮውን ይመልከቱ። የአውቶቡስ መስመርዎን ያግኙ 1፣ 2፣ 3 ቀላል ነው በትምህርት ቤት ስለ ሞባይል ስልኮች አጠቃቀም፡የስልክ ጊዜን መቀነስ ማለት የበለጠ የመማሪያ ጊዜ ማለት ነው። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመፀዳጃ ክፍሎችየትምባሆ ማጬሻዎችን የሚለይ መሣሪያ/Vape Detection Sensors መጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጤናማ የትምህርት አካባቢን ለመጠበቅ ይረዳል።
ምናልባት አምልጦዎት ከሆነ፡ 25-26 ጥሩ ስሜት ተሰምቶናል!
ወደ-ት/ቤት-የመመለስ አውደ ርዕይ ላይ በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ተሳትፏል።