አበይት ጉዳዮች
ጁን 04, 2026
|
|
|
|
|
ቦርዱ የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት አጽድቋል፤ የተደረገው የሠራተኞች ቅነሳ አንዳንድ የሠራተኞችን ቁጥር እና ፕሮግራሞችን ይነካሉ። |
|
ዛሬ (ጁን 4)፣ የትምህርት ቦርድ የካውንቲው ካውንስል ያደረገውን የበጀት ውሳኔ ተከትሎ የበጀት ዓመት 2027 የሥራ ማስኬጃ በጀት ላይ የመጨረሻ ውሳኔ አድርጓል፣ ይኼውም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ከጠየቀው በጀት $36 ሚሊዮን ዶላር በታች እንዲሆን ተደርጓል። MCPS ሁሉንም የስቴት እና የፌዴራል መስፈርቶችን ማሟላት እና ለተማሪዎች ወሳኝ አገልግሎቶችን መስጠቱን ይቀጥላል።
ውሳኔውንይመልከቱ፣ተጨማሪ ግንዛቤ ለማግኘት ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
በሊተርሲ እና በሂሳብ ትምህርት የሶስተኛ ሩብ ዓመት የትምህርት አፈፃፀም ግምገማ እድገት አሳይቷል |
|
ቦርዱ ጁን 4 በተካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ፣ በሊተርሲ እና በሂሳብ ትምሕርት ዘርፍ አበረታች ውጤቶችን የሚያሳይ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የትምህርት አፈጻጸም ወቅታዊ መረጃ አግኝቷል። በቀረበው ሪፖርት መሠረት የሊተርሲ ትምህርት ችሎታ ውጤት ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን በጉልህ አሳይቷል፣ በሪፖርቱ ላይ እንደተገለፀው የሊተርሲ ትምህርት ችሎታ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች በጉልህ የታየ ሲሆን፣ ይህም ተማሪዎች በመሠረታዊ የሊተርሲ ችሎታ (DIBELS) የውጤት አመልካች ላይ ከነበረው 57.8% ወደ 65.7% እና ካለፈው ዓመት (2025 መኸር እስከ ክረምት 2026) ጋር ሲነጻጸር በሌክቱራ 62.3% ወደ 72% አድጓል - ሁለቱም የሊተርሲ ትምህርት ችሎታ ቁልፍ መለኪያዎች ናቸው።። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
በስቴቱ MCPS ባለ ተሰጥኦ እና ከፍተኛ ችሎታ ፕሮግራሞች ላይ ፈጠራዎች ተንፀባርቀዋል። |
|
የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምሪያ (MSDE) የትምህርት አመት 2025–2026 ባለ ተሰጥኦ እና ከፍተኛ ችሎታ ተከታታይ ትምህርት ውስጥ ከተካተቱት አራት የትምህርት ስርዓቶች አንዱ እንደሆነ MCPS እውቅና ሰጥቶታል፣ ይህም የላቀ ትምህርት አዳዲስ አቀራረቦችን አጉልቶ ያሳያል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
የዋሽንግተን ፖስት ሽልማት ለሮክ ቪው ትምህርት ባለሙያና ርዕሰ መምህር ሉዊት ቤኔት እውቅና ሰጥቷል |
|
የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ጁን 4 ቀን የትምህርት አመት 2026 የርዕሰ መምህር እና የአመቱ ምርጥ መምህር ሽልማት አሸናፊዎችን እና የመጨረሻ እጩዎችን አስታውቋል። በየዓመቱ፣ ዘ ፖስት በትምህርት ቤት አመራር ረገድ የላቀ ብቃትን ለማበረታታት እና በዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮፖሊታን አካባቢ የትምህርት መሻሻል አስተዋጽኦ ለማድረግ ሽልማቶችን ያቀርባል። ስለ MCPS የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች የበለጠ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
ለስቴት ቤተ-መጻሕፍት ሽልማት ሁለት የመጨረሻ እጩዎች ተመርጠዋል። |
|
ሁለት የሚዲያ ባለሙያዎች 2026 የሜሪላንድ ትምህርት ቤት ቤተ-መጻሕፍት ባለሙያ ሽልማት የመጨረሻ እጩዎች ሆነዋል፣ ይህም የትምህርት ቤት ቤተ-መጻሕፍት ባለሙያዎችን በትምህርት ቤት ቤተ-መጻሕፍት ሚዲያ ዘርፍ ላሳዩት አርአያነት ያለው አገልግሎት እና አስደናቂ ስኬቶችን ለማበረታታት የተበረከተ ነው። ከሃይላንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አሌክሳንድራ ሞሰስ/Alexandra Moses እና ከክላርክስበርግ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳሪያ ቴይለር/Daria Taylorከስቴት እውቅና ከተሰጣቸው 10 ከፍተኛ የመጨረሻ እጩዎች መካከል ናቸው።
ላውራ ኤሊስ/Laura Ellis ከዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ከፍላወር ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መሊሳ ኪንግ/Melissa King እንዲሁም ለሽልማቱ ታጭተዋል። አሸናፊዎቹ በኦክቶበር ወር በሚካሄደው የሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች ቤተ-መጻሕፍት ባለሙያዎች ኮንፈረንስ ላይ ይገለጻሉ። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ትምህርት ቤቶች (በቅርቡ) ይዘጋሉ፣ መልሶ የመስጠት እንቅስቃሴ ይጀመራል |
|
አርብ፣ ጁላይ 24 ከጠዋቱ 9 a.m.–2 p.m. በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ Gaithersburg High School, 101 Education Blvd. በሚካሄደው 25ኛው አመታዊ የትምህርት ቁሳቁሶች አቅርቦት የመሰብሰብ እንቅስቃሴ ላይ ይሳተፉ። /በጌትስበርግ። ቤተሰቦች አስደሳች እና ትርጉም ያለው የድጋፍ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ፣ የማህበረሰብ፣ እና የግንኙነት ቀን ከእኛ ጋር እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል። ለትምህርት ቤት የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን በነፃ ይውሰዱ። በተጨማሪም፣ የአፕካውንቲ ማዕከል እና Rise-N-Shine Foundation ለቤተሰቦች የምግብ ሳጥኖችን ያሰራጫሉ፣ SNAP ጥቅማጥቅሞች፣ ነፃ እና ቅናሽ ዋጋ ያላቸው ምግቦች እና የሠመር የድጋፍ ፕሮግራሞች የመሳሰሉ ወሳኝ አገልግሎቶችን ለማግኘት የመመዝገብ እድሎች ይኖራሉ።
ተማሪዎች ከዝግጅቱ በፊት እና በዝግጅቱ ወቅት በእርዳታ የተሰበሰቡ የትምህርት ቁሳቁሶችን ለማራገፍ፣ ለመደርደር፣ እና እንደገና ለማሸግ በፈቃደኝነት ሲያገለግሉ የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ። በጎ ፈቃደኞች ከጁላይ 20 እስከ ጁላይ 23 ያስፈልጋሉ።
የተማሪ በጎ ፈቃደኛ ቅጽ
|
|
|
|
|
|
ስለ መጪዎቹ የጊዜ ሰሌዳ ማሳሰቢያ፦ |
|
ረቡዕ፣ ጁን 17 ለተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ቀን ነው። የትምህርት ቤት የመጨረሻ ቀን ሐሙስ፣ ጁን 18 ሲሆን K-12 ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ነው። አርብ፣ ጁን 19 ስርዓትአቀፍ ዝግ የሚሆንበት ቀን ነው፤ ሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶችና ቢሮዎች ዝግ ይሆናሉ።
የመጨረሻ የሪፖርት ካርዶች እስከ ሰኞ፣ ጁን 29 ድረስ ParentVue ላይ ይገኛሉ፣ እስከ ማክሰኞ፣ ጁን 30 ድረስ በፖስታ ቤት ወደ ቤት ይላካሉ።
|
|
|
|
|
|
አሁን ማወቅ ይችላሉ — MCPS ድረ ገጽ |
|
MCPS ድረ ገጽ ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ ለሠራተኞች እና ለማህበረሰባችን መረጃ ለማግኘት በጣም ጥሩ ከሆኑ የመረጃ ምንጮች አንዱ መሆኑን ያውቃሉ? በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን፣ አዳዲስ መገልገያዎችን/ሪሶርሶችን እና የሚፈልጉትን ለማግኘት ቀላል መንገዶችን በመጠቀም ማሻሻያዎች ይደረጋሉ። የሚፈልጉትን ርዕስ ለማግኘት "AskMCPS chat box" ላይ ወይም የፍለጋ ዝርዝር ላይ ይተይቡ። እና፣ 'በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጉዳዮችን' ለማወቅ ለምሳሌ፦ የምሳ ዝርዝሮች፣ የአውቶቡስ መርሃ ግብሮች፣ የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር እና ቅጾች የመሳሰሉ በጣም የሚገበኙ ገጾች ፈጣን ምላሽ ያመጣልዎታል።
በሚከተሉት ቋንቋዎች ይመልከቱ፦ English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese
|
|
|
|
ተማሪዎች መቀመጫቸውን እንዲይዙ ያበረታቷቸው |
|
ተማሪዎች 2026–2027 የትምህርት አመት ለትምህርት ቦርድ የኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ አባል ለመሆን እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ። ይህ ከዲስትሪክት መሪዎች ጋር በመተባበር ለመሥራት፣ በዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የግንኙነት እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ጥረቶችን ለማጠናከር እና MCPS ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ የተማሪዎችን ድምጽ ለመወከል የሚያስችል እድል ነው። ማመልከቻዎች እስከ አርብ፣ ጁን 19 እኩለ ቀን ድረስ መቅረብ አለባቸው።ያመልክቱ
|
|
|
|
|
|
የሠመር እረፍት ጊዜዎን ወደ አገልግሎት ይለውጡት |
|
የሠመር ወቅት ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት (SSL) እድሎች ላይ ለመሳተፍ እና 75 ሰዓት የስቴት የምረቃ መስፈርትን ለማሟላት እና SSL ሰዓቶችን ለማግኘት ጠቃሚ ጊዜ ነው! የአሁኑ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች አርብ፣ ጁን 19 ጀምሮ SSL ሰዓቶችን ማግኘት መጀመር ይችላሉ።
በጁን ወር ያሉ እድሎች
|
|
|
|
|
|
USG ነፃ የሙያ ቅኝት ፕሮግራም ያቀርባል |
|
በሼዲ ግሮቭ ዩኒቨርሲቲዎች ከ ጁን 29 እስከ ጁላይ 1 (በየቀኑ ከጠዋቱ 9 a.m.- 3 p.m.) ነፃ reachHIRE Summer Bridge program ፕሮግራም ያካሄዳል። ፕሮግራሙ፣ ለጀማሪ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ ሲንየሮች ድረስ ክፍት ሲሆን፣ ወደፊት ስለመጪዎቹ የአካዳሚክ እና የሙያ አማራጮች ግንዛቤ ለማግኘት ከባለሙያዎች ጋር የመገናኘት እድል ይሰጣል። ተማሪዎች በመስተጋብራዊ አውደ ጥናቶች አማካኝነት የሙያ ዝግጁነት ክህሎቶችን ለመገንባት በቡድን ሆነው ይሰራሉ እና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሣተፍ የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን እና ስራዎችን ያስሳሉ። ምሳ ይቀርባል። ይመዝገቡ
|
|
|
|
MCPS ደንቦችን የማሻሻያ አስተያየት እንዲሰጥባቸው አቅርቧል |
|
MCPS በአሁኑ ጊዜ በግምገማ ላይ ባሉ በርካታ ደንቦች ላይ በታቀዱ ማሻሻያዎች ላይ የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል። ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች ፣እና የማህበረሰብ አባላት የለውጦቹን ረቂቅ እንዲገመግሙ እና በታቀዱት ማሻሻያዎች ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ይበረታታሉ።
በአሁኑ ጊዜ የሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥብቸው የተዘጋጁት ረቂቅ ማሻሻያዎች የትምህርት ውጤት አሰጣጥ እና ሪፖርት ማድረግ፤ ምደባ፣ ማስታወቅያ፣ ማቆየት እና የተማሪዎችን የተፋጠነ ትምህርት፤ የግል ሞባይል ስልኮች፤ አጠቃላይ የጤና ትምህርት እና የተማሪዎች በትምሕርት ላይ መገኘትን ጨምሮ የሚዳስሱ ርዕሶችን ያካትታሉ።
የታቀዱትን ማሻሻያዎች ለመገምገም እና ስለ ሕዝባዊ አስተያየት ሂደት የበለጠ ለማወቅ፣ MCPS የህዝብ አስተያየት ድረ ገጽ ይጎብኙ። በታቀዱት ለውጦች ረቂቅ ላይ አስተያየቶች በኢሜይል ሊቀርቡ ይችላሉ።
|
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያ |
|
|
|
|
|
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ |
|
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|