የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ጃኑዋሪ 15, 2026

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

ከተማሪዎ ትምህርት ጋር ያለዎትን ተሳትፎ ይቀጥሉ

የማርክ መስጫ ክፍለጊዜው ወደ ማብቂያው እየተቃረብን ስንመጣ፣ ለተማሪ ስኬት ወሳኝ የሚሆነው በትምህርት ቤት እና በቤት መካከል የሚደረግ የሁለትዮሽ ግንኙነት ነው።

የተማሪዎችን አፈፃፀም በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በርካታ መንገዶች አሉ፡

  • በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ መጨረሻ ላይየሪፖርት ካርዶችይሰጣሉ።

  • ጊዜያዊ ሪፖርቶች፣ በማርክ መስጫ ክፍለጊዜ አራተኛው እና ስድስተኛው ሳምንታት ይሰጣሉ።

  • መምህራንን በስልክ ጥሪዎች እና በኢሜይሎች ማግኘት ይቻላል።

  • የወላጅ/የተንከባካቢ–የመምህር ኮንፈረንሶች ይደረጋሉ።

ስለ ትምህርት ውጤቶች፣ ለተማሪዎች የሚሰጡ የቤት ስራዎች እና የአስተማሪ ግብረመልስ መረጃ ለማግኘት በጣም ጥሩው መንገድ ParentVUE መጠቀም ነው።  

የተማሪዎን የትምህርት አፈፃፀም በተመለከተ ምንም አይነት ድንገተኛ ጥርጣሬ እንዳይኖር ለማረጋገጥ፣ ወላጆች የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦

  • ቀጥታ ተደራሽነት፦ የጊዜያዊ ሪፖርቱ ከተሰጠ በኋላ የተማሪዎ የትምህርት አፈጻጸም ከቀነሰ፣ አስተማሪዎችን በስልክ፣ በኢሜል፣ ወይም በጽሑፍ ማነጋገር ይቻላል።

  • ወቅታዊ ሰነዶችን ማቅረብ፡ የጎደሉ የትምህርት ቤት ስራዎች ካሉ አስተማሪዎች በጊዜ ያሳውቃሉ።

የሠመር ትምህርት ቤት፡ ተጨማሪ እድሎች፣ ተጨማሪ ተደራሽነት፣ ተጨማሪ ድጋፍ ይሰጣል።

በዚህ አመት የሠመር ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ላይ ለውጦች ይደረጋሉ። MCPS ለቤተሰቦች ወጥነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት፣ የትምህርት ጊዜን ውጤታማ ለማድረግ እና የአርብ ቀንን ለዕቅድ ዝግጅት፣ ለሙያ ትምህርት፣ ለሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ እና ለመጓጓዣ ማስተካከያዎች እንዲውል ለማድረግ በሳምንት የአራት ቀናት (ከሰኞ እስከ ሐሙስ፣ ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ 2:30 p.m.,) ተግባራዊ ይደረጋል። ይበልጥ ያንብቡ።

አሁን ማወቅ ያለብዎት፡ የሁለተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ — የትምህርት እርምጃዎን በትኩረት ይመልከቱ።

ሁለተኛው የማርክ መስጫ ወቅት አርብ፣ ጃንዋሪ 23 ይጠናቀቃል፣ ስለዚህ አሁን ተማሪዎች በትምህርታቸው ያሳዩትን እድገት በትኩረት ለመከታተል ጥሩ ጊዜ ነው። ተማሪዎች ስራቸውን በሰዓቱ አጠናቀው ማቅረብ አስፈላጊ ነው፤ በማርክ መስጫ ክፍለጊዜው የመጨረሻ ሳምንት ዘግይቶ የሚቀርብ የትምህርት ስራ ተቀባይነት አይኖረውም። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

የትምህርት ቦርድ በሦስት ፖሊሲዎች ላይ የሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል።

የትምህርት ቦርዱ እንደ ጀነሬቲቭ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የመሳሰሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን MCPS ኦፕሬሽኖች እና መመሪያዎች ጋር ለማዋሃድ የአጠቃቀም መመሪያ መርሆችን ለማዘመን በቀረቡት ፖሊሲ IGS፣ በትምህርት ቤት አገልግሎት የሚሰጡ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በሚመለከት በተደረጉ ማሻሻያዎች ላይ ከማህበረሰብ አስተያየት እንደሰጥባቸው ይፈልጋል። ፖሊሲው ከኦክቶበር 27, 2025 ጀምሮ የማህበረሰብ አስተያየት እንዲሰጥበት ቀርቧል፤ አስተያየቶች እስከ ሰኞ፣ ጃንዋሪ 26 ድረስ መቅረብ አለባቸው። 

ቦርዱ በተጨማሪም ፖሊሲዎችና ደንቦች እንዴት እንደሚዘጋጁና ለሕዝብ እንደሚቀርቡ ለማዘመንና ለማብራራት ፖሊሲ BFA፣ የፖሊሲ ቅንብር፣እና ፖሊሲ GCC፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች፣ MCPS እጩ ተቀጣሪዎች፣ ኮንትራክተሮች፣ እና በጎ ፈቃደኞች የጀርባ ታሪክ ማጣራት ላይ አስተያየቶች እንዲሰጡ የሚፈልግ ሲሆን ይህም የብሔራዊ እና የስቴት የወንጀል ድርጊት መረጃ ዳታቤዞችን በጣት አሻራ ላይ የተመሰረቱ ፍተሻዎችን እና ተጨማሪ የደህንነት መረጃዎችን መስፈርቶች ወደ አንድ አጠቃላይ ሰነድ ለማዋሃድ ጠቃሚ ይሆናል። BFA እና GCC ፖሊሲዎች ከጃንዋሪ 10 ጀምሮ ለአስተያየት የቀረቡ ስለሆነ አስተያየቶች እስከ ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 31 ድረስ መቅረብ አለባቸው።

የረቂቅ ፖሊሲውን ቋንቋ ይገምግሙ እና አስተያየት ይስጡ

ተማሪ የቦርድ አባልነት "SMOB" እጩዎችን የማቅረቢያ ጊዜ አሁን ክፍት ነው

ተማሪ የትምህርት ቦርድ (SMOB) አባል ለመሆን ለመወዳደር የሚፈልጉ ተማሪዎች ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 29 እስከ 5 p.m. ድረስ እጩዎችን ማቅረብ ይችላሉ። SMOB ለመወዳደር ተማሪዎች MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ በአሁኑ ጊዜ 10ኛ ክፍል ወይም 11ኛ ክፍል ተማሪ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪ መሆን አለባቸው።

የመጠቆሚያ ቅጾች SMOB Election Protocols41-43 ገጾች ላይ ይገኛሉ። የተሞሉ ቅጾች፣ ስካን ተደርገው ለተማሪዎች አመራር እና እንቅስቃሴዎች ዳይሬክተር ለሼላ ቼሪ "Shella Cherry, director of Student Leadership and Activities" በኢሜል መላክ አለባቸው።

SMOB የምርጫ ድረ-ገጽ

ማሳሰቢያ፡ የትምህርት አገልግሎት የሰጡ እጩዎችን ጥቆማ ለማቅረብ ክፍት ነው።

የትምህርት ቦርድለሕዝባዊ ትምህርት የላቀ አገልግሎት ለሰጡ የትምህርት አመት 2026 ሽልማቶች እጩዎችን እየተቀበለ ነው። ሽልማቶች የሚሰጡት ለሚከተሉት ነው፦

  • የቢዝነስ አጋር

  • የማህበረሰብ አጋር

  • የት/ቤት አገልግሎት በጎ-ፈቃደኛ

  • የተማሪ አገልግሎት ሽልማት

እጩዎችን እስከ ሰኞ፣ ማርች 9 5 p.m. ድረስ መጠቆም ይቻላል። እጩዎችንበእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል።

MLK ክብረ በዓል ነፃ ኮንሰርት ይቀርባል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ 31ኛው አመታዊ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር ታዳሚ ለመሆን ይዘጋጁ። ክብረ በዓሉ እና የልደት በዓል እሁድ፣ ጃንዋሪ 18 ከቀኑ 4 p.m. ጀምሮ ይከበራል። አድራሻው፦ The Music Center at Strathmore, 5301 Tuckerman Lane, North Bethesda. ዝግጅቱ በነፃ የሚቀርብ ቢሆንም፤ቲኬት መያዝ ያስፈልጋል። 

ተጨማሪ መረጃ

የታሪክ ቀን ውድድር ዳኞች ይፈለጋሉ

የማህበረሰብ አባላትን እና የታሪክ ምሁራንን የሚመለከት ጥሪ፦ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የእናንተን እገዛ ይፈልጋሉ! 2026 የሞንትጎመሪ ካውንቲ የታሪክ ቀን ውድድር ቅዳሜ፣ ማርች 7 ይካሄዳል።

እድሜዎ ቢያንስ 18 ዓመት የሞላዎት ከሆነ፣ በፈቃደኝነት ዳኛ ሆነው የተማሪዎችን ሥራ በመገምገም ለመሥራት ያስቡበት። ተማሪዎች ከሚከተሉት አምስት ምድቦች በአንዱ ምርምር ያቀርባሉ፤ ኤግዚቢሽኖች፣ ትርኢቶች፣ ዘጋቢ ፊልሞች፣ ድረ-ገጾች ወይም ወረቀቶች። ዳኞቹ በታሪካዊ ጥራት እና በአቀራረብ ውጤታማነት ላይ በመመስረት ለውድድር የቀረቡትን ግብአቶች ይገመግማሉ። ዳኞች ከዝግጅቱ በፊት Zoom የስልጠና ክፍለ ጊዜ ይሰጣቸዋል። የቀድሞ ልምድ አስፈላጊ አይደለም።

ዝግጅቱ የሚካሄደው ማርች 7 ከጠዋቱ 8 a.m.–2 p.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በሚከተለው አድራሻ ነው፦ Sligo Middle School, 1401 Dennis Avenue in Silver Spring.

ጥያቄ ካለዎት ወደ Kelli Champagne እና Abbie Lamb በኢሜይል ይላኩ።

ለተመራቂ ሲንየር ተማሪዎች NAACP ስኮላርሺፕ ሽልማት

የሞንትጎመሪ ካውንቲ NAACP ቅርንጫፍ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂ ሲንየሮች $1,000 ስኮላርሺፕ ይሰጣል። ማመልከቻ ለማቅረብ የመጨረሻው ቀን አርብ፣ ማርች 6 ነው። አመልካቾች 3.0 ወይም ከዚያ በላይ GPA ሊኖራቸው ይገባል፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ፣ በእምነት ላይ በተመሰረቱ፣ በሃይማኖት ላይ በተመሰረቱ ወይም በበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት ውስጥ መሳተፍ እና “Unfinished Business: Reclaiming Our Rights Restoring Our Power.” በሚል ጭብጥ ላይ ያተኮረ 300 ቃላት ድርሰት ማቅረብ አለባቸው።

ተጨማሪ መረጃ
ያመልክቱ

ስኮላርሺፑ እሁድ፣ ሜይ 17 በሚካሄው አመታዊ የፍሪደም ፈንድ የእራት ግብዣ ላይ ይሰጣል።

የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀንን ከጥቃት የተረፉ ባለታሪኮች ጋር ማክበር

ዓለም አቀፍ የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀንን ለማክበር፣ MCPS ሐሙስ፣ ጃንዋሪ 29 ከቀኑ 5:30-6:30 p.m. በዙም ዌብናር ያስተናግዳል። ተናጋሪው የሆሎኮስት ሰለባ የነበረው Holocaust survivor Peter Feigl ነው። ተማሪዎች ስለ ተሳትፎአቸው 1 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ይመዝገቡ

በዋትኪንስ ሚል ክላስተር የሥራ ትርኢት ላይ የአካባቢ ድርጅቶች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

የዋትኪንስ ሚል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ረቡዕ፣ ፌብሩዋሪ 25 ከቀኑ 6-8 p.m. በዋትኪንስ ሚል ክላስተር ለቤተሰቦች፣ ለተንከባካቢዎች፣ እና ለማህበረሰብ አባላት የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶችን የሥራ ትርኢት ያዘጋጃል። ይህ ዝግጅት ቤተሰቦችን ከአካባቢው አሠሪዎች፣ ከሥራ ስልጠና ፕሮግራሞች፣ እና ከሥራ ግብረኃይል ሪሶርሶች ጋር ለማገናኘት የታለመ ነው። የሚፈልጉ ድርጅቶች፣ አሠሪዎች፣ እና ፕሮግራሞች በትርኢቱ ላይ እንዲሳተፉ ይፈልጋል። 

የፍላጎት መግለጫ ቅጽ
ዋትኪንስ ሚል ክላስተር የስራ ትርኢት

PEP ለወላጆች እና ለተንከባካቢዎች ነፃ የቨርቹዋል ትምህርቶችን ይሰጣል

የወላጆች ማበረታቻ ፕሮግራም (PEP) በዚህ ክረምት ለወላጆች እና ለተንከባካቢዎች ነፃ የማበረታቻ ድጋፍ እየሰጠ ነው። የስምንት ሳምንት በኦንላይን PEP የቤተሰብን የመቋቋም አቅም የመገንባት ፕሮግራም ቤተሰቦች ግንኙነቶችን እንዲያጠናክሩ፣ የህፃናትን የአእምሮ ጤና እንዲደግፉ፣ እና የትምህርት ስኬትን እንዲያበረታቱ ይረዳል። ቢያንስ አምስት ክፍለ ጊዜዎችን የሚከታተሉ እና ግምገማውን የሚያጠናቅቁ ተሳታፊዎች $50 ዶላር የስጦታ ካርድ ያገኛሉ። ክፍለ ጊዜዎቹ የሚጀምሩት በፌብሩዋሪ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሲሆን በእንግሊዝኛ፣ በስፓንሽኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ይሰጣሉ። ይመዝገቡ/Register.

ቅጹን ለማግኘት ካስቸገረ ወይም ለሚነሱ ጥያቄዎች በስልክ ቁጥር 301-929-8824 ይደውሉ ወይም ኢሜይል ይላኩ

የካውንስል አባሉ ስለ MCPS የሥራ ማስኬጃ በጀት ውይይት የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎችን ሊያካሂዱ ነው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የካውንስል አባል ዊል ጃዋንዶ (Will Jawando ) ስለ MCPS የሥራ ማስኬጃ በጀት ከማህበረሰብ የማዳመጥ ክፍለ ጊዜዎችን ያካሂዳሉ። ጃዋንዶ (Jawando) የካውንስሉ የትምህርት እና የባህል ኮሚቴ ሊቀመንበር ናቸው።

ቀኖቹን ያስታውሱ፦ ማክሰኞ፣ ፈብሩዋሪ 3 (በዙም ላይ)፤ ረቡዕ፣ ማርች 4 እና ረቡዕ፣ ማርች 11። 

ጊዜዎቹን እና ቦታዎችን ጭምር ተጨማሪ መረጃ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። 

ሠመር ራይዝ የተማሪዎች ምዝገባ አሁን ተጀምሯል።

2026 ሠመር ራይዝ "Summer RISE" የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ማክሰኞ፣ ፌብሩዋሪ 17 ድረስ ክፍት ነው። 

ሠመር ራይዝ ከንግድ ተቋማት፣ ከመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር በሙያ ላይ ያተኮረ የትምህርት ልምድ ይሰጣል። ፕሮግራሙ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሶፎሞር ተማሪዎች እና ለጁኒየር ተማሪዎች ክፍት ሲሆን፣ እነዚህ ተማሪዎች በኢንዱስትሪ ምርጫቸው መሰረት ቢያንስ 50 ሰዓታት በአካል፣ በቨርቹዋል ወይም በጣምራ እድሎችን በመጠቀም ከጁን 22 እስከ ጁላይ 24 ድረስ ተቀብለው የሚያለማምዷቸው የሙያ አስተናጋጆችን ያገኛሉ።

የበለጠ ለማወቅ፣ የተማሪ እና የወላጅ/የአሳዳጊ የመረጃ ክፍለ ጊዜ ላይ ይሳተፉ ወይም ሠመር ራይዝ "Summer RISE" ድረ-ገጽ ይጎብኙየሙያ ተለማማጆችን ተቀብለው ለማስተናገድ የአስተናጋጆች ምዝገባ እስከ አርብ፣ ማርች 13 ድረስ ክፍት ነው።

እነዚህን ሌሎች የተማሪ አማራጭ እድሎችን መመልከትዎን እርግጠኛ ይሁኑ፦ 

  • HBCU Fair፡ ለዚህ ዝግጅት ይመዝገቡ፣አርብ፣ ፌብሩዋሪ 13 The Universities at Shady Grove, 9630 Gudelsky Drive in Rockville. MCPS በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት ቀደም ብሎ ተማሪዎች የሚለቀቁ ወይም ት/ቤት የመዘጋት ሁኔታ ካጋጠመው፣ እነዚያ የትምህርት ቀናት ወደ ቨርቹዋል የትምህርት ቀን ይዛወራል። ተጨማሪ መረጃ በቅርቡ ይወጣል።

  • ሲ-ስፓን ተማሪካም ውድድር "C-SPAN StudentCam Competition"፡ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ከውድድሩ ጭብጥ ጋር በተያያዘ "ከነፃነት መግለጫ ጋር በማነጻፀር የአሜሪካን ታሪክ ማሰስ"/“Exploring the American Story through the Declaration of Independence.” በሚል ርዕስ ላይ የቪዲዮ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ከፍተኛው ሽልማት $5,000 ነው። የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 20 ነው።

  • "Arts and Humanities Awards" ሽልማቶች፦ለተውኔት አርቲስቶች እና ለጸሐፊዎች የተማሪ ሽልማቶች ይኖራሉ። ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው። አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት፣ የምክር አገልግሎት እና ስራቸውን የማሳየት እድል ይኖራቸዋል። የጊዜ ገደብ፡- አርብ ጃኑ. 23.

  • ስለ ጥቁሮች ታሪክ የሚቀርብ ውድድር፡ ይህ የድርሰት ጽሑፍ ውድድር 9ኛ–12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ክፍት ነው። ሃያ የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች የሽልማት ገንዘብ ለማሸነፍ ድርሰቶቻቸውን በቀጥታ ታዳሚዎች ፊት እንዲያነቡ ይጋበዛሉ። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ጃንዋሪ 25 ነው።

  • የቀጣዩ ትውልድ የአመራር ቀን "Next Generation Leadership Day" ይህ ዝግጅት 4ኛ እና 5ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የዎርክሾፕ ቀን ነው። ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 በሚካሄደው ዝግጅት ላይ ወርክሾፖችን ለመፍጠር እና ለማቅረብ/አማካሪ ለመሆን የሚችሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ይፈለጋሉ። ወርክሾፕ ለማዘጋጀት እስከ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 13 ድረስ ያመልክቱ። እስከ ሰኞ፣ ማርች 9 ወርክሾፕ ለማቅረብ ያመልክቱ።

  • አክብሮትን ይምረጡ የተሰኘ የቪድኦ ውድድር/"Choose Respect Video Contest" ለመለስተኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ይህ ውድድር በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች የፍቅር ጓደኝነት ጥቃትን በተመለከተ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ኦርጅናል ቪዲዮ ፈጥረው/ቀርጸው እንዲያቀርቡ የተዘጋጀ ውድድር ነው። ቪዲዎችን የሚያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 15 ነው።

  • የጌትስበርግ የመጽሐፍ ፌስቲቫል የግጥም ውድድር፦ የዘንድሮው ጭብጥ "ሰብአዊነት ምንድን ነው?" በተሰኘ ርዕስ የሚቀርብ ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ መሆን አለባቸው። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 20 ነው።

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሳይንስ ትርኢትቅዳሜ፣ ማርች 22 ከጠዋቱ 11:45 a.m.–4 p.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው FDA Building 75, 10903 New Hampshire Avenue ይካሄዳል። 

  • አስተማማኝ የቪዲዮ ውድድር "Keeping It Safe Video Contest"፡ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከ 21 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ተማሪዎች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና አስከፊ ጉዳቶች 30 ሰከንድ ቪዲዮ ፈጥረው/አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል። የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።

  • "Sustainability Poster Contest"፡ ሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች በዚህ አመታዊ ውድድር ላይ የኢነርጂ ቁጠባ፣ የቆሻሻ ቅነሳ፣ እና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ግንዛቤን ለማሳደግ መሳተፍ ይችላሉ። አዲሱን የዲጂታል አርት ይመልከቱ! የመጨረሻው ቀን ዓርብ፣ ኤፕሪል 3 ነው።

MoCo የሠመር ካምፕ ምዝገባ ጃኑዋሪ 20 ይጀመራል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሠመር ካምፖች ምዝገባ ማክሰኞ፣ ጃንዋሪ 20 ከጠዋቱ 6:30 a.m. ላይ ይጀምራል። በሠመር ካምፕ መመሪያ ውስጥ ያሉትን አቅርቦቶች ይመልከቱ። 2026 Rec Assist ማመልከቻዎች አሁን መቀበል ተጀምሯል። ብቁ ለሆኑ የካውንቲ ነዋሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል ይሰጣል።

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2026 Montgomery County Public Schools