MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ማርች 05, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  የመጋቢት 3 የፋሲሊቲዎች የሥራ ክፍለ ጊዜ ዋና ዋና ነጥቦች፡ መረጃው በትክክል የሚያሳየው ነገር

ማክሰኞ፣ ማርች 3፣ የትምህርት ቦርድ በሱፐርኢንቴንደንቱ በተመከረው የ2027–2032 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) ላይ የስፕሪንግ ፋሲሊቲዎች እና የወሰን ስራ ክፍለ ጊዜ/Spring Facilities and Boundaries Work Session አካሂዷል፣ ስለ ምዝገባ አዝማሚያዎች፣ የቤቶች ልማት፣ የረጅም ጊዜ የፋሲሊቲ እቅድ እና ሀሳብ የቀረበባቸው ክልሎች እና የፕሮግራሞች እቅዶች ላይ የታሰበበት እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውይይት ቀጥሏል።

ይበልጥ ያንብቡ።

የማርች 3 ስብሰባን ይመልከቱ

በዚህ ወር፣ ቦርዱ የቻርለስ ደብሊው ዉድዋርድን እንደገና ለመክፈት የአማራጭ Bን የተሻሻለ ቨርዥን እና የቶማስ ኤስ. ዉተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ወደ ክራውን ፋርም ለማዛወር የአማራጭ Hን የተሻሻለ ቨርዥን ላይ የስራ ክፍለ ጊዜዎችን ማካሄዱን ቀጥሏል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።

ቀደም ሲል የተካሄዱ ስብሰባዎችን ይመልከቱ፡

 
  Lace Up for a Cause/ለአንድ ዓላማ የጫማ ክርዎትን ይሰሩ: የበላይ ተቆጣጣሪ ሸፍል በመጪው ኤፕሪል 11

የቀን መቁጠሪያያዎት ላይ ምልክት ያድርጉ እና ስአንድ ዓላማ ስኒከር ጫማዎች ይሰሩ! የመጀመሪያው የሱፐርኢንቴንደንቱ ሸፍል ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ወደ ቦህረር ፓርክ ይመጣል።

የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለማስወገድ እንዲረዳ የMCPS የትምህርት ፋውንዴሽን የመመገቢያ ፕሮግራምን ለመደገፍ የማህበረሰብ እና የንቅናቄ ጠዋት ላይ ይቀላቀሉን። ምዝገባው ከ 30 ዶላር ጀምሮ ሲሆን የሩጫ ልብስ፣ ቲሸርት እና የዝግጅት ቀን እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ!

 
  ማወቅ ያለብዎት ጉዳይ፡ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሠመር ትምህርት ፕሮግራም

ለሰመር ዕቅድ እያወጡ ነው? የMCPS የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሰመር ፕሮግራሞች ተማሪዎች ለምረቃ በትክክለኛው መንገድ ላይ እንዲቆዩ ወይም ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲመለሱ ያግዛሉ። እነዚህ ፕሮግራሞች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ኦሪጅናል ክሬዲት የማግኘት ወይም በሚያስፈልጉ ኮርሶች ላይ ውጤት የማሻሻል እድል ይሰጣቸዋል። በካውንቲው ውስጥ ስድስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ሁለት ክፍለ ጊዜዎች እና በሳምንት ለአራት ቀናት የክፍል ስብሰባዎች ይኖራሉ። ተማሪዎች በሲነርጂ ላይ የምዝገባ ሂደቱን ለማጠናቀቅ የትምህርት ቤቱን አማካሪያቸውን ማነጋገር አለባቸው። 

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 
  RespectFest ወርክሾፖችን፣ ለታዳጊዎች እና ለቤተሰቦች ሪሶርሶችን ይዞ ይመለሳል

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና ወላጆች በRespectFest ወቅት ስለ ጤናማ ግንኙነቶች፣ የፍቅር ጓደኝነት ጥቃትን መከላከል እና ፈቃድ መስጠት እና የማህበረሰብ ሪሶርሶችን መማር ይችላሉ። ይህ አመታዊ ዝግጅት ከማርች 8–14 የሚደረጉ ቨርቹዋል ወርክሾፖችን እና እሁድ፣ ማርች 15 በዊተን ማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል ከ1-4 p.m. በአካል የሚካሄድ ፌስቲቫልን ያቀርባል።የSSL ሰዓቶችን ያግኙ እና የራፍል ሽልማቶችን ያሸንፉ! ተጨማሪ ግንዛቤ ይውሰዱ

 
  የአገልግሎት ሽልማቶችን ለማግኘት የSSL ሰዓቶችን እስከ ማርች 27 ድረስ ያስገቡ

የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) የሽልማት ሰነድ የመጨረሻ ቀን አርብ፣ ማርች 27 ነው። 240 ወይም ከዚያ በላይ የተመዘገቡ የSSL ሰዓቶች ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የክብር አገልግሎት የምስክር ወረቀት ያገኛሉ፣ እና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የ75 ሰዓት መስፈርትን የሚያጠናቅቁ የመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የሱፐርኢንቴንደንቱን የSSL ሽልማት ያገኛሉ። ብቁ ለመሆን፣ ተማሪዎች እስከ ማርች 27 ድረስ የMCPS ቅጽ 560-51 ለትምህርት ቤታቸው የSSL አስተባባሪ ማስገባት አለባቸው። ሌሎች የSSL ቅጾች በሙሉ ከአርብ ሜይ 29 ዓ.ም. በፊት መቅረብ አለባቸው።

ሁሉም የMCPS ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመረቅ 75 የSSL ሰዓታት ማግኘት አለባቸው፣ እናም የስፕሪንግ እረፍት ተማሪዎች በSSL እድሎች ውስጥ ለመሳተፍ አመቺ ጊዜ ነው!ይበልጥ ይወቁ እናእድሎችን ያግኙ

 
  ማሳሰቢያ!
  • 2026–2027 መዋዕለ ሕፃናት፡ የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ParentVUE ፖርታል አማካኝነት በኦንላይን በመካሄድ ላይ ነው። ሴፕቴምበር 1, 2026 ድረስ 5 ዓመት የሚሞላቸው ልጆች ብቁ ናቸው። ቤተሰብዎ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ከሆኑ፣ እዚህ PreentVue አካውንት መክፈት ያስፈልግዎታል።

  • ከ2026–2027 የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት ምዝገባ፦ እስከ ሴፕቴምበር 1፣ 2026 ድረስ 3 ወይም 4 ዓመት የሚሞላቸው ልጆች ላሏቸው ከገቢ አንጻር ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች ነጻ የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት አገልግሎት ይሰጣል።የቅድመ መዋይለ ህጻናት እና የሄድ ስታርት ምዝገባየሚካሄደውበኦንላይንወይም በአካል በማህበረሰብ ቦታዎች በማርች ወቅት

  • የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ሰኞ፣ ማርች 9 ይጀመራል። ስለ ምዝገባ መረጃ ለማግኘት፣ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር አለባቸው። ስለ መርሃ ግብሮቹ እና ክፍያዎችን በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እዚህ ያንብቡ። 

  • ጊዜያዊ የሽግግር ጊዜዎች አርብ፣ ማርች 6፡ ይገኛሉ ጊዜያዊ የሽግግር ጊዜዎች በ ParentVue ላይ ይለቀቃሉ። ቤተሰቡ የParentVue አካውንት ለሌለው ተማሪ ከማርች 10 በፊት ወደ ቤታቸው በፖስታ ይላካሉ። ለማስታወስ ያህል፣ ጊዜያዊ የሽግግር ሪፖርቶች ወላጆች ልጃቸው የመውደቅ አዝማሚያ እንዳለው ወይም ካለፈው የማርክ መስጫ ወቅት አንስቶ ከአንድ በላይ የፊደል ደረጃ መውረዱን እንዲያውቁ ያደርጋል። ከጊዜያዊ ሽግግሩ በኋላ የልጅዎ አፈፃፀም እንደገና ከቀነሰ፣ በቀጥታ ከአስተማሪው ይሰማሉ - በስልክ፣ በኢሜል ወይም በጽሑፍ።

  •  የሕዝብ ትምህርት አገልግሎት ሽልማቶች የትምህርት ቦርድ ዓመታዊ ሽልማቶች የመጨረሻ ቀነ ገደብ ሰኞ፣ ማርች 9 ነው።

  • SAT የትምህርት ቀን፡ MCPS ረቡዕ፣ ማርች 11 በትምህርት ቤት ዓመታዊ SAT ፈተና ያካሂዳል። ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪዎች (2023-2024 የትምህርት አመት ለመጀመሪያ ጊዜ 9ኛ ክፍል የገቡ ተማሪዎች) በዚህ ቀን SAT ፈተና መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። MCPS ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተማሪዎችን ወጪ ይሸፍናል። 

  • የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች የቅጥር ትርኢት፡ ማክሰኞ፣ ማርች 17፣ ከ10:30 a.m.-12:30 p.m በ16651 Crabbs Branch Way in Rockville በሚገኘው የትራንስፖርት አገልግሎቶች ዲቪዥን። ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች MCPS Careers portal ላይ አስፈላጊ መረጃ የሚሰጥ መገለጫ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ 240-740-6080 ይደውሉ ወይም ኢሜይል ይላኩ።

  • የቀጥታ ቲያትር፦ የስነ ጥበብ ቀንን ያስሱ እና በአቅራቢያዎ ያለ ትርኢት ይመልከቱ!

 
  USG የስፕሪንግ ኦፕን ሀውስ ያካሂዳል።

የሼዲ ግሮቭ (USG) ዩኒቨርሲቲዎች የወደፊት ተማሪዎችን እና እንግዶችን ስለ USG ካምፓስ እና በዘጠኝ የዩኒቨርሲቲ አጋሮቹ በUSG ስፕሪንግ 2026 የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ኦፕን ሃውስ ስለሚሰጡት የተለያዩ የዲግሪ መርሃ ግብሮች ቅዳሜ ኤፕሪል 11ቀን ከ10 a.m. to 2 p.m በሚካሄደው ፕሮግራም ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተጋብዘዋል። ተሳታፊዎች ግቢውን መጎብኘት፣ የነፃ ትምህርት እድሎችን ማሰስ፣ ከፕሮግራም አማካሪዎች ጋር መገናኘት እና በቦታው ላይ ሆነው ማመልከት ይችላሉ። ዝግጅቱ የሚካሄደው በህንጻ IV (የባዮሜዲካል ሳይንሶች እና ኢንጂነሪንግ ፋሲሊቲ)፣ 9631 Gudelsky Drive in Rockville ነው።

ተጨማሪ መረጃ

 
  የዝውውር ወቅት አሁን እየተከናወነ ነው፣ ኤፕሪል 7 ያበቃል

ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከተመደቡበት የመኖሪያ አካባቢ ትምህርት ቤት እንዲዛወሩ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸው የMCPS 2026-2027 የትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ (COSA) የዝውውር ወቅት በመካሄድ ላይ ነው። የዝውውር ጥያቄዎች እስከ ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 7 ድረስ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።

 
  አስፈላጊ ቀኖች

*አዲስ* መጪ የተማሪ እድሎች፡

  • የአሜሪካ የግብርና መምሪያ የ1890ቱ የብሔራዊ የምሁራን ፕሮግራም ከ19ኙ የ1890 የመሬት ግራንት ዩኒቨርሲቲዎች በአንዱ በምግብ፣ በግብርና፣ በተፈጥሮ ሀብት ሳይንስ ወይም በሌሎች ተዛማጅ ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ለሚከታተሉ የአሜሪካ ዜጎች የነፃ ትምህርት ዕድል ይሰጣል።መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን እሑድ፣ ማርች 8 ነው።

  • የ Girl Power ውድድር፡ለሴቶች ታሪክ ወር እውቅና ለመስጠት፣ ዓመታዊው ምዝገባዎች አሁን ክፍት ናቸው። እድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ልጃገረዶች ክፍት ሲሆን የዘንድሮው ጭብጥም፡- ባለፉት ጊዜያት እና በአሁኑ ጊዜ ያሉ ሴቶች አስደናቂ እና የገሀዱ ዓለም ሱፐርፓወሮችን አሳይተዋል። ማን ያነሳሳሻል - በታሪክ ውስጥ ትልቅ ስራ የሰራ ሰው፣ የቤተሰብ አባል፣ ጎረቤት ወይም ጠበቃ - እና ለውጥ ለማምጣት ኃይሏን/ስልጣኗን እንዴት ተጠቀመችበት? አሸናፊዎች በጁን ወር በሚካሄደው ክብረ በዓል ላይ ይጋበዛሉ።ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።

  • ቀኑን ያስታውሱ፡ The Leadership Academy for Social Justice (LASJ) ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11፣ በዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ 10:30 a.m.-1 p.m. የማህበራዊ ፍትህ ትርኢት ያካሂዳል።

  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርጫ ሰራተኞችን መፈለግ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምርጫ ቦርድ ለ2026 የግዛት ቀዳሚ ምርጫ የምርጫ ሰራተኞች ሆነው እንዲያገለግሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ይፈልጋል። ተማሪዎች ለሰሩበት ለእያንዳንዱ ሙሉ ቀን እስከ $250 ወይም እስከ 25 የSSL ሰዓታት ማግኘት ይችላሉ። አመልካቾች የአሜሪካ ዜጎች፣ የሜሪላንድ ነዋሪዎች፣ ቢያንስ 16 ዓመት የሞላቸው እና ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው። ሁለት ቋንቋ የሚናገሩ ተማሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ።

ሌሎች ማስታወሻዎች፡

  • Latina Legacy Conference፡- ለላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሴት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ይህ ኮንፈረንስ ቅዳሜ፣ ማርች 7 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register

  • የማት ፓፒርሜስተር ሽልማት/The Matt Papirmeister Award፡ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኪነጥበብ/አርት ተማሪዎች ክፍት ነው። የገንዘብ ሽልማት፡ $3,500 ዶላር፣ $3,000 ዶላር እና $2,500 ዶላር ተዘጋጅቷል።መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን እሑድ፣ ማርች 15 ነው።

  • አስተማማኝ የቪዲዮ ውድድር "Keeping It Safe Video Contest"፡ ውድድሩ ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ከ 21 ዓመት እድሜ በታች የሆኑ ተማሪዎች የአልኮል መጠጥ መጠጣት ስለሚያስከትላቸው አደጋዎች እና አስከፊ ጉዳቶች 30 ሰከንድ ቪዲዮ ፈጥረው/አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።

  • Sober Vibes Essay Contest: የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ሲንየሮች ከፕሮም በፊት፣ በፕሮም ወቅት፣ ወይም ከዚያ በኋላ መጠጥ እንዳይጠጡ አሳማኝ የመወዳደሪያ ድርሰት እንዲጽፉ ይበረታታሉ። ቪዲዮ ለውድድር መቅረብ ያለበት የመጨረሻው ቀን ማክሰኞ፣ ማርች 31 ነው።

  • የሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች ደህንነት ማዕከል 2026 የስነጥበብ ትርኢት ያዘጋጃል፡ የዘንድሮው ጭብጥ፣ ለወደፊት ዝግጁ የሆኑ ትምህርት ቤቶች፣ 3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ደህንነት ለእነሱ ምን ማለት እንደሆነ ያላቸውን አመለካከት እንዲያጋሩ ጥሪ ያቀርባል።የመጨረሻ ቀን፡ እሑድ፣ ሜይ 31 ነው።

 
  የትምህርት በጀት መድረኮች ለማርች 11 ተዘጋጅተዋል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምክር ቤት የትምህርት እና የባህል ኮሚቴ ሊቀመንበር ዊል ጃዋንዶ በቅርቡ የሚካሄደውን የትምህርት በጀት መድረክ ያስተናግዳሊ። MCPS ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር እና የሞንትጎመሪ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጄርሜይን ዊሊያምስ ጭምር ይሳተፋሉ። የካውንቲው ምክር ቤት የትምህርት እና የባህል ኮሚቴ ለጠቅላላው የካውንቲ ምክር ቤት የትምህርት ወጪን በተመለከተ ምክረ ሀሳቦችን የማቅረብ ኃላፊነት አለበት። መድረኩ ረቡዕ፣ ማርች 11፣ በ 6:30 p.m በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። 

ይመዝገቡ/RSVP
ስለ ዝግጅቱ አጭር የመግለጫ ጽሑፍ 

 
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2026 Montgomery County Public Schools